Get Mystery Box with random crypto!

ከአርብ መስከረም 25 እስከ ቅዳሜ በዓሉ እስኪጠናቀቅ የሚዘጉ የአዲስ አበባ መንገዶች! #FastMe | FastMereja.com

ከአርብ መስከረም 25 እስከ ቅዳሜ በዓሉ እስኪጠናቀቅ የሚዘጉ የአዲስ አበባ መንገዶች!
#FastMereja
የኢሬቻ ሆራ ፊንፊኔ በዓል ተከብሮ እስከሚጠናቀቅ የትራፊክ መጨናነቅ እንዳይፈጠር የተወሰኑ መንገዶችን ለተሽከርካሪ ዝግ እንደሚሆኑ የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡
***
መስከረም 26 ቀን 2016 ዓ/ም የኢሬቻ ሆራ ፊንፊኔ በዓል በአዲስ አበባ በልዩ ልዩ ዝግጅቶች ይከበራል፡፡

በዓሉ ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ የትራፊክ መጨናነቅ እንዳይከሰት የተወሰኑ መንገዶች ለተሽከርካሪ ዝግ ስለሚሆኑ አሽከርካሪዎች አማራጭ መንገዶች እንዲጠቀሙ አዲስ ፖሊስ ገልፆል፡፡ በመሆኑም ከቀኑ 8:00 ሰዓት ጀምሮ በዓሉ እስከሚጠናቅ
• ከቦሌ አየር መንገድ በሚሊኒዬም አዳራሽ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ወሎ ሰፈር አደባባይ
• ከመገናኛ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ 22 ማዞሪያ
• ከ4ኪሎ በውጭ ጉዳይ ሚ/ር ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ኮንሰን መስቀለኛ ወይም ወዳጅነት ፓርክ
• ከፒያሳ በቸርቸር ጎዳና ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ቴዎድሮስ አደባባይ
• ከጦር ሃይሎች በለገሃር ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ልደታ ከፍተኛ ፍርድ ቤት
• ከጀሞ በትንባሆ ሞኖፖል ወደ ሜክሲኮ የሚወስደው መንገድ አፍሪካ ህብረት አደባባይ
• ከቄራ ወደ ሜክሲኮ አደባባይ የሚሄደው መንገድ ቡልጋርያ ማዞሪያ
• በአዲሱ መንገድ ከቄራ በቂርቆስ ወደ ለገሃር የሚወስደው መንገድ ታቦት ማደሪያ
• ከሳሪስ ፣ በጎተራ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ጎተራ ማሳለጫ
• ከቦሌ ወደ ቅዱስ ዑራኤል ቤተ ክርስቲያን የሚወስደው መንገድ አትላስ ሆቴል አካባቢ
• ከአዋሬ ወደ ካሳንቺዝ የሚወስደው መንገድ ሴቶች አደባባይ
• ከልደታ በጌጃ ሰፈር ፣ ጤና ጥበቃ የሚወስደው መንገድ አብነት ፈረሰኛ ፖሊስ አካባቢ
• ከመርካቶ በጎማ ተራ ወደ አምስተኛ የሚወስደው መንገድ በርበሬ በረንዳ
• ከመርካቶ በራስ ቴአትር ወደ ጎማ ቁጠባ ተክለ ሃይማኖት አደባባይ
ከአርብ መስከረም 25 ቀን 2016 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ጀምሮ ፕሮግራሙ እስከሚጠናቀቅ ድረስ መንገዶቹ ለጊዜው ለተሽከርካሪ ዝግ ይሆናሉ፡፡

በዓሉ በሚከበርበት ዙሪያ እና በአካባቢው በግራና በቀኝ ለረጅም ሆነ ለአጭር ጊዜ ተሽከርካሪ አቁሞ መሄድ ፍፁም የተከለከለ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ ገልጿል፡፡

በመጨረሻም ህብረተሰቡ የፖሊስን አገልግሎት ለማግኘትም ሆነ አጠራጣሪ ነገሮች ሲያጋጥሙት መረጃ ለመስጠት በ991 ወይም 816 ነፃ የስልክ መስመሮችን እና 011-1-26- 43-59 ፣ 011- 5- 52- 63-02/03 ፣ 011-542-40-77፣ 011-5-54-36-81 እንዲሁም በ987 ፣ 991 እና 816 ነፃ የስልክ መስመሮች መጠቀም እንደሚችልና ለፀጥታ ስራው ስኬታማነት ህብረተሰቡ እያደረገ ላለው ቀና ትብብር በመላው የፀጥታ አካላት ስም አዲስ አበባ ፖሊስ ምስጋናውን እያቀረበ በዓሉ የሰላምና የደስታ እንዲሆን መልካም ምኞቱን ገልጿል፡፡

@fastMereja