Get Mystery Box with random crypto!

በባሕር ዳር እና አካባቢው ገበያዎች አንድ ኩንታል ጤፍ እስከ 10 ሺሕ ብር እየተሸጠ እንደሚገኝ ሸ | FastMereja.com

በባሕር ዳር እና አካባቢው ገበያዎች አንድ ኩንታል ጤፍ እስከ 10 ሺሕ ብር እየተሸጠ እንደሚገኝ ሸማቾች እና ነጋዴዎች ተናገሩ

በባሕር ዳር እና አካባቢው ገበያዎች አንድ ኩንታል ጤፍ እስከ 10 ሺሕ ብር እየተሸጠ እንደሚገኝ ሸማቾችና ነጋዴዎች ተናገሩ። ባለፉት ጥቂት ወራት በጤፍ ላይ የታየው ከፍተኛ የዋጋ ጭማሪ የሸማቾችን አቅም እየተፈታተነ ነው። የማዳበሪያ እጥረት በገበሬዎች ዘንድ የፈጠረው ሥጋት እና የመንግሥት የቁጥጥር ማነስ ለዋጋ ጭማሪው እንደ ገፊ ምክንያት ይቀርባሉ

የምግብ እህል ዋጋ በእጅጉ እየጨመረ በመሄዱ ነዋሪዎች ኑሯቸውን ባግባቡ መምራት መቸገራቸውን ገልጠዋል፣ አንድ ኩንታል ጤፍ ባህር ዳር ላይ እስከ 10ሺህ ብር እየተሸጠ ነው፣ ሸማቾችም ሆኑ ነጋዴች ለምግብ ዋጋ መጨመር ከማዳበሪያ እጥረት ጋር በተያያዘ ነው ይላሉ፣ በቀጣይ ዓመት ምርት ላይኖር ይችላል ከሚል ስጋት አርሶ አደሩ ምርቱን ወደ ገበያ ማውጣት ባለመቻሉ የጤፍ ዋጋ ንሯል ብለዋል፣ አንድ አርሶአደር በበኩላቸው የኢንዱስትሪ ዋጋ መናሩ ለምግብ እህል መወደድ ሌላው ምክንያት እንደሆነ አመልክተዋል፡፡

የባሕር ዳርና አካባቢው ነዋሪዎች ሰሞኑን ለዶይቼ ቬሌ እንዳመለከቱት፣ በስፋት በህብረተሰቡ ዘንድ በስፋት ለምግብነት የሚያገለግለው ጤፍ ባለፉት 3 ወራት ብቻ እጥፍ በሚባል ደረጃ በመጨመሩ ኑሮን በአግባቡ ለመምራት ተቸግረዋል፡፡

ወ/ሮ ላዋይሽ አደመ የባህር ዳር ከተማ ነዋሪ ሲሆኑ በባህር ዳር ከተማ አንዱ በሆነው የጤፍ ገበያ ጤፍ ሲሸምቱ አግኝተናቸው ነበር፣ አንድ ኩንታል ጤፍ ካለፈው ወር በ3000 ብር ጭማሪ እንዳሳየ ነግረውናል፣ ምክንት ያሉትንም አብራርተዋል፡፡

ዘገባው የዶይቼ ቬሌ ነው!!

@fastmereja