Get Mystery Box with random crypto!

ወቅታዊ መረጃ ከዩቲዩብ በስፒከር ሰምተሃል የተባለ ግለሰብ በቁጥጥር ስር ዋለ በመተከል ዞን በድባ | FastMereja.com

ወቅታዊ መረጃ ከዩቲዩብ በስፒከር ሰምተሃል የተባለ ግለሰብ በቁጥጥር ስር ዋለ

በመተከል ዞን በድባጤ ወረዳ በርበር ቀበሌ በሞባይል መሸጫ ሱቅ ውስጥ የሚሰራ ግለሰብ ወቅታዊ መረጃ ከዩቲዩብ በስፒከር ሰምተሃል የተባለ ግለሰብ መታሰሩ ተሰምቷል ። አ/ቶ ኦላኔ ጉሲ የተባለን ግለሰብ በዛሬው ዕለት ከረፋዱ አራት ሰዓት ገደማ ፖሊስ እና የበርበር ቀበሌ ሊቀ መንበር ከስራ ቦታው ትፈለጋለህ በሚል ወደ ንዑስ ፖሊስ ጣቢያ መወሰዱን ድርጊቱን የተመለከቱ የአይን እማኞች ለብስራት ራዲዮ ተናግረዋል ። ግለሰቡ በስፒከር ሲከታተል የነበረው መረጃ ወቅታዊ ጉዳይ ጋር የተያያዘ እንደነበር ተገልጿል ።
ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ ብስራት ራዲዮ የበርበር ቀበሌ ምክትል ሊቀ መንበር የጠየቀ ሲሆን ግለሰቡ እንዲታሰር የተደረገው ሲሰማው በተገኘው መረጃ ነው ብለዋል ። ነገር ግን ጉዳዩን በተመለከተ ከእኛ ጋር መነጋገር ሲገባ ወደ መገናኛ ብዙሃን መውሰድ አግባብ አይደለም ሲሉ አክለዋል።

Via: ዳጉ ጆርናል!

@fastmereja