Get Mystery Box with random crypto!

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የአገልግሎት ክፍያ ማሻሻያ ማድረጉን ገለፀ #FastMereja የኢትዮጵያ | FastMereja.com

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የአገልግሎት ክፍያ ማሻሻያ ማድረጉን ገለፀ
#FastMereja
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በቅርቡ በሚሰጣቸው አገልግሎቶች ላይ የክፍያ ማስተካከያ ማድረጉ ይታወቃል። የተሻሻለውን የአገልግሎት ክፍያ በተመለከት ከደንበኞቻችን ባገኘው ግብረ መልስ መሠረት በአንዳንድ አገልግሎቶች ላይ ድጋሚ የክፍያ ማሻሻያዎች አድርጓል።

በድጋሚ ማሻሻያ የተደረገባቸው አገልግሎቶች እና የተሻሻለው ክፍያ እንደሚከተለው ቀርቧል፡

1. በወዲአህ በተከፈቱ ሂሳቦች በቅርንጫፍም ሆነ በሞባይል ባንኪንግ የሚደረግ ከሂሳብ ወደ ሂሳብ ገንዘብ የማስተላለፍ አግልግሎት ከክፍያ ነፃ ነው፤
2. በሙዳራባህ ውል የተከፈቱና እና ለረጅም ጊዜ ያልተንቀሳቀሱ ሂሳቦች (Inactive Accounts) ከክፍያ ነፃ ናቸው፤
3. በቅርንጫፍ የሚከናወን ከሂሳብ ወደ ሂሳብ ገንዘብ የማስተላለፍ አገልግሎት ክፍያ እንደሚከተለው ተሻሽሏል፡

• ከብር 1 እስከ 10,000 - ብር 5
• ከብር 10,000 እስከ ብር 100,000 - ብር 10
• ከብር 100,001 በላይ - ብር 10 ሲደመር በእያንዳንዱ 100 ሺ 5 ብር (ከ100 ብር ያልበለጠ)

4. በሞባይል ባንኪንግ አገልግሎት የሚከናወን ከሂሳብ ወደ ሌላ ደንበኛ ሂሳብ ገንዘብ የማስተላለፍ አገልግሎት ክፍያ እንደሚከተለው ተሻሽሏል፡

• ከብር 1 እስከ 50,000 - ነፃ
• ከብር 50,001 እስከ ብር 100,000 - ብር 5
• ከብር 100,001 እስከ ብር 200,000 - ብር 10
• ከብር 200,001 እስከ ብር 300,000 - ብር 15
• ከብር 300,001 በላይ - ብር 20

5. በሞባይል ባንኪንግ አገልግሎት ሌላ ባንክ ወደሚገኝ ሂሳብ ገንዘብ ለማስተላለፍ (RTGS) ብር 50 የአገልግሎት ክፍያ ያስከፍላል፤
6. ከ P2P የገንዘብ ዝውውር በ ኢትስዊች (ETSWITCH) 5 ብር እና የኢትስዊች ክፍያን በመደመር የአገልግሎት ክፍያ ይከፈልበታል፤
7. ወደ ሲቢኢ ብር ሂሳብ ከ50 ብር በታች ለማስገባት የሚከፈል የአገልግሎት ክፍያ የለም፤
8. በሲቢኢ ብር በቀን ከ3 ጊዜ በላይ የገንዘብ ልውውጥ ሲኖር ገንዘብ የማስገባት አገልግሎት እንደሚከተለው የአገልግሎት ክፍያ ይታሰብበታል፡

• ከብር 50 በታች - ነፃ
• ከብር 51 እስከ ብር 500 - ብር 6.45
• ከብር 501 እስከ ብር 2,000 - ብር 7.60
• ከብር 2,001 እስከ ብር 3,000 - ብር 8.18
• ከብር 3,001 እስከ ብር 4,000 - ብር 9.33
• ከብር 4,001 እስከ ብር 5,000 - ብር 10.48
• ከብር 5,001 እስከ ብር 6,000 - ብር 11.63
• ከብር 6,001 በላይ - የሚገባው ገንዘብ 0.2 በመቶ

@fastmereja