Get Mystery Box with random crypto!

ልጅ ያሬድ የተባለውን ግለሰብ በህግ ለመጠየቅ የሚያስችል ሥራ እየተሰራ እንደሆነ የኢትዮጵያ ኦርቶዶ | FastMereja.com

ልጅ ያሬድ የተባለውን ግለሰብ በህግ ለመጠየቅ የሚያስችል ሥራ እየተሰራ እንደሆነ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን አስታወቀች
#FastMereja
ባለፉት ቀናት  በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ቅጥር ውስጥ በመግባት ከእምነቷ ውጭ የሆነ መዝሙር የዘመረች ወጣት  የፈጸመችው ተግባር ጥፋት መሆኑን አምና በፈጸመችው ጥፋት  በመጸጸት በቅድስት ቤተ ክርሰቲያን አውደ ምህረት ተገኝታ ይቅርታ መጠየቋን ተከትሎ ልጅ ያሬድ የተባለ ግለሰብ እንኳን የኃይማኖት ሀገር በሆነችው ኢትዮጵያ ቀርቶ እምነት የለሽ በሚባሉት ሀገራት የማይደረግ የድፍረት ስድብና አጋንታዊ የሆነ ጸያፍ ቃላትን በመጠቀም በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ላይ በማህበራዊ ድህረ ገጹ ላይ በተደጋጋሚ  ያስተላለፈውን መልዕክት ተመልክተነዋል።

በዚህ ድፍረት የተሞላበት  ድርጊትም በርካታ ኦርቶዶክሳውያን አዝነዋል፣አልቅሰዋል፣ በድርጊቱ ክፉኛ በመበሳጨትም ከፍትህ አደባባይ ፍርድ  እንደሚጠብቁ  በተለያየ መልኩ እያሳወቁ ናቸው።

ቤተ ክርስቲያን የክርስቶስን መስቀል ሁሌ መሸከም የየዕለት  ተግባሯ ቢሆንም ከሚሊዮን በላይ ተከታይ ያላትንና  ላለፉት ሁለት ሺህ ዘመናት ሀገርን በፍቅርና በስነምግባር ጥላ ሥር ሰብስባ ያኖረች ቤተ ክርስቲያን መሆንዋ እየታወቀ  በእንዲህ አይነት በወረዳና ተሰምቶ በማያውቅ ድፍረት  ቤተክርስቲያንን በመስደብ ሕዝበክርስቲያኑን ለማሳዘን መሞከር እጅግ አደገኛ ተግባር ነው።

ቤተክርስቲያንም ይህን  ጸያፍ ተግባር የፈጸመና  የተሳደበን ግለሰብ በዝምታ ማለፍ  ስለማይገባት  ጉዳዩን በህግ መምርያ በኩል በመከታተል ተገቢውን ሁሉ  የምታደርግ መሆኑን ከወዲሁ እየገለጸች በህግ መምሪያችንና በህግ ባለሙያዎቻችን አማካኝነት አስፈላጊውን ሁሉ እስክታደርግ  ድረስ ምዕመናን ከቅድስት ቤተክርስቲያን የተማሩትን ትዕግስትና ትህትናን መሰረት ባደረገ አግባብ  በፍጹም ክርስቲያናዊ ጨዋነት እንድትጠብቁና በጉዳዩ ዙሪያ ከጸጥታ ከአካላት ጋር በትብብርና በአንድነት  በመጠቆም እንድትተባሩ ቅድስት ኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያናችን ጥሪዋን ታስተላልፋለች።

@fastmereja