Get Mystery Box with random crypto!

1.5 ቢሊዮን ብር የፈጀው ስቴይ ኢዚ ፕላስ ሆቴል ስራ ሊጀምር ነው #FastMereja በባለፉት | FastMereja.com

1.5 ቢሊዮን ብር የፈጀው ስቴይ ኢዚ ፕላስ ሆቴል ስራ ሊጀምር ነው
#FastMereja

በባለፉት ስምንት አመታት በግንባታ ላይ የነበረው ስቴይ ኢዚ ፕላስ ሆቴል እነሆ ግንባታውን አጠናቆ ከሁለት ሳምንት በኋላ ሙሉ ለሙሉ አገልግሎት መስጠት እንደሚጀምር የሆቴሉ ስራ አስኪያጅ አቶ አሚር ሰዒድ ዛሬ በሆቴሉ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ተናግሯል።

ስቴይ ኢዚ ፕላስ ሆቴል (Stay Easy plus) በጥንዶቹ በአቶ ዳግማዊ መኮንን እና በወ/ሮ ህይወት አየለ ባለቤትነት የተገነባ ሲሆን፣ ሆቴሉ ለግንባታ ከአንድ ነጥብ አምስት ቢሊዮን ብር በላይ ፈጅቷል። ምድሩን ጨምሮ ዘጠኝ ወለሎች አሉት። ባለ አምሰት ኮከብ ደረጃ ለማግኘት ያመለከተው ሆቴሉ በአጠቃላይ 103 ክፍሎች ያሉት ሲሆን ከ15 እስከ 1,5ዐዐ ሰው ማስተናገድ የሚችሉ ስድስት የስብስባና፣ የሰርግ አዳራሾች እንዲሁም የጥበብና ቲያተሪካል አርት እና ሌሎች ዝግጅቶችን ማቅረብ ለሚፈልጉ ምቹ አዳራሾች አሉት።

ሶስት ባር እና አንድ መመገቢያ አዳራሾች ያለው እራሱን የቻለ የዳቦና የኬክ መጋገሪያ ኪችን ያለው በሰዓት ከ3ዐ,ዐዐዐ ዳቦ በላይ ማምረት የሚችል ማሽን ያሉት ሲሆን ኦፕን ኪችን እንዲሁም ግዙፍ የላውንደሪ አገልግሎት መስጠት የሚችሉ ማሽኖች አሉት፡፡

"ከደቡብ አፍሪካ ከስደት ስንመጣ የመጀመሪያው ባለ 3 ኮኮብ ስቴይ ኢዚ ሆቴል በ22 አካባቢ ገንበተን ስራ የጀመርነው አሁን እሱ አድጎ ነው ትልቁን ስቴይ ኢዚ ፕላስ ሆቴል የገነባው" ያሉት የሆቴሉ ማኔጂንግ ዳይሬክተር ወ/ሮ ህይወት አየለ ናቸው በተጨማሪም በበጎ አድራጎት ለስምነት አመታት ለበዓል ሁለት ሰንጋዎችን በማረድ አቅመ ደካማ ለሆኑ ሰዎች እየለገሰን ነው ብለዋል።

ሆቴሉ በአጠቃላይ ከ250 በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የስራ ዕድል መፍጠር ችሏል። በእንጦጦ እና ሱልልታ የሩጫ ከእንጦጦ ፓርክና ቦታኒክ ጋርደን ልምምድ ለሚያደርጉ አትሌቶች በቅርብ የሚገኝ ደረጃውን የጠበቀ ሆቴል ከመሆኑ ባሻገር መኝታ ክፍል ለያዘ እንግዳ ሙሉ በሙሉ አዲስ አበባን ከአራቱም አቅጣጫ መመልከት የሚያስችል ልዩ እይታ ያለው ሆቴል ነው ተብሏል።

ሆቴሉ የከርሰ ምድር ውሃ ያለው ሲሆን በሰከንድ አምስት ሊትር ውሃ ማመንጨት የሚችል ሲሆን ለማህበረሰቡም ለ24 ሰዓት በነፃ እንዲጠቀሙ ፈቅዷል።

ሆቴሉ በአጠቃላይ የያዘው ስፍራ 2,250 ሜትር ስኵር ሲሆን በ 1,7ዐዐ ሰኵር ላይ ሆቴሉ ተገንብቷል። የኤሌትሪክ መኪና ይዘው ለሚመጡ ደንበኞቹ ኤሌክትሪክ ቻርጅ ማድረጊያ ቦታ ያለው ሲሆን በቅርቡ በሚጠናቀቁት የማስፋፊያ ፕሮጀክቱ ሰፖርት መስሪያ ጂም ፣ሳውና እና ስቲም ባዝ ፣ መዋኛ ገንዳ፣ የዮጋ አዳራሽ በተጨማሪም የባህል ሬስቶራንትና የሙዚቃ አዳራሽ ይኖረዋል፡፡

ከመሀል ከተማ ፒያሳ በመኪና አስር ደቂቃ ብቻ የሚወስድ አዲሱ ገበያ ከፍ ብሎ ቶታል አጠገብ የሚገኝ ሲሆን ፀጥ ያለ እና ነፋሻማ ስፍራ ላይ የሚገኝ ሆቴል ነው።

@fastmereja