Get Mystery Box with random crypto!

FastMereja.com

የቴሌግራም ቻናል አርማ fastmereja — FastMereja.com F
የቴሌግራም ቻናል አርማ fastmereja — FastMereja.com
የሰርጥ አድራሻ: @fastmereja
ምድቦች: ዜና , ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 36.80K
የሰርጥ መግለጫ

FastMereja.net

Ratings & Reviews

2.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 21

2021-09-03 11:39:52 ባጋጠመን ቴክኒክ ችግር ለበርካታ ጊዜያት ቆሞ የነበረው የቴሌግራም ቻናላችን ከዛሬ ጀምሮ መረጃ ማቅረብ ይጀምራል።
6.2K views08:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-01-07 19:24:45 የደም መጣጩ ህውሀት አባላት በቁጥጥር ስር ዋሉ ። እርምጃም ተወሰደባቸው ።

የመከላከያ ሀይል ሰምሪት መምሪያ ኃላፊ ብ/ጄኔራል ተስፋዬ አያሌው እንዳረጋገጡት ፣ አቶ ተክወይኒ አሰፋ ፣ ዶክተር ሰለሞን ኪዳኔ ፣ አቶ ገ/መድህን ተወልደ ፣ አቶ ወ/ጊዮርጊስ ደስታ ፤ አምባሳደር አባዲ ዘሞ ፣ ወ/ሮ ቅዱሳን ነጋ ፣ አቶ ቴድሮስ ሃጎስ ፣ ወ/ሮ ምህረት ተክላይ ፣ አቶ አብርሃም አደም መሃመድ በቁጥጥር ስር ውለዋል ።

አቶ ሴኮ ቱሬ ጌታቸው ፣ አቶ ዘርአይ አስገዶም ፣ አቶ አበበ ገ/መድህን ፣ አቶ ዳንኤል አሰፋ ደግሞ እርምጃ የተወሰደባቸው ናቸው ።

ምንጭ መከላከያ

@FastMereja
55.1K viewsedited  16:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2020-12-18 09:45:21 የሕወሓት ጁንታ አመራሮች የሚገኙበትን ለጠቆመ 10 ሚልዮን ብር ሽልማት ማዘጋጁትን የመከላከያ ሠራዊት አስታወቀ

የመከላከያ ሠራዊት መረጃ ዋና መምሪያ ኃላፊ ሌተናል ጄነራል አስራት ዴኔሮ ዛሬ ረፋድ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ የጁንታው አመራሮችን በአጭር ጊዜ በቁጥጥር ስር ለማዋል የሚደረገውን ጥረት ለማገዝ ሽልማቱ መዘጋጀቱን አስታውቀዋል።

በዚህም የመከላከያ ሠራዊት የህወሓት ጁንታ አመራሮች ያሉበትን ቦታ ለጠቆመ የ10 ሚሊዮን ብር ሽልማት እንደሚሰጥ አመልክተዋል።

የሕወሓት ጁንታ አመራሮች የሚገኙነትን የሚያውቅ ማንኛውም ግለሰብ በአካባቢው ለሚያገኘው የመከላከያ ሠራዊት አባል በአካል በመቅረብ አልያም በመከላከያ ወራዊት የስልክ ቁጥሮች መጠቆም እንደሚቻል ተገልጿል።
Via: EBC

-------------
@fastmereja
16.6K views06:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2020-12-16 12:03:36
አንጋፋው የጥበብ ባለሙያ ተባባሪ ፕሮፌሰር ተስፋዬ ገሰሰ በ84 አመት እድሜአቸው ዛሬ ታህሳስ 7 ቀን 2013 ከዚህ አለም በሞት ተለይተዋል።

@fastmereja
40.9K viewsedited  09:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2020-12-10 17:29:34 አዲስዓለም ባሌማ (ዶ/ር) ፍርድቤት ቀረቡ

የሕወሓት የጥፋ ቡድን ከፍተኛ አመራር የነበሩት አዲስዓለም ባሌማ (ዶ/ር) በፀረ-ሰላም ቡድን ተደራጅተው በመስራት ተጠርጥረው ፍርድቤት ቀረቡ።

ተጠርጣሪው አምባሳደር በነበሩበትም ዘመን ኢትዮጵያ ከውጭ ሀገራት ጋር ያላትን መልካም ግንኙነት ለማበላሸት እና ለማስቆም ተፅዕኖ ሲፈጥሩና ሲሰሩ እንደነበር መርማሪ ፖሊስ ለችሎቱ አስረድቷል።

በተጨማሪም የመንግስት መረጃና ምስጥሮችን አሳልፈው ሲሰጡ እንደነበር መርማሪ ፖሊስ ለችሎቱ አብራርቷል።

ከኦነግ ሸኔ ከፍተኛ አመራሮች ጋርም መረጃ ሲለዋወጡ እና የመንግስትን ምስጢር አሳልፈው በመስጠት ለተፈፀሙ ወንጀሎች በጋራ ሲሰሩ እንደነበር አስረድቷል ሲል ኤፍቢሲ ዘግቧል።

በህግ ሲፈለጉ ከነበሩት የጁንታው ሕወሓት ቡድን አባላት መካከል አንዱ የሆኑት አዲስዓለም ባሌማ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የመረጃ ፍሰት ቃል አቀባይ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ከትላንት በስቲያ መግለፃቸው ይታወሳል።
Via:ኢቲቪ

@fastmereja
14.1K views14:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2020-12-10 16:53:02 የአምባሳደር ስዩም መስፍን ባለቤትና ወንድ ልጁ ፍርድ ቤት ቀረቡ

በትናንትናው ዕለት በቁጥጥር ስር የዋሉት የአምባሳደር ስዩም መስፍን የትዳር አጋር ወ/ሮ ፈለገህይወት በርሔና ልጃቸው አጋዚ ስዩም ዛሬ ፍርድ ቤት ቀርበዋል፡፡

ሁለቱ ተጠርጣሪዎች ከመስከረም 30 በኋላ መንግስት የለም በማለት ከህወሓት ፀረ ሰላም ቡድኖችና ከኦነግ ሸኔ አመራሮች ተልዕኮ በመቀበል በአዲስ አበባ ሁከትና አመፅ ለመቀስቀስ ገንዘብ በማሰራጨትና ወጣቶችን በመመልመል ተጠርጥረው መያዛቸውን መርማሪ ፖሊስ አስታውቋል፡፡

ተጠርጣሪዎቹ በስዩም መስፍን ስም በተመዘገበ የመንግስት ቤቶች እና በፀሀይ ሪል እስቴት ውስጥ በሚገኝ መኖሪያ ቤት ላይ በፍርድ ቤት ትዕዛዝ ምርመራ ተደርጓል ሲል መርማሪ ፖሊስ አስረድቷል፡፡

በተለይም በመንግስት ቤቶች በተደረገው ፍተሻ ሁለት ሽጉጦች ተገኝተዋል፡፡ እንዲሁም በፀሀይ ሪል እስቴት በሚገኝ መኖሪያ በተደረገ ብርበራ ኤሌክትሮኒክስ መሳሪያዎችን ማግኘቱን መርማሪ ፖሊስ ለችሎቱ አስረድቷል፡፡

ፖሊስ ለተጨማሪ ምርመራ ተጨማሪ ጊዜ ያስፈልገኛል ሲልም አስረድቷል፡፡

የአቶ ስዩም መስፍን ባለቤት ወ/ሮ ፈለገህይወት አንደኛው ሽጉጥ ባላቤቴ ራሱን የሚጠብቅበት ሲሆን ሌላኛው ደግሞ ከውጭ ሀገር በስጦታ የተሰጠው ነው ስትል አብራርታለች፡፡

ተጠርጣሪዎቹ ዋስትና እንዲሰጣቸው የጠየቁም ሲሆን፤ ወይዘሮዋ ልጄ አጋዚ የአዕምሮ ህመምተኛ ስለሆነ መድሀት እንዲገባልን ስትል ጠይቃለች፡፡

ጉዳዩን የተከታተለው ችሎት ለተጨማሪ ምርመራ 8 ተጨማሪ ቀናት በመፍቀድ፣ ለፖሊስ በታሰሩበት ቦታ አስፈላጊው መድሀኒት እንዲገባላቸው አዟል፡፡
Via: ፋና

@fastmereja
10.9K viewsedited  13:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2020-12-02 16:05:02 የተሳሳተ መረጃ ማስተካከያ
==============
ህዳር 23 ቀን 2013 ዓ.ም
አዲስ አበባ
የኢፌዲሪ ፈዴራል ፖሊስ ኮሚሽን የሀገር ክህደት ወንጀል የፈፀሙ በርካታ የከሀዲው ጁንታ ህዋሀት ቡድን አባላት የሆኑ ጀኔራል መኮንኖች ፣ ከፍተኛና የመስመር መኮንኖች ላይ የመያዣ ትዕዛዝ ማውጣቱንና እነዚህን ህገወጦች በቁጥጥር ስር ለማዋል ክትትል መጀመሩን ለህዝብ ይፋ ማደረጉ ይታወቃል።
ኮሚሽኑ የክትትል ስራውን አጠናክሮ የቀጠለ ቢሆንም በኢትዮ FM የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ወንጀል መከላከል ዘርፍ ሃላፊ የሆኑት ም/ኮሚሽነር ጀነራል መላኩ ፋንታ ገልፀዋል በሚል 38 የህዋሀት አመራሮች በቁጥጥር ስር ውለዋል ስል ያስተላለፈው መረጃ ሐሰትና በም/ኮሚሽነር ጀነራሉ ያልተላለፈ መሆኑን እየጠቆምን ተያዙ በሚል ሃላፊው የገለፁት መከላከያ ውስጥ የግንኙነት መስመር ያቋረጡና ከዚህ ድርጊት ጋር በተያያዘ የተጠረጠሩ ሜጀር ጀነራል ገብረመድህን ፍቃዱን (ወዲ ነጮን) ጨምሮ 38 ግለሰቦች ፍርድ ቤት ስለመቅረባቸው መሆኑን እየጠቆምን ከጁንታው ቡድን አባላት ከአሁን በፊት ከተገለጹት በስተቀር እስከአሁን ተጨማሪ አዲስ የተያዙ አለመኖራቸው ታውቆ ሌሎች ሚዲያዎች ይህንን የተዛባ መረጃ ለህብረተሰቡ ከማሰራጨት እንዲቆጠቡ በጥብቅ እናሳስባለን ።
የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን

@fastmereja
13.3K viewsedited  13:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2020-12-02 11:09:29 የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን በቦንብ ፍንዳታው ምንም የደረሰ ጉዳት አለመኖሩን ገለፀ፡፡
***
ህዳር 23 ቀን 2013 ዓ/ም ከጠዋቱ 1፡30 ሰዓት ላይ በቦሌ ክ/ከተማ ልዩ ቦታው ጎርጎርዮስ አደባባይ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በሚገኝ አንድ የቆሻሻ መጣያ ገንዳ ውስጥ ተጥሎ የተገኘ ቦምብ ከአካባቢው ሰዎች በደረሰው ጥቆማ የፈንጅ አምካኝ ባለሙያዎች ወደ ቦታው በማቅናት ለማምከን ባደረገው ሙከራ ምክንያቱ ባልታወቀ ሁኔታ ሊፈነዳ ችሏል፤
በዚህም አንድ ግለሰብ የቦንቡ ፍንጣሪ በቅርብ ርቀት ከሚሰራበት ጋራዥ ቅጥር ግቢ በስራ ላይ ሳለ በፍንጣሪው ቀላል ጉዳት የደረሰበት ሲሆን ተጎጂው የህክምና ርዳታ በማግኘት ወደ ቤቱ መመለሱን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን እየገለፀ ፖሊስ ከጉዳዩ ጋር ግንኙነት ባላቸው ግለሰቦችና አጠቃላይ የምርመራውን ውጤት እንደደረሰን የምናሳውቅ ሲሆን በተመሳሳይ በዚሁ ክ/ከተማ ወረዳ 6 ልዩ ቦታው ጉርድ ሾላ ቅዱስ ያሬድ ሆስፒታል ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ለፖሊስ በደረሰ መረጃ መሰረት ባለሙያዎች ቦታው ድረስ በመገኘት ቦንቡን የማምከን ስራ ሰርተዋል፡፡
በነብስ ውጪ ግቢ ጣር ላይ የሚገኘው የጁንታው ተላላኪዎች በከተማችን አዲስ አበባ በንፁሃን ላይ ከባድ ጉዳት ለማድረስ የሚደርጉትን መንፈራገጥ ለማምከን የሚቻለው ህብረተሰቡ ከፖሊስ ጋር የሚኖረውን የመረጃ ልውውጥ በማጠናከርና አካባቢውን በንቃት በመጠበቅ መሆኑን ኮሚሽኑ ማስገንዘብ ይወዳል፡፡

አዲስ አበባ ፖሊስ
-------------
@fastmereja
12.7K views08:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2020-12-01 20:01:31 ወ/ሮ ኬሪያ ኢብራሂም ለመንግስት እጅ ሰጡ

ከተፈላጊ የህወሓት ጁንታ አባላት አንዷ የሆኑት ወይዘሮ ኬሪያ ኢብራሂም ለመንግስት እጅ ሰጡ።

ወይዘሮ ኬሪያ ኢብራሂም የህውሓት ከፍተኛ አመራርና በመንግስት ከፍተኛ ሃላፊነት የነበራቸው እንዲሁም በፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤነት አገልግለዋል። ፋና

@fastmereja
21.2K viewsedited  17:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2020-11-30 20:41:02 የአሮጌው ብር የመገበያያ ጊዜ ከነገ ጀምሮ ያበቃል

የአሮጌው ብር ኖት የመገበያያ ጊዜ ከነገ ህዳር 22 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ ያበቃል።

የአሮጌው ብር ኖት ቅያሬ ታህሳስ 6 ቀን 2013 ዓ.ም እንደሚጠናቀቅ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ከዚህ ቀደም መግለጹ ይታወሳል።

ባንኩ ከዚህ ቀደም ህዳር 10 ቀን 2013 ዓ.ም በሰጠው መግለጫ እንዳስታወቀው፤ ከነገ ጀምሮ በአሮጌው የብር ኖት መገበያየት አይቻልም።

ከመስከረም 6 ቀን 2013 ዓ.ም አሮጌ የብር ኖቶች በአዲስ የብር ኖቶች እየተቀየሩ መሆኑ ይታወቃል።

የብር ኖት ቅያሬው በሶስት ወራት ውስጥ እንደሚጠናቀቅ መወሰኑም አይዘነጋም።
-------------
@fastmereja
10.9K views17:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ