Get Mystery Box with random crypto!

FastMereja.com

የቴሌግራም ቻናል አርማ fastmereja — FastMereja.com F
የቴሌግራም ቻናል አርማ fastmereja — FastMereja.com
የሰርጥ አድራሻ: @fastmereja
ምድቦች: ዜና , ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 36.80K
የሰርጥ መግለጫ

FastMereja.net

Ratings & Reviews

2.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 19

2022-10-15 12:03:21
ዛሬ በባህር ዳር መካሄድ በጀመረው 10ኛው ጣና ፎረም እየተካፈሉ ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ እና የሱዳን ሉዓላዊ የሽግግር ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ሌተናል ጄነራል አብደል ፈታህ አል ቡርሃን ከፎረሙ ጎን ለጎን በሁለቱ ሀገራት የጋራ ጉዳዮች ዙሪያ መምከራቸውን ኢቢሲ ዘግበዋል።
@FastMereja
8.6K views09:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-15 11:56:23 "የህወሓት መሪ ተይዟል በሚል የሚናፈሰው ወሬ ሀሰት ነው" መከላከያ ሰራዊት
@FastMereja
ከመከላከያ ሰራዊት የተሰጠው መግለጫ ሙሉ እንደሚከተለው ይቀርባል

ሰሞኑን በማህበራዊ ሚዲያ የአሸባሪው ህወሓት መሪ ደብረጺዮን ገ/ሚካኤል ተያዘ እየተባለ የሚናፈሰው ወሬ ጠላት ሆን ብሎ የፈጠረው መሆኑን እንገልፃለን፡፡

አሸባሪው ህወሓት ለ3ኛ ጊዜ የከፈተውን ጦርነት ጀግናው የመከላከያ ሰራዊታችን እየመከተ ባለበት በአሁኑ ወቅት የሽብር ቡድኑ መሪ ደብረጺዮን ተያዘ ተብሎ የሚነዛው ወሬ ለማዘናጋት መሆኑ መታወቅ አለበት፡፡

በማህበራዊ ሚዲያ እየተዘዋወረ ያለው የቪዲዮ መረጃ ደብረጺዮን ተይዟል ፤ ጦርነቱም ቆሟል በሚል እየተላለፈ ያለው መልዕክት ጠላት አጀንዳውን ለማስፈፀም ሆን ብሎ ያደረገው መሆኑን እናሳውቃለን፡፡

አሸባሪው የህወሓት ቡድን ሴራዎችን እና ሌሎች ሃሰተኛ መረጃዎችን ፈብርኮ ህዝብን ግራ ማጋባት እና ማዘናጋት የለመደው ተግባሩ በመሆኑ ሌሎች የማህበራዊ ሚዲያዎችም ጠላት ሆን ብሎ የሚያሰራጫቸውን መረጃዎች ከማራገብ እንዲቆጠቡ እንገልፃለን።
7.7K viewsedited  08:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-15 10:57:13 የአባ ሰንጋ በሽታ መከሰቱን ከዘገብን በኋላ አንድ ተከታተያችን (Vit mamila) የሚከተለውን ስለ በሽታው ጠቃሚ መረጃ ለፋስት መረጃ ልኮልናል።
#FastMereja
አባ ሰንጋ (Anthrax)
አስከፊው በሽታ

የበሽታው መንስኤ
አንትራክስ (Anthrax) በሽታው ባሲለስ አንትራሲስ (Bacillus anthracis) በሚባል በሽታ አምጪ ተህዋሲያን የሚከሰት ሲሆን ይህ ተህዋሲያን በአፈር ውስጥ ስፖር(Spore) በመፍጠር ለአመታት የመደበቅ አቅም ያለው ነው። በሽታው ብዙ አይነት አጥቢ እንስሳትን ያጠቃል። በሽታውን በሁለተኛው አለም ጦርነት ባይሎጂካል መሳሪያ (Biological Weapon) ይጠቀሙበት እንደነበር ይገለፃል። በሀገራችን ኢትዮጵያ ይህ በሽታ ረጅም አመታትን አስቆጥሯል።

የበሽታው ምልክቶች

ይህ በሽታ በጥቂት ሰአታቶች ውስጥ ለሞት የሚዳርግ እና ተላላፊ የሆነ በሽታ ነው። ሶስት የበሽታው ፍጥነት በደረጃ ሲቀመጡ እጅግ ፈጣን (peracute) ፈጣን(acute) እና መካከለኛ ፈጣን (sub acute) ናቸው። የበሽታው ዋና እና የተለየ ምልክት በአፍ እና በአፍንጫ ያልረጋ ደም መፍሰስ ሲሆን በተጨማሪም እንስሳቶቹ ማመንዠግ ያቆማሉ፣ ከፍተኛ ትኩሳት ይኖራል፣ ከፍተኛ የመተንፈስ ችግርም የሚያጋጥማቸው ይሆናል። ክሮኒክ አንትራክስ (chronic anthrax) በብዛት የሚታየው በአሳማዎች ሲሆን ጉሮሮ አካባቢ እብጠት ይኖራቸዋል በተጨማሪም ከአፋቸው አረፋ የሚደፍቁም ይሆናል።

የበሽታው ስርጭት
በሀገረ ዛምቢያ በዚህ በሽታ በትንሹ 30 ሰዎች በ1992 እ.አ.አ ሞተዋል። በሀገረ አልጀሪያ ደግሞ 59 ሰዎች አንድ የቤተሰብ አባላት መጠቃታቸው ተዘግቧል። በተጨማሪም አንትራክስን (Anthrax) ሀያል የአለም ሀገራት እንደ ባይሎጂካል መሳሪያ (Biological Weapons) የሚጠቀሙበት ሲሆን በ1979 እ.አ.አ በራሺያ እና በአሜሪካ ድንበር መሀል ሰቨርድሎስኪ (sverdlovsk) በምትባል ግዛት ላይ በነበረው አለመግባባት በአጠቃላይ በሺዎች መሞታቸውን የአሜሪካ መንግስት ይፋ አድርጓል። በወቅቱ ለግል እርባታ ድርጅቶች በሚዘጋጅ መኖ (bone meal) በማድረግ አልያም በአየር ወለድ በሽታ በእፅዋቶች አማካኝነት ይሆናል የሚል መላ ምት አስቀምጠዋል።

የበሽታው ህክምና
በፍጥነት ህክምና የሚያገኙ እንስሳት የመትረፍ እድል አላቸው። በመጀሪያ በደም ስር የሚሰጥ ቤንዛይሊንፔንሲልን (benzylpenicillin) ሲሆን አስከትለን ኢንትራመስኩላር (Intramuscular) አሞክሲሊን (Amoxicillin) የምንሰጥ ይሆናል።

የበሽታው መከላከያ ዘዴ
በአንትራክስ የሞተ እንስሳ በውስጡ በሽታ አምጪ ተህዋሲያኑ ባሲለስ አንትራሲስ በብዛት የሚራባ ሲሆን ስጋውን ለመጠቀም መሞከር እና ማረድ አካባቢውን(ውሀውን፣ ሳሩን፣ አፈሩን) በዚህ በሽታ እንዲበከል ማድረግ ነው። በኋላም እንስሳቶች ለግጦሽ በሚሰማሩበት ወቅት ይተላለፍባቸዋል። በተለይ ከባድ ዝናብ ሲጥል አፈሩ ለመደበኛ አየር ስለሚጋለጥ በሽታው ሊባባስ ይችላል።

በዋናነት በበሽታው የተጠቁትን 2ሜትር ቆፍሮ አቃጥሎ መቅበር፣ የአካባቢ ንፅህና መጠበቅ፣ ዲስኢንፌክታንትን መጠቀም ፣ በሚኖረው ንኪኪ ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግ በበሽታው ላልተጠቁት ክትባት መስጠት እጅግ አስፈላጊ ነው።
6.9K views07:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-14 21:46:46
ከመንገድ ላይ ወድቆ የተገኘውን 42,000/አርባ ሁለት ሺህ/ብር ለሳውላ ከተማ ፖሊስ ጽ/ቤት አስረከበች።

ወ/ሮ ሸዋ ተሾመ የተባለችው የሳውላ ከተማ ነዋሪ የሆነቸው ግለሰብ ማንም በሌለበት በመንገድ ላይ በጥቁር ፌስታል ታስሮ ወድቆ የነበረውን ገንዘብ በማግኘት የሰው ላብ እና የሰው ሀቅ ገንዘብ ስለሆነ ባለቤቱን መድረስ አለበት በማለት በተለያየ መንገድ ባለቤቱ ተፈልጎ በፖሊስ አማካኝነት መድረስ አለበት በማለት በቀን 02/02/2015 ዓ/ም ወደ ተቋማችን በአካል ቀርባ አስረክባለች።

የተገኘውን ገንዘብ በአደራ የተረከበው የሳውላ ከተማ ፖሊስ ጽ/ቤት የገንዘቡን ባለቤት የሆነውን የደንባ ጎፋ ወረዳ ሎጠ ቀበሌ ነዋሪ አቶ አማሬ ዳሞታ መሆኑን ማግኘት ችሏል።

ወድቆ የተገኘውን ገንዘብ የአቶ አማሬ ዳሞታ መሆኑን አስፈላጊው ማጣራት ከተደረገ በኃላ ዛሬ በቀን 04/02/2015 ዓ/ም ለባለቤቱ ማስረከብ ተችሏል ሲል ከፖሊስ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
7.3K views18:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-14 21:46:18
#የጭካኔ_ጥግ

#እናት 4ህፃናት ልጆቿን እንጀራ ለማጉረስ ሁሌም ለሊት 12:00ሰዓት ከቤት ወጥታ ካገኘች የቀን ስራዋን
ሰራርታ ማታ 12:00ሰዓት ትመለሳለች!!

ግንበኛው #አባት ደግሞ አረፋፍዶ ጠዋት 2:00ሰዓት ከቤት ይወጣና ስራውን ሰርቶ እንደጨረሰ እሱም ወደ ልጆቹ ይመለሳል!!

በአንደኛው ክፉ ቀን እናት እንደተለመደው በለሊት መውጣቷን ተከትሎ አባት የ14ዓመቷ የ6ተኛ ክፍል ተማሪ የመጀመሪያ ሴት ልጁን"አባዬ እባክህ ተወኝ" እያለችው አስችሎት በተኛችበት በጭካኔ ደፈራት! #አውሬ_ነው!!

ህፃኗ ልጅ መናገር እየፈራች ስቃይዋን እንደምንም ችላ ብትኖር በድጋሚ የእናት መውጫ ሰዓት ጠብቆ አንገላቶ ደፈራት!!

በጣም ፈሪ፣ምንም አይነት የወንድ ጓደኛ የሌላት ሴት
ከወራት በኋላ በአካባቢና ጎረቤት ውትወታ ሰትመረመር ምንም የማታውቀው የ14ዓመት ህፃን "የ3ወር እርጉዝ ነሽ" ተባለች!አማራጭ ስላልነበራት ሁሉንም ለፖሊስ ተናገረች!!

አረመኔው አባት እስር ቤት ገብቶ ፍርድ ቤት ቆሞ 18ዓመት ቢፈረድበትም ህፃኗ ከአባቷ ያረገዘችውን ጨቅላ ከ15ቀናት በፊት ወልዳለች!!ትምህርቷን አቋርጣለች!!ጡት ማጥባት ስላልቻለች የአንድ አመት ልጅ ያላት እናቷ እያገዘቻት በደሳሳ ጎጆአቸው ውስጥ በስቃይ እየኖሩ አሉ!!

አሁን እናትና ልጅ የሚፈልጉት ህፃኗ ያቋረጠችውን ትምህርት እንድትቀጥል፣የስነልቦና ድጋፍ እንዲደረግላት፣ልጇም የሆነበትን ሳያውቅ ከአካባቢው ርቆ እንዲያድግ ከምትኖርበት አዋሳ ውጪ ያለ ድርጅት እንዲረከባት #እባካችሁን አግዙኝ እያለቻችሁ ነው! #እየፀለይንላት #ሼር በማድረግ የሚቀበላትን ድርጅት እንፈልግላት
0939790111-ተስፋሚካኤል
0941767845-ሙሉነሽ
6.9K views18:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-14 20:34:47 በካፋ ዞን ቦንጋ ከተማ የአባ ሰንጋ በሽታ በመከሰቱ ህብረተሰቡ ስጋ ከመመገብ እንዲቆጠብ ተገለፀ።

ጥቅምት 4 ቀን 2015 ዓ.ም በካፋ ዞን የቦንጋ ከተማ አስተዳደር ከተማ ግብርና ጽ/ቤት የእንስሳት ጤና ባለሙያ የሆኑት አቶ ወንድሙ አበበ እንደገለፁት ፣ ለቅዳሜ እርድ ከተዘጋጁ የእርድ በሬዎች ውስጥ አንድ በሬ በድንገት በአባ ሰንጋ በሽታ ምክንያት ሞቶ መገኘቱን ተናግረዋል፡፡

በሬው ከመሞቱ በፊት ከሌሎች በሬዎች ጋር የተቀላቀለ በመሆኑ ከዚህም ጋር ተያይዞ ሌሎች በሬዎች ላይ የበሽታው ምልክት ታይቷል ብለዋል፡፡

በአፍ ፣ በአፍንጫና በቂጥ እንዲሁም ላም ከሆነች በሽንት መሽኛ ቀዳዳ የደምና መሰል ፈሳሽ በሚታይበት ጊዜ የአባ ሰንጋ በሽታ መሆኑ ይጠረጠራል ሲሉ ገልፀዋል፡፡

አባ ሰንጋ ከሰው ወደ እንስሳ ፣ ከእንስሳት ወደ ሰው የሚተላለፍ ገዳይ በሽታ ነው ያሉት አቶ ወንድሙ ፣ ከዞንና ከከተማ መዋቅር የተውጣጡ የባለሙያዎች ቡድን እርድ እንዳይካሄድ ውይይት በማድረግ ተወስኗል ብለዋል፡፡

በሽታው እጅግ አጣዳፊ በመሆኑ የህብረተሰቡን ጤና ለመጠበቅ በአከባቢው የሚገኙ ከብቶችን በማከም የበሽታውን ስርጭት ለመግታት ጥረት እናደርጋለን ሲሉ አክለዋል፡፡

አቶ ወንድሙ አያይዘውም እርድ ከማገድ ባለፈ ለእርድ የተዘጋጁ በሬዎች በባለሙያዎች መታየት እንዳለባቸው ገልጸው ፣ የሞተውን በሬ አከባቢውን በማይበክል ሁኔታ ለመቅበር ከማዘጋጃ ቤት ጋር በመሆን አስፈላጊውን ግብዓት የማዘጋጀት ሥራ በመሠራት ላይ ይገኛል ብለዋል፡፡

ከዚህ ጋር ተያይዞ የአከባቢው ነዋሪዎች የእንስሳት ኮቴ ተቆጥሮ የበሽታው ስርጭት ያለመስፋፋቱ እስኪረጋገጥ ድረስ ማንኛውንም እርድ ማካሄድ እንደማይገባቸው ተናግረው ፣ ህብረተሰቡ ላልተወሰነ ጊዜ ስጋ እንዳይመገብ አሳስበዋል፡፡

ለእርድም ሆነ ለሌሎች አገልግሎቶች የቁም እንስስሳት በተለይም የበሬ ሰንጋዎች ከተለያዩ ወረዳዎች ወደ ተለያዩ አከባቢዎች የሚንቀሳቀሱበት ሁኔታዎች ስላሉ ፣ ላልተወሰነ ጊዜ የቁም የእንስሳት ከቦታ ቦታ ከማዘዋወር ህብረተሰቡ እንዲታቀብም መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

ዘገባው :- የቦንጋ ከተማ አስተዳደር የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ነው፡፡
7.8K views17:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-14 13:12:31
በአርቲስት ማዲንጎ አፈወርቅ መኖሪያ ቤት አርቲስት ጎሳዬ ተስፋዬ እንደባህላችን የማስተዛዘኛ እራት ኘሮግራም አካሄደ በርካታ አርቲስቶችና የኪነ -ጥበብ ባለሙያዎች ተገኝተው ሃዘንተኞቹን በማፅናናት ከጎናቸዉ መሆናቸዉ ያሳዮ ሲሆን በእለቱ የእግዚሐብሔር ቃል ትምህርት እንዲሁም አርቲስት ጎሣዬ ተስፋዬ ወንድማችን በአካል ቢለየንም በመንፈስ አብሮን ነዉ ሀዘን ማብዛት አያስፈልግም ማዲን የሚያስጠሩ ኘሮግራሞችንና ቋሚ ሐዉልት እናቆምለታል ከሱ ሞት እኛ ብዙ ልንማርና ልንዋደድ ይገባል። በቀጣይ በአራራይ እድር በየጊዜ እየተገናኘን መረዳዳት ይኖርብናል በማለት ተናግሯል።
8.7K views10:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-08 16:52:43
ሰበር ዜና
በትናንትናው ዕለት ከገረሴ ዙርያ ወረዳ 12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና ለመፈተን አርባምንጭ ጫጮ ካምፓስ የመጣች ተማሪ በሰላም ተገላገለች::
ተማሪ መድኃኒት መርጊያ የገረሴ ዙርያ ወረዳ የደንብሌ ኦቶራ 2ኛ ደረጃ የማህበራዊ ሳይንስ የማታ ተማሪ የነበረች የሰባት ወር ዕርጉዝ ስትሆን በሰላም መንትያ ልጆችን ተገላግላለች፡፡
በአሁኑ ሰዓት ህፃናት በማሞቂያ ክፍል በጥሩ ጤንነት ላይ ይገኛሉ፡፡
6.4K views13:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-08 15:57:24 "የኦሮሚያ ክልል ትምህርት ቢሮ ቀድሞ ባልተዘጋጀበት ስራ እያስጨነቀን ነው!"
የትምህርት ቤቶች ርዕሰ መስተዳደሮች
#FastMereja
በኦሮሚያ ክልል በዘንድሮ የትምህርት ዘመን የመጀመሪያ ደረጃ ተማሪዎችን ምገባ አስጀምራለሁ ብሎ ማቀዱ ጥሩ ስራ ቢሆንም ቀድመው መሟላት የሚገባቸው ስራዎች ሊሰሩ ይገባ ነበር ሲሉ በክልሉ የሚገኙ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ርዕሰ መስተዳደሮች ቅሬታቸውን ለፋስት መረጃ ገለፁ።

እንደ ርዕሰ መስተዳደሮቹ ገለፃ ለምግብ ማብሰያ፣ የመመገቢያ እና ለመጠጫ የሚሆኑ እቃዎች በሌሉበት እና በጀት ሳይመደብ በድንገት ተነስተው ፕሮግራሙን ማስጀመሩ አግባብ አይደለም በአሁኑ ሰዓት እነዚህን እቃዎች ከእድሮች ላይ በመከራየት እንዲሁም ወጪዎችን ከነዋሪው እና ከባለሃብቶች ማሰባሰብ ጊዜ የሚጠይቅ ስራ ነው በድንገት ተነስቶ እንዚህን ስራዎች መስራት እጅግ አስቸጋሪ ሆኖብናል ብለዋል።

የምግብ ማብሰያ እና መመገቢያ እቃዎችን ቀድሞ ቢገዙ እና የምግብነት የሚሆኑ እህሎችን ለመግዛት የሚያስፈልገውን ገንዘብ ቀድሞ ማሰባሰብ ቢቻል ስራው የተሳለጠ ይሆናል አሁን ትምህርት በተጀመረበት ወቅት ማቴሪያል እና ገንዘብ መሰብሰብ ተገቢ አይደለም።
6.7K views12:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-07 18:43:17
ጅማ ዞን ከሲግሞ ወረዳ የ12ኛ ክፍል ተፈታኝ ተማሪዎችን ጭኖ ወደ ጅማ ዩኒቨርሲቲ ስጓዝ የነበረ አውቶብስ አደጋ ደርሶበታል ነገር ግን ተማሪዎች ምንም ጉዳት ሳይደርስባቸው መትረፋቸውንና የተማሪዎች ወላጆችም እንዲረጋጉ የሲግሞ ወረዳ የመንግስት ኮሚኒኬሽን ገልፃዋል።
2.2K views15:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ