Get Mystery Box with random crypto!

በትግራይ ክልል 9 ሺህ 514 ተማሪዎች ከነገ ጀምሮ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ይወስዳሉ በትግ | FastMereja.com

በትግራይ ክልል 9 ሺህ 514 ተማሪዎች ከነገ ጀምሮ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ይወስዳሉ

በትግራይ ክልል ከነገ ጀምሮ በሚሰጠው የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና 9 ሺህ 514 ተማሪዎች ለፈተና እንደሚቀመጡ የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር የትምህርት ጥራት ማረጋገጫ ኤጀንሲ አስታወቀ።

በኤጀንሲው የትምህርት ምዘናና የፈተናዎች ዳይሬክተር አቶ ክንፈ ፍስሃ እንደገለጹት፥ ተፈታኝ ተማሪዎቹ በመቐለ፣ በአክሱም፣ በአዲግራትና በራያ ዩኒቨርሲቲዎች ለአርባ አምስት ቀናት የማጠናከርያ ትምህርት ተሰጥቷቸዋል።

ከተፈታኞቹም 6 ሺህ 513 ተማሪዎች የተፈጥሮ ሳይንስና 3 ሺህ አንድ ደግሞ የማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች መሆናቸውን አስረድተዋል። ከመካከላቸውም 3 ሺህ 941 ሴቶች እንደሆኑ ጠቅሰዋል።

ዘገባው የኢቢሲ ነው!!
@FastMereja