Get Mystery Box with random crypto!

FastMereja.com

የቴሌግራም ቻናል አርማ fastmereja — FastMereja.com F
የቴሌግራም ቻናል አርማ fastmereja — FastMereja.com
የሰርጥ አድራሻ: @fastmereja
ምድቦች: ዜና , ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 36.80K
የሰርጥ መግለጫ

FastMereja.net

Ratings & Reviews

2.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 18

2023-04-11 13:06:33
የአባይ ሚዲያ ጋዜጠኞች እና ሰራተኞች ደሞዝ አልተከፈለንም አሉ!

ለበርካታ አመታት አባይ ሚዲያ በሚል የዩቲዩብ ስያሜ ፖለቲካዊ ይዘት ያላቸውን ዘገባዎችን እና ትንታኔዎችን ለተመልካቾች ሲያደረስ የነበረው አባይ ሚዲያ ካለፉት ሁለት አመት ጀምሮ በቴሌቪዥን ቻናል በመምጣት በይበልጥ በመዝናኛ ፕሮግራሞች ላይ እያተኮረ ያለው ሚዲያው አሁን ላይ ለሠራተኞቹ ከ ሶስት እስከ አራት ወር ደሞዝ መክፈል እንዳልቻለ አንዳንድ የጣቢያው ሠራተኞች ለፋስት መረጃ አቤቱታቸውን አሰምተዋል። ፋስት መረጃ በጉዳዩ ላይ የሚዲያው ኃላፊዎችን በስልክ አነጋግረን ነበር "በአካል ቢሮ ካልመጣችሁ በስልክ ማብራሪያ አንሰጥም" የሚል ምላሽ ሰጥተውናል።

@fastmereja
5.6K views10:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-11 12:24:37
መስከረም አበራ “ለኢ-መደበኛ አደረጃጀቶች ወታደራዊ ስልጠና እና የተኩስ ልምምድ ስትሰጥ ነበር” ሲል ፖሊስ ወነጀለ

ከትላንት በስቲያ እሁድ በፖሊስ ቁጥጥር ስር የዋለችው የመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዋ መስከረም አበራ፤ “ሁከት እና ብጥብጥ በማነሳሳት ወንጀል” ተጠርጥራ በፍርድ ቤት 13 የምርመራ ቀናት ተፈቀደባት። መስከረምን ፍርድ ቤት ያቀረባት የፌደራል ፖሊስ፤ “ተጠርጣሪዋ ለኢ-መደበኛ አደረጃጀቶች ወታደራዊ ስልጠና እና የተኩስ ልምምድ ስትሰጥ ነበር” ሲል ለፍርድ ቤቱ አስረድቷል።

ፖሊስ ዛሬ ማክሰኞ ሚያዚያ 3፤ 2015፤ በመስከረም ላይ ውንጀላውን ያቀረበው፤ ለፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ የጊዜ ቀጠሮ ችሎት ነው። በችሎቱ መስከረምን ወክለው የቀረቡት ጠበቃዋ አቶ ሄኖክ አክሊሉ በበኩላቸው ፍርድ ቤቱ የደንበኛቸውን የዋስትና መብት እንዲጠብቅ ጠይቀዋል። መረጃው የኢትዮጵያ ኢንሳይደር ነው።

@fastmereja
5.6K views09:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-11 11:50:26
#ሀረሪ

ታዋቂው የሀረሪ ሙዚቃ አርቲስት ሙክታር አህመድ ከዚህ አለም በሞት ተለየ።

ታዋቂው የሀረሪ ሙዚቃ አርቲስት ሙኽታር አህመድ ጋሪ ከዚህ አለም በሞት ተለይቷል። አርቲስት ሙክታር የሀረሪ ሙዚቃዎችን በማዘመን እና አንድ ደረጃ ከፍ በማድረግ የራሱን አሻራ ያሳረፈ በአድማጩ ከፍተኛ አድናቆትን ያተረፈ ባለ ልዩ ተሰጥኦ አርቲስት ነው መሆኑን ከሀረሪ ብዙሀን መገናኛ ኤጀንሲ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
ለአርቲስት ሙኽታር አህመድ ቤተሰብ ወዳጅ ዘመዶቹና አድናቂዎቹ መፅናናትን እንመኛለን!!

@fastmereja
5.5K views08:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-11 10:58:32
#አዲስአበባ

አንድ ግለሰብ ወድቆ ያገኙትን ከ7 ሺ ብር በላይ ለፖሊስ አስረከቡ፣ ገንዘቡ የኔ ነው የሚል ሰው መጥቶ ይውሰድ ተብሏል።

ሚያዚያ 2 ቀን 2015 ዓ/ም አቶ በሽር አህመዲን የተባሉ ግለሰብ ወድቆ ያገኙትን 7 ሺህ 700 ብር የራሴ ያልሆነና ያልለፋሁበት ገንዘብ ነው በማለት ለአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ማስረከባቸውን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡

ግለሰቡ የፈፀሙትን ተግባር ፖሊስ አድንቆ ገንዘቡ የእኔነው የሚል ግለሰብ አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ በመቅረብ መረከብ እንደሚችል አስታውቋል፡፡ ማህበረሰቡ ወድቆ ያገኘውን እና ባለቤቱ ያልተገኘ ንብረትን በአካባቢው ለሚገኝ ፖሊስ ጣቢያ የማስረከብ ልምድ ሊያዳብር እንደሚገባ የአዲስ አበባ ፖሊስ መልዕክቱን አስተላልፏል፡፡

@fastmereja
5.8K views07:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-10 23:28:25 #ባህርዳር

በባሕር ዳር ከተማ በቦምብ ፍንዳታ ሦስት ሰዎች ተገደሉ

በባህር ዳር ከተማ፣ በተለምዶ ዓባይ ማዶ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ፣ ትላንት ምሽት፣ በአንድ የምግብ እና መጠጥ መሸጫ የንግድ ተቋም ላይ በደረሰ የቦምብ ፍንዳታ የሦስት ሰዎች ሕይወት ማለፉንና ወደ 10 የሚደርሱ ሰዎች መቁሰላቸውን፣ በአካባቢው የሚገኘው የዐዲስ ዓለም የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ተወካይ ሜዲካል ዳይሬክተር አስታወቁ፡፡ ስለ ጥቃቱ ተጨማሪ መረጃ ከፖሊስ ለማግኘት ያደረግነው ጥረት ለጊዜው አልተሳካም ሲል ቪኦኤ ነው የዘገበው።

@fastmereja
6.6K views20:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-10 22:18:32 #AddisAbaba በአዲስ አበባ መብራት ላይ ስፖኪዮ ስርቆት እየተባባሰ ነው!

በአዲስ አበባ ከተማ የትራፊክ መብራት ይዞቿው የቆሙ ተሽከርካሪዎች ላይ የስኪዮ ስርቆት እየተባባሰ መምጣቱ አሳሳቢ ሆኗል። በዛሬው እለት ብቻ በቦሌ መንገድ ጃፓን ተብሎ በሚጠራው መስቀለኛ መንገድ ላይ መብራት ይዟቸው የቆሙ መኪኖች ውስጥ ሁለቱ የስኪዮ ስርቆት አጋጥሟቸው ተመልክተናል።

ነገሩ የሆነው እንዲህ ነው መብራት ይዟችሁ በምትቆሙበት ወቅት በስፍራው ያሉ የጎዳና ተዳዳሪዎች ለልመና ወደ መኪናው ጠጋ ይላሉ በሁለቱም አቅጣጫ ይለምናሉ እርሶ ትኩረቶ በአንዱ አቅጫ ሲሆን በሌላኛው አቅጣጫ ያለው ልጅ ተዓምር በሚባል ፍጥነት ስፖኪዮውን ነቅሎ ከአካባቢው በሩጫ ያመልጣሉ። ዛሬ የሆነውም ይህ ነው ትኩረት ሊሰጠው ይገባል።

@fastmereja
7.5K views19:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-10 20:40:34
ከፌስቡክ በተጨማሪ በቴሌግራም መጥተናል እነሆ ለቴሌግራም ተከታታዮች የፋስት መረጃ ትክክለኛው ቻናል @fastmereja የሚል username ሲሆን ከታች ባለው ሊንክ መቀላቀል ይችላሉ።
https://t.me/fastmereja
https://t.me/fastmereja
7.9K views17:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-01 15:48:04 "የጦርነቱ ዓላማ ወልቃይትን ማስመለስ እና ህወሓትን ማጥፋት አልነበረም" አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን

ከጅምሩ የጦርነቱ ዓላማ ወልቃይትን ማስመለስና ሕወሓትን ማጥፋት አልነበረም ያሉት ሬድዋን (አምባሳደር)፣ የጦርነቱ ዋና ዓላማ የነበረው የአገሪቱን ሉዓላዊነት ማስከበርና ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓት ማስፈን የሚሉት እንደሆኑ አስረድተዋል፡፡ ‹‹ሕወሓትን እንደ ፖለቲካ ኃይል የማጥፋት ዓላማ ያለው ሰው ይኖራል፣ ነገር ግን የፌዴራል መንግሥቱ ዓላማ አይደለም፤›› ብለዋል፡፡

‹‹ወልቃይት በአማራና በትግራይ ክልሎች መካከል ያለ ፀብ ነው፣ በሁለት ክልሎች መካከል ያለው ፀብ ደግሞ የሚፈታው የፌዴሬሽን ምክር ቤት በሚመራው ሥርዓት፤›› ነው ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል፡፡

‹‹የፌዴራል መንግሥት አቋም ተራ በተራ ጡንቻ እየተፈታተን አንዳችን ሌላችንን ማንበርከክ ይቁም፤›› የሚል መሆኑን የገለጹት የብሔራዊ ደኅንነት አማካሪው፣ ‹‹ወልቃይትን ከዚህ ቀደም ሕወሓት ጡንቻ ስለነበረው በጉልበት ወስዷል፣ አሁን ደግሞ ሕወሓት ሸብረክ ሲል ጡንቻ ያለው አካል ይውሰድ ካልን መጪው ትውልድ 20 ዓመት ጠብቆ ድንገት ጡንቻ ካገኘ ይወስደዋል፡፡ ስለዚህ ዘላቂው መፍትሔ ጡንቻ ሳይሆን ሕግና ሥርዓት ነው፤›› በማለት ገልጸዋል፡፡

‹‹አንድ ሰው ትግራይን ሲወድ ካርታውን ብቻ ሳይሆን ሕዝቡን ነው፣ ነገር ግን ካርታውን ወዶ ሕዝቡን መጥላት አይቻልም፤›› ሲሉም አክለዋል፡፡ ‹‹ቲፎዞና ደም መርጠን መለቃቀስ ይቅር፣ የትም ቦታ ሰው ሲሞት ሁላችንም ሊሰማን ይገባል፤›› ብለዋል፡፡

ምንጭ ሪፖርተር

@FastMereja
5.2K viewsedited  12:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-16 13:03:25
አልማዟ አልማዝ አያና አሸነፈች
#FastMereja
ዛሬ በተካሄደው የአምስተርዳም ማራቶን አትሌት አልማዝ አያና በመጀመሪያ የማራቶን ውድድሯ አሸንፏለች፣ ገንዘቤ ዲባባ 2ኛ፣ ፀሀይ ገመቹ 3ኛ
6.9K views10:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ