Get Mystery Box with random crypto!

ስኳርን በማቅለጥ እና ሌላ በዕድ ነገር በመጨመር ንፁህ ማር በማስመሰል ይሸጥ ይነበረ ግለሰብ በሕግ | FastMereja.com

ስኳርን በማቅለጥ እና ሌላ በዕድ ነገር በመጨመር ንፁህ ማር በማስመሰል ይሸጥ ይነበረ ግለሰብ በሕግ ቁጥጥር ዋለ።

በወልድያ ከተማ አስተዳደር በዕቴጌ ጣይቱ ክፍለ ከተማ በ02 ቀበሌ ልዩ ስሙ ትንፋዝ ተብሎ በሚታወቀው ሰፈር ስኳር ከማር ጋር በማቅለጥ ይሸጥ የነበረ ግለሰብ፤ በህብረተሰቡ በተሰጠ ጥቆማ ትናንት ሰኔ 25 ቀን 2015 ዓ.ም በቁጥጥር መዋሉን የክፍለ-ከተማው ፖሊስ ጽ/ቤት የሥራ ባልደረባ የሆኑት ረዳት ኢንስፔክተር ጌታቸው ይፍሩ አስታቀዋል።

ግለሰቡ ቤተ ተከራይቶ አራት ሰዎችን ቀጥሮ ስኳሩን ከማሩ ጋር በፈላ ውሃ እያቀለጠ በመቀላቀል ላይ ሳለ በቁጥጥር ስር መዋሉን የገለጹት ረዳት እንስፔክተሩ ግለሰቡ ካቀለጠ በኋላ ለካፌ ባለቤቶች ለፈጢራ ምግብ እና ለሌሎችም የምግብ አገልግሎት በንፁህ ማር ስም ከወለድያ እስከ አላማጣና ሌሎች አካባቢዎችም በመዘዋወር ሲሸጥ መኖሩን የእምነት ቃል ሰጥቷል ብለዋል።

ኢንስፔክተር አያይዘውም አሁን ላይ እጅ ከፍንጅ የያዝነው ውሃ፣ ስኳርና ማር ሲሆን፤ የሚያቀልጥበት ቤትም ከወለሉ እስከ ጥራው በቆሻሻ የተሞላ መሆኑን ገልጸው ለጊዜው እኛ በዓይናችን ማየት ያልቻልነው ሌላም የተጨመረ ባዕድ ነገር ካለ ከጤና ተቋማት ጋር በመሆን የምርመራ ሥራው በላቡራቶሪ እንዲደገፍ እያደረግን ነው ብለዋለ።

በመጨረሻም ረ/ኢንስፔክተር ድርጊቱን ፈጻሚዎቹ በሕግ ቁጥጥር ስር ውለው የወንጅል ክስ የመመስረት ሂደት መጀሙሩን ገልጸው፤ ሕብረተሰቡ እንዲህ ዓይነት ድርጌቶችን በቅርበት ለሚገኝ የፖሊስ ተቋም በመጠቆም የራስንም የበርካታ ሕዝብንም ከጤና እክል የመታደግ ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ አሳስበዋል።

ዘገባው የወልድያ ከተማ ኮሙኒኬሽን ነው!!

@fastmereja