Get Mystery Box with random crypto!

በአዲስ አበባ መንገዶች ላይ ሽንት መሽናት 200 ብር መቅጣት ሊጀመር ነው ተባለ! #FastMerej | FastMereja.com

በአዲስ አበባ መንገዶች ላይ ሽንት መሽናት 200 ብር መቅጣት ሊጀመር ነው ተባለ!
#FastMereja
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን በቅርቡ ያወጣው ደንብ ቁጥር 150/2015 ምን ይከለክላል? ሲል ኤፍ ኤም አዲስ 97.1 ይህን ዘገባ ይዞ ወጥቷል፣ ሶፍት፥ወረቀት፥ የአቶብስ ትኬት ፥ የታሸገ ውሃ መያዣ ፕላስቲክ ጥሎ የተገኘ እንደሆነ 200 ብር መቀጮ ይከፍላል። የጣለውን እንዲያጸዳ ይገደዳል።

በመዲናዋ መንገዶች ላይ ሽንት ሲሸና የተገኘ ደግሞ 200 ብር እንዲከፍል ይደረጋል። ሰርግና መሰል ህዝባዊ ፕሮግራሞች አዘጋጅቶ ካጠናቀቀ በሗላ ስፍራውን በተገኒው ሁኔታ ያላጸዳ 5ሺ ብር ይቀጣል።

ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ እስካሁን ደንቡን ማስተዋወቅ እና ማስተማር ላይ ቆይቻለው። አሁን ግን ወደ እርምጃ መሄዴ ነው ብሏል።

@fastmereja