Get Mystery Box with random crypto!

FastMereja.com

የቴሌግራም ቻናል አርማ fastmereja — FastMereja.com F
የቴሌግራም ቻናል አርማ fastmereja — FastMereja.com
የሰርጥ አድራሻ: @fastmereja
ምድቦች: ዜና , ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 36.80K
የሰርጥ መግለጫ

FastMereja.net

Ratings & Reviews

2.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 20

2022-10-07 18:42:57
በቡኢ ከተማ ላይ በአርቲስት ጸጋዬ ሲሜ የተገነባው "ኦሴባሳ ጥላ" ሆቴል መስከረም 28/2015 ዓ.ም ተመርቆ ለአገልግሎት ክፍት እንደሚሆን ተነገረ።

ሆቴሉ ለሥራ አጥ ዜጎች የሥራ ዕድል በመፍጠር ረገድም ትልቅ ፋይዳ እንደሚኖረው እና ከ30 በላይ ሠራተኞች እንደሚኖሩት ተመላክቷል። የመኝታ ፣የመዝናኛ እና የሆቴል አገልግሎት እንደሚሰጥ ተገልጿል።
2.2K views15:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-07 18:42:26
ዛሬ የሳይንስ ሙዚየሙን ገብተን ጎበኘነው!! በጣም ደስ የሚል ስራ መሆኑን ከጎብኚዎች አስተያየት ተቀብለናል!! በርካቶች እየተሰራ ባለው ነገር ተደስቷል። ወላጆች ልጆቻቸውን ይዘው እየጎበኙ ነው። ምስሉ ላይ የምትመለከቷት "ሰላም" ትባላለች በሀገራችን አርተፊሻል ኢንተለጀንስ (AI) የተሰራች አስጎብኚ ናት። ከቀናት በኋላ የሙዚየሙ አስጎብኚ ሰላም ናት። በአራት ቋንቋ የማስጎብኘት ስራዋን ትጀምራለች። ሰላምን እና ሌሎች የAI ቴክኖሎጂዎችን ለመጎብኘት በተለይ ልጆቻችሁን ይዛችሁ የሳይንስ ሙዚየም ሂዱ ልጆች በፍፁም መቅረት የለባቸውም ሙዚየሙ የቀጣዩ ትውልጅ ሀብት ነው።

እንዳትጉላሉ መግቢያው በውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር በኩል ነው። ወንዶች ቦርሳ ተሸክሞ መግባት ክልክል ነው! እራሳችሁን የሚገልፅ መታወቂያ ያዙ!!
#FastMereja
2.2K views15:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-07 12:37:23 ብሔራዊ ባንክ ሕገ ወጥ የገንዘብ ዝውውርን ለሚጠቁሙ ወሮታ ሊከፍል ነው

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በአገሪቱ የሚካሄዱ ሕገወጥ የገንዘብ ዝውውሮችን ለመቆጣጠር በጥቆማ ለሚተባበሩ ግለሰቦች የተለያየ መጠን ያለው ወሮታ እንደሚከፍል አስታወቀ።

የብሔራዊ ባንክ ገዢ ዶክተር ይናገር ደሴ ዛሬ አዲስ አበባ ውስጥ በሰጡት መግለጫ መንግሥት ሕገወጥ የገንዘብ ዝውውሮችን ለመቆጣጠር የተለያዩ እርምጃዎችን እየወሰደ መሆኑን ተናግረዋል።

በአገሪቱ እየተባባሰ ያለውን የዋጋ ንረት እና የኑሮ ውድነት ለማረጋጋት በሕገወጥ መንገድ የሚካሄዱ የተለያዩ የገንዘብ ዝውውሮችን ለመቆጣጠር ያስችላሉ ያላቸውን እርምጃዎችን አሳውቋል።

በዚህም ምክንያት በባንክ ከተፈቀደው በላይ የገንዘብ መጠን ይዘው የሚገኙ ግለሰቦችን ለጠቆሙ ከተያዘው ገንዘብ 15 በመቶ፣ የውጭ አገር ገንዘብ ዝውውር ለሚጠቁሙ 15 በመቶ፣ ሕገወጥ ሐዋላን ለሚጠቁሙ 25 ሺህ ብር ወሮታ ብሔራዊ ባንክ እንደሚከፍል ገዢው አሳውቀዋል።

ከዚህ በተጨማሪም የወርቅ ኮንትሮባንድ ለሚጠቁሙ 15 በመቶ የወርቁን ዋጋ፣ የሐሰተኛ የገንዘብ ኖት ህትመትን ለሚጠቁሙ ከ20 ሺህ እስከ 200 ሺህ ብር የሚደርስ ወሮታ እንደሚከፈልም ተገልጿል።

ባለፉት ሁለት ዓመታት በአገሪቱ ውስጥ ያለው የውጭ ምንዛሪ ዋጋ እየጨመረ ሲሆን፣ በአሁኑ ወቅት ያለው የምንዛሪ ዋጋ ከዚህ በፊት ከነበሩት ሁሉ ከፍተኛው መሆኑን ነጋዴዎች ይናገራሉ።

በዚህም በይፋዊው የባንኮች ግብይት የዶላር የምንዛሪ ዋጋ የአንድ የአሜሪካ ዶላር ዋጋ 52 ብር አካባቢ ሲሆን፣ በጥቁር ገበያ በእጥፍ እንደሚመነዘር ነጋዴዎች ገልጸዋል።

ዶክተር ይናገር ደሴ እንዳሉት ሕገወጥ የገንዘብ ዝውውርን ለመቆጣጠር መንግሥት እስካሁን በወሰዳቸው እርምጃዎች 391 ሰዎች በሕገወጥ መንገድ ገንዘብ ሲያዘዋውሩ እና የሐዋላ ሥራ ሲያከናውኑ በቁጥጥር ስር ውለው ጉዳያቸው በሕግ ተይዟል።

ቢቢሲ አማርኛ
4.6K views09:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-07 09:38:12
#ፈገግ ስትሉ ዋሉ
ዛሬ መስከረም 27 በአለም አቀፍ ደረጃ የፈገግታ ቀን ነው! የተከፉ ሰዎች ተደስተው ፈገግ ሲሉ ደስ ይላሉ፣ ያዘኑ ፊቶች በፈገግታ ሲበሩ ደስ ይላሉ፣ ፈገግ ያሉ ሰዎች ፈገግታን በሌሎች ያጋባሉ…
#worldsmileday
#FastMereja
5.5K views06:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-17 22:49:26
ልዩ መረጃ

የሱማሌ ክልል ፕሬዘዳንት አቶ ሙስጠፋ ላይ ዛሬ ዲኬ በተባለው አካባቢ የገጠመው ያልተጠበቀ ጥቃት ተርፏል።
12.9K viewsedited  19:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-08 20:09:12 መረጃዎችን በቴሌግራም ቻናል ማቅረብ ልንጀምር ነው።
20.5K views17:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-21 00:06:35
እያነጋገረ ያለው ቪዲዮ
ይህ ቪዲዮ የተቀረፀው በጉጂ ዞን ሲሆን በቪዲዮ ላይ እየቀረፀ ያለው የኦነግ ሸኔ አባል ሲሆን ንግግሮቹም በጥቅሉ ሲተረጎሙ እኛ ነዋሪውን አንነካም ግቡና ቤት ተቀመጡ፣ የፖለቲካ እስረኞችን እያስፈታን ነው፣ እኛ የምንፈልገው ሚሊሻን ነው ሲሉ ይደመጣል፣ ቪዲዮ ከተለቀቀ ቆየት እንዳለም ተነግሯል።
@FastMereja
70.2K views21:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-17 19:39:04
የት ይሆን ይህ ደግሞ?
112.1K views16:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-09-03 12:00:48 #የዓለማየሁ ዓለም
ከማዕረግ ጌታቸው (ይነገር ጌታቸው)
============

አሜሪካ ገብተው የሆሊውድ ፊልም ተዋናይ መሆን የፈለጉት ጓደደኛሞች አዲስ አበባን ተሰናብተው ምጽዋ ደርሰዋል፡፡ የያኔዎቹ ተስፈኞች ምጽዋ ገብተው ሳይጐበኟት ሊሰናበቷት አልፈለጉም፡፡ ያረፉበትን ቤት ለቀው ማምሻውን በቀይ ባህር ነፋሻማ አየር ታጅበው ቶሪኖ የምሽት ክበብ ገቡ፡፡ ቤቱ በሰዎች ተሞልቷል፡፡ የመርከባቸውን መልህቅ ጥለው አዳራቸውን በምሽት ቤቱ ያደረጉ የውጭ ሐገር ሰዎች እዚህም እዛም ከሙዚቃው ጋር ይወዛወዛሉ ፡፡ ሆሊውድን ሊቀላቀሉ ለሸገር ጀርባ የሰጡት ወጣቶችም ለባህር ዳርቻዋ ከተማ አዲስ አይመስሉም ፡፡ በመጣው የውጭ ሙዚቃ ሁሉ አብረው ይደንሳሉ፡፡

የኤልቪስ ፕሪስሊ ሙዚቃ ከፍ ብሎ እየተደመጠ ነው፡፡ የዳንስ ሰገነቱ ላይ ያለው ታዳጊ የብዙዎችን ቀልብ ስቧል :: ዳንሱም ግጥሙንም እኩል ያስኬደዋል ::ይህ የገረማቸው የምሽት ክበቧ ታዳሚዎች በዚህ ሰው ተገርመው ሲመለከቱት ቢቆዩም ግብፃዊያኑ ግን አይተውት ዝም ሊሉ አልፈለጉም፡፡ ከሙዚቃው በኋላ ጠርተው አናገሩት፡፡ የምጽዋ ልጅ አለመሆኑን ነገራቸው :: ሆሊውድ ውስጥ የፊልም ተዋናይ ለመሆን ፈልጐ ከአዲስ አበባ ጠፍቶ መምጣቱን ገለፀላቸው፡፡

ግብፃዊያኑ መርከበኞች የሱን ምኞት የራሳቸው አደረጉት ፡፡ከጓደኛህ ጋር ሎሳንጀለስ ድረስ እንወስድሀለን አሉት ፡፡ ሩቅ የመሰለው ምኞት ከንጋቱ ወገግታ ጋር አብሮ ሊፈካ ተቃረበ :: በቀጣይ ቀን ከግብፃዊያኑ ካፒቴኖች ጋር የሚገናኝበትን ሰዓት ውስኖ ከስደት ወዳጁ ጋር ወደ ክፍሉ ተመለሰ ::

የዓለማየሁ እሸቴን ህልም የምትፈታው ዕቃ ጫኟ መርከብ“ሳሂካ” ትባላለች :: የጉዞ ሰዓቷ ደርሷል :: ካፒቴኗ ባልደርቦቹን አሁንም አሁንም ይጠይቃል :: ፀጉረ ሉጫ የጠይም መለሎ ወጣት ተሳፈረ ?ይላቸውል :: ምላሻቸው አልምጣም የሚል ነው ::“ሳሂካ” መልህቋን አንስታ የአሜሪካ ጉዞዋን አንድ አለች፡፡ እነዚያ ሆሊውድን ናፍቀው ምጽዋ የደረሱ ወጣቶች ግን በፖሊስ እጅ ነበሩ ፡፡

ነገሩን ለማጣራት ሲሞክሩ ዓለማየሁን የሚያውቅ ዘመድ ወደ አሜሪካ ከማያውቀው ሰው ጋር ሊጓዝ መሆኑን ሰምቶ ለፖሊስ አመልክቶ መሆኑ ተነገራቸው ፡፡ ብዙ አልቆዩም :: የልጅነት አምሮታቸውን እርም ብለው ወደ አዲስ አበባ ተመለሱ ::

1934 ዓ.ም ሰኔ 10 ቀን ብርሀንና ሰላም ማተሚያ ቤት አካባቢየተወለደው ዓለማየሁ እሸቴ ገና በልጅነት ዘመኑ እናት እና አባቱ ፍች በመፈፀማቸው ያደገው አባቱ ቤት ነው ፡፡ ለዚሀ ደግሞ ምክንያቱ አባት ልጃቸውን በወይዘሮ በላይነሽ ዮሴፍ እጅ እንዲያድግ አለመፈለጋቸው ነበር ፡፡ በ1940ዎች መባቻ እንዳብዛኛው የዘመኑ ሕፃናት የአብነት ትምህርትን አሀዱ ብሎ የጀመረው ዓለማየሁ ከጥቂት ጊዜ በኋላ አባቱ አቶ እሸቴ አንዳርጌ ዘመናዊ ትምህርት እንዲከታተል በመፈለጋቸው የፈረንሳይኛ ትምህርት የሚሰጥበት ቦታ ተመዘገበ፡፡

ነገር ግን በዚህ ትምህርት ቤት የቆየው ለወራት ብቻ ነበር፡፡ በወቅቱ ፈረንሳይኛ ከማወቅ ይልቅ አረብኛ መማር የተሻለ ነው የሚል ምክርን የሰሙት አባቱ አቶ እሸቴ አንዳርጌ ከአሊያንስ ኢትዮ ፈራንስ አስወጥተው ዑመር ስመተር ትምህርት ቤት አስገቡት ፡፡

የኢትዮጵያዊው ኤልቪስ የማይደበዝዝ ትዝታ አንዱ መገኛም ዑመር ስማትር ትምህርት ቤት ነው ::ትምህርት ቤት ውሎ ወደ ቤቱ ሲመለስ ቤታቸው በሰዎች ተጨናንቆ ይመለከታል፡፡ የያኔው ብላቴና ነገሩ ባይገባውም እንደ ሁልጊዜው ሁሉ በቤቱ የተገኙትን እንግዶች ሰላምታ እየሰጠ አለፈ፡:

ከእነዚህ መኃል ግን አንደኛዋ ሴት በአፍታ ሰላምታ የምትለየው አልሆነችም :: ዓይኖቿ እምባ አዝለው ደጋግማ አቀፈችው ::እንግዶቹ ዓለማየሁን እናትህ እኮ ናት በደንብ ሰላም በላት እንጂ አሉት ::ለመጀመሪያ ጊዜ ከእናቱ ጋር ተዋወቀ፡፡ ይህ ትውውቅ ግን ብዙ የዘለቀ አልነበረም፡፡ ወይዘሮ በላይነሽ ተመልሳ ወደ ቤቷ አቀናች፡፡ ብላቴናውም ዳግሞ እናቱን መናፈቅ ጀመረ፡፡

የአንደኛ ደረጃ ትምህርቱን በአብዮት ቅርስ ትምህርት ቤት የተከታተለው ኢትዮጵያዊው ኤልቪስ የስድስተኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተናን የወሰደው በአርበኞች ትምህርት ቤት ነበር፡፡ ይህ ትምህርት ቤት ታዳጊው ከአንድ የትምህርት ምእራፍ ወደ ሌላ ምዕራፍ የተላለፈበት ብቻ ሳይሆን ከያኒው ዓለማየሁ እሸቴ እየመጣ መሆኑንም ያበሰረ ነው ::በ1951 ዓ.ም በትምህርት ቤቱ የወላጆች በዓል ላይ ኢትዮጵያዊው ኤሊቪስና ጓደኞቹ የእንጨት ጊታር ይዘው መሬት ላይ እየተንፈራፈሩ በቴሌቭዥን እንዳዮቸው ሙዚቀኞች የተዘጋጁበትን ዜማ አቀረቡ ፡፡

ዓለማየሁ በአብዮት ቅርጽ የወደቀ እንጨትን ጊታር ባደረጉ እኮዮቹ ታጅቦ መደረክ ላይ ይሰየም እንጅ የእሱ ታዋቂነት ምንጭ ግን ተዋናይነቱ ነበር “ኪንግ ሪቻርድስ ኤንድ ዘ አኖውን ኪንግ” የተባለው በትምህርት ቤት ቆይታው የተወነበት ቴአትርም ዓለማየሁን ብዙ እንዲያስብ አድርጐታል፡፡ ፡፡በዚህ የተነሳም ከትምህርት እየቀረ ዘመነኞቹን ፊልሞች መመልከት አዘውተረ፡፡ .....

(በቅርቡ ለንባብ ከሚበቃው "ጠመንጃና ሙዚቃ-የወርቃማው ዘመን ታዝታዎች "መጽሐፍ የተቀነጨበ )
@FastMereja
8.5K views09:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-09-03 11:45:39 በታላቁ ቤተመንግስት እነማን ተሸለሙ ዝርዝር መረጃ

1. አትሌት ሰለሞን ባረጋ በ10ሺ ሜትር ወርቅ 2.8 ሚሊዮን ብር የሚያወጣ መኪና እና 50 ግራም የወርቅ ኒሻን ተበርክቶለታ ።

2. አትሌት ለሜቻ ግርማ በ3 ሺ ሜትር መሰናክል የብር ሜዳሊያ የ1.5 ሚሊዮን ብር ሽልማት

3 . አትሌት ጉዳፍ ፀጋዬ በ5 ሺህ ሜትር የነሐስ ሜዳሊያ የ1 ሚሊዮን ብር

4. አትሌት ለተሰንበት ግደይ 10 ሺ ሜትር የነሐስ ሜዳሊያ የ1 ሚሊዮን ብር እንዲሁም ፤

5. አትሌት ጌትነት ዋለ በ3000 ሜ.መሰናክል ዲፕሎማ 200 ሺህ ብር

6. አትሌት በሪሁ አረጋዊ በ10 ሺ ሜትር ዲፕሎማ 200 ሺህ ብር

7. አትሌት መቅደስ አበበ 3000 ሜ.መሰናክል ዲፕሎማ 200 ሺህ ብር

8. አትሌት ፍሬወይኒ ኃይሉ በ1500 ሜትር ዲፕሎማ 200 ሺህ ብር

9. አትሌት ሮዛ ደረጄ በማራቶን ዲፕሎማ 200 ሺህ ብር

10 . አትሌት እጅጋየሁ ታዬ በ5 ሺ ሜትር ዲፕሎማ 150 ሺህ ብር

11. አትሌት ሰንበሬ ተፈሪ በ5 ሺ ሜትር ዲፕሎማ 150 ሺህ ብር

12. አትሌት ዮሚፍ ቀጄልቻ በ10 ሺ ሜትር ዲፕሎማ 150 ሺህ ብር

13. አትሌት ሀብታም አለሙ በ800 ሜትር ዲፕሎማ 150 ሺህ ብር

14. አትሌት ዘርፌ ወንድማገኝ 3000ሜ.መሰናክል ዲፕሎማ 150 ሺህ ብር

15. አትሌት ሰለሞን ቱፋ በወርልድ ቴኳንዶ በ58 ኪሎ ግራም ዲፕሎማ 150 ሺህ ብር

ለአሠልጣኞች

1. ነሐስ ላስገኘ ም/አሰልጣኝ ንጋቱ ወርቁ 70 ሺህ ብር
2.ነሐስ ላስገኘ ም/አሰልጣኝ ኢሳ ሼቦ 70 ሺህ ብር
3. ነሐስ ላስገኘ ዋና አሰልጣኝ ህሉፍ ይህደጎ 100 ሺህ ብር

4. ብር ሜዳሊያ ላስገኘ ም/አሰልጣኝ ኢብራሂም ዳኜ 100 ሺህ ብር

5.ነሐስ ላስገኘ ዋና አሰልጣኝ ሀይሌ እያሱ 100 ሺህ ብር

6. ብር ሜዳሊያ ዋና አሰልጣኝ ተሾመ ከበደ 200 ሺህ ብር

7. ወርቅ ላስገኘ ም/አሰልጣኝ ኮ/ር ቶሌራ ዲንቃ 200 ሺህ ብር

8. ወርቅ ላስገኘ ዋና አሰልጣኝ ሁሴን ሼቦ 300 ሺህ ብር ሽልማት ተበርክቷል ።

ለተሳታፊ አትሌቶች ለእያንዳንዳቸው የ50 ሺህ ብር ሽልማት ተበርክቷል

በቶኪዮ ኦሎምፒክ በእግር ኳስ ዳኝነት የተሳተፈው ኢንተርናሽናል ዳኛ ባምላክ ተሰማ ልዩ ተሸላሚ በመሆን 100 ሺህ ብር ተበርክቶለታል ።
@fastmereja
7.6K viewsedited  08:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ