Get Mystery Box with random crypto!

የአባ ሰንጋ በሽታ መከሰቱን ከዘገብን በኋላ አንድ ተከታተያችን (Vit mamila) የሚከተለውን ስ | FastMereja.com

የአባ ሰንጋ በሽታ መከሰቱን ከዘገብን በኋላ አንድ ተከታተያችን (Vit mamila) የሚከተለውን ስለ በሽታው ጠቃሚ መረጃ ለፋስት መረጃ ልኮልናል።
#FastMereja
አባ ሰንጋ (Anthrax)
አስከፊው በሽታ

የበሽታው መንስኤ
አንትራክስ (Anthrax) በሽታው ባሲለስ አንትራሲስ (Bacillus anthracis) በሚባል በሽታ አምጪ ተህዋሲያን የሚከሰት ሲሆን ይህ ተህዋሲያን በአፈር ውስጥ ስፖር(Spore) በመፍጠር ለአመታት የመደበቅ አቅም ያለው ነው። በሽታው ብዙ አይነት አጥቢ እንስሳትን ያጠቃል። በሽታውን በሁለተኛው አለም ጦርነት ባይሎጂካል መሳሪያ (Biological Weapon) ይጠቀሙበት እንደነበር ይገለፃል። በሀገራችን ኢትዮጵያ ይህ በሽታ ረጅም አመታትን አስቆጥሯል።

የበሽታው ምልክቶች

ይህ በሽታ በጥቂት ሰአታቶች ውስጥ ለሞት የሚዳርግ እና ተላላፊ የሆነ በሽታ ነው። ሶስት የበሽታው ፍጥነት በደረጃ ሲቀመጡ እጅግ ፈጣን (peracute) ፈጣን(acute) እና መካከለኛ ፈጣን (sub acute) ናቸው። የበሽታው ዋና እና የተለየ ምልክት በአፍ እና በአፍንጫ ያልረጋ ደም መፍሰስ ሲሆን በተጨማሪም እንስሳቶቹ ማመንዠግ ያቆማሉ፣ ከፍተኛ ትኩሳት ይኖራል፣ ከፍተኛ የመተንፈስ ችግርም የሚያጋጥማቸው ይሆናል። ክሮኒክ አንትራክስ (chronic anthrax) በብዛት የሚታየው በአሳማዎች ሲሆን ጉሮሮ አካባቢ እብጠት ይኖራቸዋል በተጨማሪም ከአፋቸው አረፋ የሚደፍቁም ይሆናል።

የበሽታው ስርጭት
በሀገረ ዛምቢያ በዚህ በሽታ በትንሹ 30 ሰዎች በ1992 እ.አ.አ ሞተዋል። በሀገረ አልጀሪያ ደግሞ 59 ሰዎች አንድ የቤተሰብ አባላት መጠቃታቸው ተዘግቧል። በተጨማሪም አንትራክስን (Anthrax) ሀያል የአለም ሀገራት እንደ ባይሎጂካል መሳሪያ (Biological Weapons) የሚጠቀሙበት ሲሆን በ1979 እ.አ.አ በራሺያ እና በአሜሪካ ድንበር መሀል ሰቨርድሎስኪ (sverdlovsk) በምትባል ግዛት ላይ በነበረው አለመግባባት በአጠቃላይ በሺዎች መሞታቸውን የአሜሪካ መንግስት ይፋ አድርጓል። በወቅቱ ለግል እርባታ ድርጅቶች በሚዘጋጅ መኖ (bone meal) በማድረግ አልያም በአየር ወለድ በሽታ በእፅዋቶች አማካኝነት ይሆናል የሚል መላ ምት አስቀምጠዋል።

የበሽታው ህክምና
በፍጥነት ህክምና የሚያገኙ እንስሳት የመትረፍ እድል አላቸው። በመጀሪያ በደም ስር የሚሰጥ ቤንዛይሊንፔንሲልን (benzylpenicillin) ሲሆን አስከትለን ኢንትራመስኩላር (Intramuscular) አሞክሲሊን (Amoxicillin) የምንሰጥ ይሆናል።

የበሽታው መከላከያ ዘዴ
በአንትራክስ የሞተ እንስሳ በውስጡ በሽታ አምጪ ተህዋሲያኑ ባሲለስ አንትራሲስ በብዛት የሚራባ ሲሆን ስጋውን ለመጠቀም መሞከር እና ማረድ አካባቢውን(ውሀውን፣ ሳሩን፣ አፈሩን) በዚህ በሽታ እንዲበከል ማድረግ ነው። በኋላም እንስሳቶች ለግጦሽ በሚሰማሩበት ወቅት ይተላለፍባቸዋል። በተለይ ከባድ ዝናብ ሲጥል አፈሩ ለመደበኛ አየር ስለሚጋለጥ በሽታው ሊባባስ ይችላል።

በዋናነት በበሽታው የተጠቁትን 2ሜትር ቆፍሮ አቃጥሎ መቅበር፣ የአካባቢ ንፅህና መጠበቅ፣ ዲስኢንፌክታንትን መጠቀም ፣ በሚኖረው ንኪኪ ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግ በበሽታው ላልተጠቁት ክትባት መስጠት እጅግ አስፈላጊ ነው።