Get Mystery Box with random crypto!

በሞተር ብስክሌት፣ በባለ አራት እግርና ባለሶስት እግር ባጃጅ ማሽከርከር ላይ ተጥሎ የነበረው እግ | FastMereja.com

በሞተር ብስክሌት፣ በባለ አራት እግርና ባለሶስት እግር ባጃጅ ማሽከርከር ላይ ተጥሎ የነበረው እግድ ነገ ይነሳል፡፡
#FastMereja
የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ በሞተር ብስክሌተኞች፣ በባለ አራት እግርና ባለሶስት እግር ባጃጅ ተሽከርካሪዎች ላይ ጥሎት የነበረውን ክልከላ ከነገ ማክሰኞ መስከረም 29/2016ዓ.ም ጀምሮ ያነሳ መሆኑን የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ አሳወቀ።

ሆኖም ፍቃዱ የሚመለከታቸው የባጃጅ አሽከርካሪዎች በቢሮው እውቅና ተሰጥቷቸው በማህበር ተደራጅተው መስመርና ታፔላ ያላቸው ሲሆኑ፤ የሞተር ሳይክሎችም በአዋጁ መሰረት ሰሌዳ ወስደው፣ ህጋዊ መንቀሻቀሻ ፍቃድና ጂፒኤስ (GPS) ያስገጠሙትን ብቻ መሆኑን ቢሮው አሳውቋል።

ከትራንስፖርት ቢሮው ህጋዊ እውቅና ውጪ የሚንቀሳቀሱ አሽከርካሪዎች ላይ ቢሮው ጥብቅ እርምጃ የሚወሰድ ገልፇል።

@fastmereja