Get Mystery Box with random crypto!

“በትራፊክ አደጋ ጉዳት የደረሰበት ማንኛውም ዜጋ እስከ 2000 ብር ድረስ በነፃ የመታከም መብት አ | FastMereja.com

“በትራፊክ አደጋ ጉዳት የደረሰበት ማንኛውም ዜጋ እስከ 2000 ብር ድረስ በነፃ የመታከም መብት አለው” የመንገድ ደህንነትና መድን ፈንድ አገልግሎት

በአዋጅ ቁጥር 70/99 2005 መሰረት ኢንሹራንስ ባለውም ሆነ በሌለው ተሽከርካሪ የአካል ጉዳት የደረሰበት ግለሰብ በግልም ሆነ በመንግሥት የጤና ተቋም እስከ 2000 ብር ድረስ ነፃና አስቸኳይ ህክምና የማግኘት መብት እንዳለው የመንገድ ደህንነትና መድን ፈንድ ድህረ ትራፊክ አደጋ ዴስክ ኃላፊ ኢክራም የሱፍ ለአራዳ ኤፍ ኤም ተናግረዋል።

በአዋጁ መሰረት ኢንሹራንስ ባላቸው ተሽከርካሪዎች ጉዳት ከደረሰ ኢንሹራንስ የገቡበት ተቋም እስከ 40 ሺህ ብር ድረስ ለአካል ጉዳትና ሞት ለደረሰባቸው ዜጎች ካሳ የመክፈል ግዴታ አለበት።

ተሽከርካሪው የ3ኛ ወገን መድህን ሽፋን ከሌለውና አሽከርካሪው ገጭቶ ካመለጠ አደጋ የደረሰበትን ወይም ህይወቱ ያለፈን ሰው የመድን ሽፋን የመስጠት ኃላፊነት የመንገድ ደህንነትና መድህን ፈንድ አገልግሎት ነው።

አሁን ያለው የመድን ሽፋን በቂ ባለመሆኑ የነፃ ህክምና እና የካሳ ክፍያ አዋጁ ተከልሶ ምክርቤቱ እስኪያፀድቀው እየተጠበቀ እንደሆነ አራዳ ሰምቷል።

Via: አራዳ ኤፍ ኤም

@fastmereja