Get Mystery Box with random crypto!

FastMereja.com

የቴሌግራም ቻናል አርማ fastmereja — FastMereja.com F
የቴሌግራም ቻናል አርማ fastmereja — FastMereja.com
የሰርጥ አድራሻ: @fastmereja
ምድቦች: ዜና , ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 36.80K
የሰርጥ መግለጫ

FastMereja.net

Ratings & Reviews

2.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 13

2023-04-26 11:32:58
በምስራቅ ትግራይ የተማሪዎች ምዝገባ እንደቀጠለ ነው
#FastMereja
የምስራቅ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ መሃሪ አባይ እንደገለፁት በክልሉ በሚገኙ ቀሪ 415 ትምህርት ቤቶች ምዝገባ መጀመሩን ተናግረዋል። በዚህም መሰረት ከ240,000 በላይ ተማሪዎች ወደ ትምህርት ቤት ይመለሳሉ ተብሎ ይጠበቃል ሲል ድምፂ ወያኔ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

@fastmereja
4.6K views08:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-25 22:55:17 በታንዛኒያ ዛንዚባር ደሴት በኢትዮጵያ መንግስት እና በኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት መካከል የሰላም ውይይት ዛሬ ተጀመረ።
#FastMereja
በታንዛኒያ የሰላም ድርድር ዛሬ ማለዳ መጀመሩን በስፍራው የነበሩ ምንጮች ለቢቢሲ ተናግረዋል። በውይይቱ ላይ የሁለቱም ወገኖች ተወካዮች ስድስት ሰዎች እየተሳተፉ መሆናቸውን ምንጮች ለቢቢሲ ተናግረዋል።

በመንግስት በኩል ወደ ታንዛኒያ የተጓዘው የልዑካን ቡድን አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን እና ዶ/ር ጌዲዮን ጢሞቲዮስ እንደሚገኙበት ቢቢሲ ዘግበዋል።

በኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት በኩል አንጋፋው የታሪክ ምሁር ፕሮፌሰር መሃመድ ሃሰን እና የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት ዋና አዛዥ አማካሪ ሚስተር ጂሬኛ ጉዳታ እና አቶ አብዲ ጠሃ እና ሌሎችም መገኘታቸውን ፋስት መረጃ ከቢቢሲ ያገኘው መረጃ ያመለክታል።

@FastMereja
5.8K views19:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-25 16:32:32
የጋምቤላ፣ የምዕራብ ወለጋ፣ የቄለም ወለጋ፣ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የአሶሳ ፣ የደቡብ ሱዳን አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ አቡነ ሩፋኤል አሶሳ ገቡ።

ሊቀ ጳጳሱ አሶሳ ህዳሴ ኤርፖርት ሲደርሱ የአሶሳ ሀገረ ስብከት ሰራተኞችና ሰንበት ተማሪዎች አቀባበል አድርገዋል ።

ሊቀ ፓፓሱ እንደ ሀገርም ሆነ እንደ ክልል አሁን ያለውን ስላም ለማስቀጠል ቤተክርስቲያን የበኩሏን ድርሻ ማበርከት በሚቻልበት ሁኔታ ከባለድርሻ አካላት ጋር እንደሚመክሩ ይጠበቃል ሲል ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ሚዲያ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

@fastmereja
6.1K views13:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-25 16:21:12
ከኦሮሚያ ክልል አባ ገዳዎች፣ የሃይማኖት መሪዎች፣ የሀገር ሽማግሌዎች በትግራይ በጦርነቱ የደረሰውን ጉዳት ለመታዘብ መቐለ ገብተዋል።

@fastmereja
5.4K views13:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-25 16:13:39
በሚኒባስ ተሽከርካሪ ውስጥ ባዶ ፍራሽ አንጥፈው የኩላሊት ታማሚ የተኛ በማስመሰል በህክምና ሰበብ ገንዘብ ሲሰበስቡ የተገኙ 4 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ፡፡

ግለሰቦቹ የማታለል ድርጊቱን ሲፈፅሙ የተገኙት በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 1 ሲኒማራስ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ነው፡፡ የአዲስ አበባ ፖሊስ እንዳስታወቀው አራት ተጠርጣሪዎች የሰሌዳ ቁጥር ኮድ 3- 43018 አ.አ በሆነ ሚኒባስ ተሽከርካሪ ውስጥ ባዶ ፍራሽ በማንጠፍ ፣ በፍራሹ ላይ የኩላሊት በሽታ ታማሚ የተኛ በማስመሰል እና የግለሰብ ፎቶ በባነር አሳትመው በመስቀል በስፒከር እየቀሰቀሱ በህክምና ወጪ ሰበብ ከህብረተሰቡ ገንዘብ ሲሰበስቡ የፖሊስ አባላት በጥርጣሬ ባከናወኑት የማረጋገጥ ስራ በቁጥጥር ስር ሊውሉ ችለዋል፡፡

መደጋገፍና መረዳዳት ከኢትዮጵያውያን መገለጫዎቻችን አንዱ ቢሆንም በአቋራጭ ለመበልፀግ ህብረተሰቡን በማታለል እንዲህ አይነት ህገ ወጥ ተግባር የሚፈፅሙ ግለሰቦች መኖራቸውን በመገንዘብ እውነተኛ ድጋፍ የሚፈልጉ ሰዎችን ማገዝ እንደተጠበቀ ሆኖ በህክምና ሰነዶች እና በሌሎች ሁኔታዎች የማረጋገጥ ስራ በመስራት አታላዮችን ማጋለጥ እንደሚገባ የአዲስ አበባ ፖሊስ መልዕክቱን አስተላልፏል፡፡

@fastmereja
4.9K views13:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-22 14:45:45 በኦሮሚያ ከግንቦት 1 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ የነዳጅ ግብይት በኤሌክትሮኒክስ ሥርዓት ብቻ ይከናወናል።
#FastMereja
ኔትወርክ በሌለበት አካባቢም ሲ ቢ ኢ ብር በመጠቀም ይቻላል ተብሏል።

በኦሮሚያ ክልል ከግንቦት 1 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ የነዳጅ ግብይት በኤሌክትሮኒክስ ሥርዓት ብቻ እንደሚከናወን የክልሉ ንግድ ቢሮ አስታወቀ፡፡

በኤሌክትሮኒክስ የሚከነወነው የነዳጅ ግዥና ሽያጭ የተሳለጠ እንዲሆንም የሚመለከታቸው አካላት ከወዲሁ ዝግጁ እንዲሆኑ ሲል ቢሮው አሳስቧል፡፡

በሌላ በኩል እንደ አቢሲያ ካርድ ኩፖን እና ሌሎች የግብይት መፈጸሚያ ዘዴዎች ሲጠቀሙ የነበሩ ተቋማት እስከያዝነው በጀት ዓመት መጨረሻ ድረስ ብቻ መጠቀም እንደሚችሉ ነው የተገለጸው፡፡

ኔትወርክ በሌለበት አካባቢም ሲ ቢ ኢ ብር በመጠቀም የነዳጅ ግብይት መፈጸም እንዲቻል ከቴሌ ጋር ስምምነት ላይ ተደርሶ መተግበሪያው መበልጸጉን የኦሮሚያ ክልል ኮሙኒኬሽን ቢሮ መረጃ ያመላክታል፡፡

@fastmereja
2.0K views11:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-22 11:44:45
የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ቴዎድሮስ አድሃኖም ገብረእየሱስ በድርጅቱ የስልጣን ዘመን ባሳዩት የአመራር ብቃት የክብር ዶክትሬት ተሰጥቷቸዋል።

የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም በሥነ ሥርዓቱ ላይ እንደተናገሩት ፕሬዝዳንት ኔልሰን ማንዴላ ለሰው ልጆች እኩልነት፣ ፍትህ እና እርቅ በሰሩት ስራ የክብር ዶክትሬት በተሰጣቸው ቦታ ሽልማታቸውን ማግኘታቸው እንዳስደሰታቸው ተናግረዋል።

@fastmereja
3.1K views08:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-22 11:43:27
የቀድሞው የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጀኔራል ሰዓረ መኮንን በአዲስ አበባ ቦሌ ሩዋንዳ ድልድይ የቆመላቸው ሐውልት እየተመረቀ ነው፡፡

@fastmereja
2.9K views08:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-21 16:11:06 የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ይቅርታ ጠየቀ!!
#FastMereja

የዒድ ሰላት ለመስገድ ከቤታችሁ ወጥታችሁ ላመለጣችሁ የከተማችንና አካባቢው ሙስሊሞች በሙሉ!!

ዛሬ በነበረው የኢድ ሰላት ፕሮግራም ላይ ለመታደም ጥሪያችንን አክብራችሁ በአንድነት አምራችሁና ደምቃችሁ ግዙፉ የከተማችን ውበት ሆናችሁ በመዋላችሁ የተሰማንን ታላቅ ደስታ እንገልፃለን።

የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት በድጋሚ እንኳን ለ1444 ዓ.ሂ የኢድ አልፊጥር በዓል በሰላም አደረሳችሁ እያልን በዛሬው እለት የተሰገደው የኢድ ሰላት በሰላም፣በደስታ መጠናቀቁ ቢያስደስትም የዒድ ሰላት ከዚህ ቀደም ሲሰገድበት ከነበረው ሰአት ቀድሞ በመሰገዱ የዒድ ሰላት ላመለጣችሁ የከተማችን ሙስሊሞች ይቅርታ እንጠይቃለን።

በትናንትናው እለት ከፌደራል መጅሊስ ጋር በጋራ በሰጠነው መግለጫ ሸሪአውን በጠበቀ መልኩ በእለቱ ንግግሮች እንደማይኖሩና በማለዳ ሰግደን እንደምንበተን ለህዝባችን ገልፀን ቢሆንም በእለቱ የተገኙት ሚድያዎች በአብዛኛው በሚባል መልኩ ትኩረት ሰጥተው ባለማስተላለፈቸው እና ከሚዲያዎቹ በተጨማሪ ሌሎች አማራጮችን በሰፊው ባለመጠቀማችን ችግሩ እንዲፈጠር ምክንያት እንደነበሩ ተረድተናል።

በተጨማሪም ከዚህ ቀደም ሲሰገድበት የነበረውን ሂደትን ለማሻሻል በሚል መልካም እሳቤ በተፈጠረ ክፍተት ሰላት ላመለጣችሁ ሁሉ ታላቅ ይቅርታ እየጠየቅን በቀጣይ የሚስተካከል መሆኑን ህዝባችን እንዲገነዘብ እያልን፣
በበጎና ገንቢ በሆነ መልኩ አስተያየታችሁን ለለገሳችሁን የከተማችን ነዋሪዎች ምስጋና እያቀረብን በዓሉ የሰላም የደስታ፣የመተዛዘን፣የመረዳዳት እንዲሆን መልካም ምኞታችንን ለመግለፅ እንወዳለን።

በድጋሚ ዒድ ሙባረክ!!!ኩሉ ዓም ወአንቱም ቢኸይር።

@fastmereja
3.0K views13:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-21 11:29:40 በባህዳር ከተማ የዒድ መስገጃ 20ሺህ ካሬ ሜትር ቦታ ተሰጠ!!
#FastMereja

የባሕር ዳር ከተማ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ድረስ ሳህሉ (ዶ/ር) በባሕር ዳር ዓለም አቀፍ ስታዲዮም በተከበረው የዒድ አልፈጥር በዓል አከባበር ሥነሥርዓት ላይ ተገኝተው ለመላው እስልምና ሃይማኖት ተከታዮች የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት አስተላልፈዋል፡፡

የሃይማኖት አስተምህሮው በሚያዝዘው መሰረት ዒድ አልፈጥርንም የተቸገሩትን በመርዳትና በመተጋገዝ የምታከብሩበት ይሁን ያሉት ከንቲባው ፤በዓሉም የፍቅርና የሰላም እንዲሆንም መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል፡፡

ችግሮችንን በመነጋገር የመፍታት ባሕልን በማዳበር ፣በመተባበርና በመከባበር ካለፉት ጉዳዮችም ልምድ በመውሰድ ለሀገር አብሮነት አንድነትና ሰላም የበኩላችሁን እንድትወጡ አሳስባለሁ ብለዋል፡፡

ከንቲባው በበዓሉ ሥነ ሥርዓት ላይ እንዳሉት በተደጋጋሚ ሲጠየቅ የነበረው የመስገጃ ቦታ ጥያቄ ምላሽ አግኝቷል፡፡

ከተማ አሥተዳደሩ ከክልሉ መንግሥት ጋር በመነጋገር በተወሰነው መሰረት "ጥያቄያችሁ ምላሽ አግኝቷል ፤ለዒድ አልፈጥር በዓል መስገጃ መንግሥት 20ሺህ ካሬ ሜትር ቦታ ፈቅዶላችኋል" ብለዋል።

ከንቲባው በቀጣይ ዓመት የዒድ በዓልን ለመስገጃ በተፈቀደው በአዲሱ ቦታ የምታከብሩ ይኾናል ብለዋል ሲል አሚኮ ነው የዘገበው።

@FastMereja
4.1K views08:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ