Get Mystery Box with random crypto!

ኢትዮጵያ ወደ ህዋ የላከቻቸው ሳተላይቶች ስራ አቆሙ #FastMereja ኢትዮጵያ የተለያዩ ሳይንሳ | FastMereja.com

ኢትዮጵያ ወደ ህዋ የላከቻቸው ሳተላይቶች ስራ አቆሙ
#FastMereja
ኢትዮጵያ የተለያዩ ሳይንሳዊ ስራዎችን ለመከወን ያግዟታል ተብለው ወደ ህዋ የመጠቁ ሁለቱ ሳተላይቶች ስራ አቁመዋል ተባለ። የስራ ጊዜያቸውን ጨርሰው የሚወገዱበት ጊዜ ስለደረሰ ሌሎች ሳተላይቶች ላይ ጉዳት በማያደርስ መልኩ ለማስወገድ እየተሰራ መሆኑ ተገልፇል።

አዲስ ሳታላይት አልምቶ ለማምጠቅም እየተሰራ መሆኑን የኢንኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ለህዝብ ተወካዮች ተናግሯል። ከዚህ ቀደም ወደ ሳተላይት የመጠቁት ምን ፋይዳ አስገኙ የሚለው እንዳልተገለፀ ነው ሸገር ሬዲዮ የዘገበው።

@fastmereja