Get Mystery Box with random crypto!

በሲኖ ትራክ በሁለት የተለያየ ቦታ የሰው ህይወት አለፈ! #FastMereja በአዲስ አበባ ከተማ | FastMereja.com

በሲኖ ትራክ በሁለት የተለያየ ቦታ የሰው ህይወት አለፈ!
#FastMereja
በአዲስ አበባ ከተማ በተለያየ አካባቢ በደረሱ የትራፊክ አደጋዎች የሁለት ሰዎች ሕይወት ማለፉን የአዲስ አበባ እሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አስታወቀ፡፡

ዛሬ ከቀኑ 5:37 ላይ በአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 5 ሰሜን ሆቴል ፊትፊት “ሲኖ ትራክ” እየተባለ የሚጠራው የደረቅ ጭነት ተሽከርካሪ መንገድ በማቋረጥ ላይ የነበረን የ50 ዓመት ጎልማሳ በመግጨቱ ሕይወቱ ማለፉን የኮሚሽኑ የሕዝብ ግንኙነት ባለሙያ ንጋቱ ማሞ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ተናግረዋል፡፡

እንዲሁም ትናንት ምሽት በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 2 ጣፎ 2ኛ በር አካባቢ መንገድ በማቋረጥ ላይ የነበረ የ44 ዓመት ጎልማሳ እንዲሁም በ “ሲኖ ትራክ” የደረቅ ጭነት ተሽከርካሪ ተገጭቶ ሕይወቱ ማለፉን ፋና ነው የዘገበው።

@fastmereja