Get Mystery Box with random crypto!

'የጦርነቱ ዓላማ ወልቃይትን ማስመለስ እና ህወሓትን ማጥፋት አልነበረም' አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን | FastMereja.com

"የጦርነቱ ዓላማ ወልቃይትን ማስመለስ እና ህወሓትን ማጥፋት አልነበረም" አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን

ከጅምሩ የጦርነቱ ዓላማ ወልቃይትን ማስመለስና ሕወሓትን ማጥፋት አልነበረም ያሉት ሬድዋን (አምባሳደር)፣ የጦርነቱ ዋና ዓላማ የነበረው የአገሪቱን ሉዓላዊነት ማስከበርና ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓት ማስፈን የሚሉት እንደሆኑ አስረድተዋል፡፡ ‹‹ሕወሓትን እንደ ፖለቲካ ኃይል የማጥፋት ዓላማ ያለው ሰው ይኖራል፣ ነገር ግን የፌዴራል መንግሥቱ ዓላማ አይደለም፤›› ብለዋል፡፡

‹‹ወልቃይት በአማራና በትግራይ ክልሎች መካከል ያለ ፀብ ነው፣ በሁለት ክልሎች መካከል ያለው ፀብ ደግሞ የሚፈታው የፌዴሬሽን ምክር ቤት በሚመራው ሥርዓት፤›› ነው ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል፡፡

‹‹የፌዴራል መንግሥት አቋም ተራ በተራ ጡንቻ እየተፈታተን አንዳችን ሌላችንን ማንበርከክ ይቁም፤›› የሚል መሆኑን የገለጹት የብሔራዊ ደኅንነት አማካሪው፣ ‹‹ወልቃይትን ከዚህ ቀደም ሕወሓት ጡንቻ ስለነበረው በጉልበት ወስዷል፣ አሁን ደግሞ ሕወሓት ሸብረክ ሲል ጡንቻ ያለው አካል ይውሰድ ካልን መጪው ትውልድ 20 ዓመት ጠብቆ ድንገት ጡንቻ ካገኘ ይወስደዋል፡፡ ስለዚህ ዘላቂው መፍትሔ ጡንቻ ሳይሆን ሕግና ሥርዓት ነው፤›› በማለት ገልጸዋል፡፡

‹‹አንድ ሰው ትግራይን ሲወድ ካርታውን ብቻ ሳይሆን ሕዝቡን ነው፣ ነገር ግን ካርታውን ወዶ ሕዝቡን መጥላት አይቻልም፤›› ሲሉም አክለዋል፡፡ ‹‹ቲፎዞና ደም መርጠን መለቃቀስ ይቅር፣ የትም ቦታ ሰው ሲሞት ሁላችንም ሊሰማን ይገባል፤›› ብለዋል፡፡

ምንጭ ሪፖርተር

@FastMereja