Get Mystery Box with random crypto!

በባህዳር ከተማ የዒድ መስገጃ 20ሺህ ካሬ ሜትር ቦታ ተሰጠ!! #FastMereja የባሕር ዳር | FastMereja.com

በባህዳር ከተማ የዒድ መስገጃ 20ሺህ ካሬ ሜትር ቦታ ተሰጠ!!
#FastMereja

የባሕር ዳር ከተማ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ድረስ ሳህሉ (ዶ/ር) በባሕር ዳር ዓለም አቀፍ ስታዲዮም በተከበረው የዒድ አልፈጥር በዓል አከባበር ሥነሥርዓት ላይ ተገኝተው ለመላው እስልምና ሃይማኖት ተከታዮች የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት አስተላልፈዋል፡፡

የሃይማኖት አስተምህሮው በሚያዝዘው መሰረት ዒድ አልፈጥርንም የተቸገሩትን በመርዳትና በመተጋገዝ የምታከብሩበት ይሁን ያሉት ከንቲባው ፤በዓሉም የፍቅርና የሰላም እንዲሆንም መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል፡፡

ችግሮችንን በመነጋገር የመፍታት ባሕልን በማዳበር ፣በመተባበርና በመከባበር ካለፉት ጉዳዮችም ልምድ በመውሰድ ለሀገር አብሮነት አንድነትና ሰላም የበኩላችሁን እንድትወጡ አሳስባለሁ ብለዋል፡፡

ከንቲባው በበዓሉ ሥነ ሥርዓት ላይ እንዳሉት በተደጋጋሚ ሲጠየቅ የነበረው የመስገጃ ቦታ ጥያቄ ምላሽ አግኝቷል፡፡

ከተማ አሥተዳደሩ ከክልሉ መንግሥት ጋር በመነጋገር በተወሰነው መሰረት "ጥያቄያችሁ ምላሽ አግኝቷል ፤ለዒድ አልፈጥር በዓል መስገጃ መንግሥት 20ሺህ ካሬ ሜትር ቦታ ፈቅዶላችኋል" ብለዋል።

ከንቲባው በቀጣይ ዓመት የዒድ በዓልን ለመስገጃ በተፈቀደው በአዲሱ ቦታ የምታከብሩ ይኾናል ብለዋል ሲል አሚኮ ነው የዘገበው።

@FastMereja