Get Mystery Box with random crypto!

𝗙𝗔𝗡𝗔 𝗧𝗩 (ፋና)️ ️️

የቴሌግራም ቻናል አርማ fana_televisions — 𝗙𝗔𝗡𝗔 𝗧𝗩 (ፋና)️ ️️ 𝗙
የቴሌግራም ቻናል አርማ fana_televisions — 𝗙𝗔𝗡𝗔 𝗧𝗩 (ፋና)️ ️️
የሰርጥ አድራሻ: @fana_televisions
ምድቦች: ዜና
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 12.32K
የሰርጥ መግለጫ

This is FANA Media and Communication Corporate’s official Telegram channel.
For more updates please visit
https://t.me/fana_televisions
#ሼር 🙏 #በማድረግ_አጋርነታችሁን_አሳዩን
ሀሳብ ወይም መረጃ ለማቀበል @FANA_TV_BOT
https://t.me/joinchat/WC9-gid0rxB-S4Ac

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2023-07-04 22:21:14
መፀዳጃ ቤት አለምድ ብሎ በዳይፐር ብቻ የሚፀዳዳውን የ3 አመት ልጁን በቁጥጥር ስር ያዋለው ፖሊስ አነጋጋሪ ሆኗል

ማይክል ሾንቦርድ የተባለው ግለሰብ በአሜሪካ፣ ፍሎሪዳ ግዛት በዴይቶና ፖሊስ መምሪያ የሚያገለግል ፖሊስ ነው።ይህ ሰው እንጀራው ከሆነው ፖሊስነት በተጨማሪ የአባትነት ሀላፊነትም አለበት።

እናም የ3 አመት ልጁ ግን እርሱ በፈለገው መንገድ ከዳይፐር ውጪ መፀዳዳት ሊለምድለት አልቻለም። በተደጋጋሚ ሞክሮ ሊሳካለት ባለመቻሉና ህፃኑ በለበሰው ልብስ ላይ ተፀዳድቶ በማግኘቱ ወደ ፖሊስ ጣቢያ ሊወስደው በቅቷል።

አባት ይህንን ድርጊት ከአንዴም ሁለቴ መፈፀሙ ብቻ ሳይሆን የጨቅላውን እጅ በካቴና ማሰሩም አስደንጋጭ ሆኗል።

ፖሊሱ ይህንን ተግባር ማከናወኑ የታወቀው በድንብ ልብሱ ላይ በተገጠመው ካሜራ ምክንያት ነው። ካሜራው ያስቀረው ምስል እና ድምፅ ላይ ህፃኑ በከፍተኛ መሸማቀቅ <<ሁለተኛ ልብሴ ላይ አልፀዳዳም>> ሲልም የሚደመጥ ሲሆን አባትም <<ይሄንን ነው መስማት የምፈልገው>> ሲል መልሶለታል።

ፖሊሱ ከዚህ ቀደም አንዲትን ህፃን ደብድቧል ባለው ሌላኛው ልጁ ላይ ተመሳሳይ እስር ፈፅሞ እንደነበርም ተነግራል። ሌላው አስገራሚ ጉዳይ ደግሞ ባለቤቱም በዚያው ተቋም መርማሪ ሆና የምትሰራ መሆኗን ዳጉ ጆርናል ፅፏል።

ይህ ሾንብሮድ የተባለው ፖሊስ የሚሰራበት መምሪያ ጉዳዩን በመመርመር ላይ ያለ ሲሆን የተወሰደ እርምጃ ስለመኖር አለመኖሩ ግን የታወቀ ነገር የለም።
2.1K viewsedited  19:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-04 22:11:52 " ውሳኔው ተገቢነት የሌለው ነው ፤ ፈተናው ከተቻለ አሁን ካልሆነ በቅርብ ቀናት ውስጥ ሊሰጥ ይገባል " - ተማሪዎች / የተማሪ ወላጆች

የሬሜዲያል መርሀግብር ሲከታተሉ ቆይተው ፈተናው ወደ መስከረም 2016 ዓ/ም የተሸጋገረባቸው ተማሪዎች እና የተማሪ ወላጆች የትምህርት ሚኒስቴር ውሳኔ ከፍተኛ ቅሬታ እንዳሳደረባቸው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።

ተማሪዎቹ እና ወላጆቻቸው ለወራት ያህል ገንዘባቸውን እየከፈሉ ትምህርቱን ከተከታተሉና የመጀመሪያ ቀን ፈተና ከወሰዱ በኃላ ሚኒስቴሩ ፈተናው ወደ መስከረም ወር መራዘሙን ማሳወቁ ፍፁም ተገቢ አይደለም በማለት ተቃውመዋል።

አዲስ አበባን ጨምሮ በተለያዩ ክልል ከተሞች የሚገኙ ተማሪዎች ውሳኔ እንዲቀለበስ የሚመለከታቸውን አካላት ተሰባስበው ለመጠየቅ ጥረት ማድረጋቸውን ገልጸዋል።

ለአብነት በአዲስ አበባ 4 ኪሎ፤ ትምህርት ሚኒስቴር አካባቢ ጥያቄ አለን ያሉ ተማሪዎች ተሰባስበው ጥያቄያቸውን ለማቅረብ ጥረት አድርገዋል፤ ከጅማ እንዲሁም ከሀዋሳ የግል ተፈኞች ጥያቄያቸውን ተሰባስበው ለማሳመት እንደጣሩ ለመረዳት ችለናል።

ውሳኔውን ቅሬታ አሳድሮብናል ያሉት የሬሜዲያል የግል ተፈታኝ ተማሪዎች፤ " ብዙ መሰዋትነት ከፍለን ነው የተማርነው ፤ ከቤተሰብ ተለይተን የቤት ክራይ እየከፈልን የት/ት ወርሀዊ ክፍያ እየከፈልን የተማርንም አለን፤ ቤተሰብም እኛን ለማስተማር ሲል ከፍተኛ ዋጋ ከፍሏል ፤ ይህን ሁሉ ተቋቁመን ለ4 ወር ያክል ቆይተን አሁን ፈተናውን እኛ የግል ት/ት ቤት ተማሪዎች ብቻ አትፈተኑም መባላችን ትክክል አይደለም፤ ይህ ውሳኔ ከፍተኛ የስነ ልቦና ጫና ያደርስብናል " ሲሉ ገልጸዋል።

በተመሳሳይ የተማሪ ወላጆች ውሳኔው ልጆቻቸው ብዙ የደከሙበትን ጥረት ወደኃላ የሚመልስ መሆኑን በመግለፅ፤ በጥናታቸው ላይ የሚያሳድረውን ስነልቦናዊ ጫና በመገንዘብ ትምህርት ሚኒስቴር ውሳኔውን በማጠፍ ልጆቻቸው ፈተናቸውን ልክ እንደ ሌሎች ተማሪዎች በተመሳሳይ ጊዜ እና ወቅት እንዲወስዱ እንዲደረግ ጠይቀዋል።

ፈተናውን አሁን ካልተቻለም ደግሞ የተማሪዎች ለፈተናው ያደረጉት ዝግጅት ብዙ ሳይጠፋባቸው በአጭር ቀናት ውስጥ እንዲሆን ተማሪዎቹ እና ወላጆቻቸው ጠይቀዋል።

ተማሪዎቹም ሆኑ ወላጆቻቸው በአሰራር ጉድለት እና በተፈጠረው ችግር ይህ ውሳኔ መተላለፉ በተማሪዎች ህይወት፣ ጊዜ እና እድሜ ላይ ጫና እንዳለው አስረድተዋል። ለዚህ የአሰራር ጉድለት ተወቃሹ ሚኒስቴሩ ሆኖ ሳለ ይህን መሰሉ ውሳኔ ተላልፎ በተማሪዎች ላይ ለሚደርሰው ጫና ማነው ተጠያቂው ? ሲሉም ጠይቀዋል።

በተወሰነው ውሳኔ " የተማሪዎች ሞራል ሊጎዳ አይገባም " ያሉ አንድ የቲክቫህ ቤተሰብ አባል ደግሞ ፤ ተፈጠረ የተባለው ችግር የት እና በማን ተፈጠረ የሚለውን ተጣርቶ ውሳኔ ሊተላለፍ ይገባ ነበር የጅምላ ውሳኔ ተገቢ አይደለም ብለዋል።

" ከጅምሩ እንዲህ ያለ ስጋት ካለ ሁሉም የግል ከፍተኛ ት/ት ተቋማት ተማሪ በመንግስት ዩኒቨርሲቲ ገብቶ እንዲፈተኑ ማድረግ ይቻል ነበር፤ ከዚህ አለፍ ሲልም ሚኒስቴሩ Plan B ሊኖረው ይገባ ነበር " ሲሉ ውሳኔውን ተቃውመዋል። ፈተና በተቻለ ፍጥነት በአጭር ጊዜ ቢሰጥ ብለዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ለተማሪዎቹና ወላጆቻቸውን ቅሬታ በተመለከተ ከሚመለከተው አካል ምላሽ ለማግኘት ጥረት ያደርጋል።

ትምህርት ሚኒስቴር፤ ቀደም ብሎ በሁሉም ሬሜዲያል ፕሮግራም ተጠቃሚ ተማሪዎች ባላቸው ተቋማት ፈተናውን በአንድ ጊዜ ለመስጠት የታቀደው ተሻሽሎ በተለይም ከ150 በላይ የሆኑና ከ200 በላይ ካምፓስ ያላቸውን የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ፈተና ቀርቶ  ወደ ፊት  በሚወሰን አግባብ ፈተናው በመስከረም ወር 2016 ዓ.ም  እንዲሰጥ መወሰኑ ይታወቃል።
1.9K views19:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-04 13:18:05
በሐዋሳ ከተማ ግብረሰዶማዊነትን የሚያወግዝ ሰልፍ ተካሄደ
በትናንትናው እለት በሲዳማና በደቡብ ክልሎች መቀመጫ በሐዋሳ ከተማ የተመሳሳይ ጾታ ጋብቻ/ግብረሰዶማዊነትን/ እና ጽንስ ማቋረጥን የሚያወግዝ ሰልፍ ተካሒዷል።

ሰልፉን ያዘጋጁት በከተማዋ ከሚገኙ 22 የቃለ ሕይወት አጥቢያ ቤተ-ክርስቲያናት የተውጣጡ ምዕምናን ናቸው። ሠልፈኞቹ ከትላንት በስቲያ እሁድ በከተማዋ ዋና ዋና ጎዳናዎች እየተዘዋወሩ ባሰሙት መፈክር የተመሳሳይ ጾታ ጋብቻ እና ጽንስ ማቋረጥን አውግዘዋል።
ሠልፈኞቹ በተመሳሳይ ፆታዊ ግንኙነት እና በውርጃ ላይ ያላቸውን ተቃውሞ ያሰሙት የጹሁፍ መልዕክቶችን በማንገብና መፈክሮችን በማሰማት ነው ፡፡ ሠልፈኞቹ ካሰሟቸው መፈክሮች መካከል “ ግብረ ሶዶማዊነትን እንቃወማለን “ ፣ “ ጽንስ ሕይወት አለው “ ፤ “ ህይወትን መግደል ሀጢያት ነው “ የሚሉ ይገኙባቸዋል ፡፡

የተቃውሞ ሠልፉን ያካሄዱት በሀዋሳ ከተማ ከ22 የቃለ ህይወት አጥቢያ ቤተክርስቲያናት የተሰባሰቡ ምዕመናን መሆናቸውን ከሠልፉ አስተባባሪዎች አንዱ መጋቢ ፍፁምዘለቀ ይናገራሉ ፡፡
ሠልፉ ያስፈለገበት ምክንያትም አገር ፣ ከተማ ፣ ህዝብ እንዲነቃ ለማድረግ መሆኑን የገለጹት መጋቢ ፍፁም “ ህዝቡ ጉዳዩን እንደተራ ነገር ሊያየው አይገባም ፡፡ አስከፊነቱን ሊረዳ ይገባል ፡፡ አዲስ ነገር አይደለም እየተባለ በማህበረሰቡ ውስጥ ሥፍራ እያገኘ ወጣቶችንም ከመንገድ እያስቀረ ይገኛል ፡፡ ሠልፉ ህብረተሰቡ ይህን እንዲውያቅ ለማድረግ የታሰበ ነው “ ብለዋል፡፡
በዩቱብ ቻናላችንም አዳዲስ ያልተሰሙ መረጃዎችን እየለቀቅን ነው።
2.1K views10:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-03 15:55:43 በጋምቤላ ክልል ዲማ ወረዳ ታጣቂዎች በከፈቱት ተኩስ ኹለት የአካባቢው ሚሊሻዎች መገደላቸው ተገለጸ በጋምቤላ ክልል በአኙዋ ብሔረሰብ ዞን በዲማ ወረዳ ለግዜው ማንነታቸው ያልታወቁ ታጣቂዎች በከፈቱት ተኩስ፤ ኹለት የአካባቢው ሚሊሻዎች ሕይወት ሲያልፍ አንድ ሚሊሻ መቁሰሉን የዲማ ወረዳ መንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት አስታወቀ፡፡

የጽ/ቤቱ ሃላፊ ኡኬሎ ኡጁሉ እንደገለጹት ከሆነ፤ በትናንትናው ዕለት ከጥዋቱ 2 :00 ላይ ለግዜው ማንነታቸው ያልታወቁ ታጣቂዎች በካችና ቀበሌ አካባቢ ገብተው በከፈቱት ተኩስ፤ በሰዓቱ ጸጥታ በማስከበር ላይ የነበሩ ኹለት ታጣቂዎች ሕይወታቸው ሲያልፍ አንድ ሚሊሻ ቆስሎ በሕክምና ላይ ይገኛል፡፡

ኡኬሎ አያይዘውም፤ ቅዳሜ ሰኔ 24/2015 ከቀኑ 3:00 አካባቢ ከካችና ቀበሌ ወደ ናምካዶ ቀበሌ በመጓዝ ላይ የነበረው አንድ ሞተረኛ በጥይት ተመትቶ ጉዳት እንደደረሰበት ገልጸዋል።

ሃላፊው አክለውም፤ በወረዳው ላይ የተሻለ ሰላም ቢኖርም ከቅርብ ግዜ ወዲህ በመንገድ ላይ ዝርፊያ የተሠማሩ ሽፍቶች በተደጋጋሚ ጥቃት እየፈፀሙ መሆኑን ገልጸው፤ የወረዳው መንግሥት ጥቃቱን ለማስቆም ከሚመለከታቸው የጸጥታ አካላት የአቅሙን ያህል እየሠራ መሆኑን መናገራቸውን የወረዳው የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ገልጿል፡፡
2.2K views12:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-02 16:29:16 የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች በጉራጌ ዞን በነዋሪዎች ላይ ግድያና እገታ እየፈጸሙ ነው ተባለ
በደቡብ ክልል ጉራጌ ዞን በተለይም ሶዶ ወረዳ፤ ራሱን የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ብሎ የሚጠራውና መንግሥት "ኦነግ ሸኔ" በሚል በአሸባሪነት የፈረጀው ኃይል በአካባቢው ማህበረሰብ ላይ ግድያና እገታ እንደሚፈጽም ነዋሪዎች ለአዲስ ማለዳ ገልጸዋል።

በዚህም የቡድኑ አባላት ነዋሪዎችን አግተው በመውሰድ አርደን የምንበላው ከብት ስጡን፣ የግል የጦር መሳሪያችሁን እንዲሁም ብር አምጡ በማለት በደል እንደሚፈጽሙ ተነግሯል።

ባለፈው ሃሙስ ሰኔ 22/2015 በነዋሪዎቹ ቤት በመግባት "የመንግሥት የጸጥታ አካላትን ትደብቃላችሁ እንዲሁም ያሉበትን ጥቆማ አልሰጣችሁንም" በሚል ነዋሪውን ሲያሰቃዩ እንደነበርና በዚህም ምክንያት አንድ የቀበሌው ነዋሪ የነበሩ አርሶ አደርን መግደላቸው ነው የተገለጸው።

የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች በአካባቢው ከስድስት ወር በፊት ጀምሮ በተደጋጋሚ ጥቃት እያደረሱ ነበር ያሉት ነዋሪዎቹ፤ ከባለፈው ሰኔ 20/2015 ጀምሮ ግን ግድያ እና እገታ እየፈጸሙ ነው ሲሉ ተደምጠዋል።

ነዋሪዎችን አግተው በመውሰድ እስከ 200 ሺሕ ብር እንደሚጠይቁ በመጥቀስም፤ በአካባቢው (በቀበሌው) በቂ የመንግሥት የጸጥታ አካላት ባለመኖራቸው ችግሩ ተባብሶ መቀጠሉን ተናግረዋል።

የታጣቂ ቡድኑ አባላት ወደ ቀበሌው ዘልቀው የሚገቡት ከኦሮሚያ ክልል በመንግሥት የጸጥታ አካላት ሲሳደዱ መሆኑም ተጠቁሟል።

የደቡብ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር እርስቱ ይርዳው በጉዳዩ ላይ መረጃ እየተሰባሰበ መሆኑን ጠቅሰው፤ "ሙሉ መረጃ ሲገኝ የምንገልጽ ይሆናል።" ገልፀዋል።
2.5K views13:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-01 16:33:25 ሁሉም የአገሪቱ የንግድ ስርዓት በሙሉ ተበላሽቷል በሚባልበት ደርጃ ላይ ደርሷል ተባለ
ሁሉም የአገሪቱ የንግድ ስርዓት በሌቦች፣ በኮትሮባንዲስቶችና በሽፍቶች የተተበተበና ስርዓት አልበኝነት የሰፈነበት በመሆኑ፣ በሙሉ ተበላሽቷል የሚባልበት ደረጃ  ላይ መድረሱን የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ገልጿል።

ምክር ቤቱ ይህን የገለጸው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የንግድና ቱሪዝም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር የ11 ወራት ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርትን በትናንትናው ዕለት ባዳመጠበት ወቅት ነው።

በዚህም የሲሚንቶ፣ የጤፍ፣ የምግብ ዘይት፣ የስንዴ፣ የወርቅ፣ የማዳበሪያ፣ እና የሌሎች ፍጆታዎች የንግድ ስርዓት ህግን ባልተከተለ አሰራር የሚመራና ህገወጥ ደላሎች የበዙብት በመሆኑ እጅግ የተበላሸ ነው ተብሏል።

የኢትዮጵያ ህዝብ በኑሮ ውድነትና በሕገወጥ ንግድ ተማሯል ያሉት የምክር ቤቱ አባላት፤ የመንግሥት አመራሮች፣ ደላሎችና ባለሀብቶች ተቀናጅተው በፈጠሩት ብልሹ አሰራር ሕዝቡ እየተጎዳ ነው ሲሉ ተደምጠዋል።

አክለውም፤ ትናንሽ ነጋዴዎች በትልልቅ ነጋዴዎች ጉዳት ይደርስባቸዋል፣ ደላሎችን መቆጣጠር ባለመቻሉም ሕገወጥነት የበላይነትን ይዟል ብለዋል።

ምክር ቤቱ ከዚህ ቀደምም በመሰረታዊ ፍጆታዎች ላይ የተደራሽነት ፍትሃዊነት እና የዋጋ ችግር መኖሩን ለመስሪያ ቤቱ ቢገልጽም ችግሩ አሁንም ተባብሶ እንደቀጠለ ነው ብሏል።

የቋሚ ኮሚቴው አባላት የሲሚንቶ ምርት አዲስ አበባን ጨምሮ በኹሉም ክልሎች እየቀረብ አለመሆኑንና ገበያ ላይ ያለውም በተጋነነ ዋጋ መሸጡን ቢኮንንም፤ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ፋብሪካዎች ካለው ፍላጎት አንጻር ከአንድ ሦስተኛ ያልበለጠ እያቀረቡ በመሆኑ፣ አቅርቦትና ፍላጎቱ እስካልተጣጣመ ድርስ ችግሩ የሚዘልቅ ሊሆን እንደሚችል ጠቁሟል።

የሚንስቴር መስሪያ ቤቱ ዋነኛ ተልዕኮ ጤናማ የተረጋጋ የአገር ውስጥ ብሎም የጠረፍ ንግድ ስርዓት መፍጠር ቢሆንም፣ ህግወጥ ንግድና ኑሮ ውድነት በከፍተኛ ሁኔታ በመባባሱ ይህ ተቋም አለ ወይ የሚያስብል ጥያቄ እንደሚፈጥር በምክር ቤቱ አባላት ተጠቅሷል።

"ማን ኮንትሮባንድ እንደሚሰራ የተጣራ መረጃ የለም" ያለው ምክር ቤቱ፤ በንግድ ስርዓቱ ላይ ጠንካራ ቁጥጥር ባለመኖሩ አብዛኛው የንግድ ማህበረሰብ የንግድ ፈቃዱን እየዘጋ ወደ ሕገወጥ ንግድ እየተቀላቀለ ነውም ብሏል።

በዚህም ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ሳይኖራቸው ሀብታም የሆኑና በንግድ ስርዓቱ ውስጥ የሚገኙ በርካታ ነጋዴዎች መኖራቸው ተመላክቷል።

ስለሆነም በዚህ ልክ የተበላሸው የንግድ ስርዓት ባስከተለው ጥፋት የተቋሙ አመራሮች "ተጠያቂ ለመሆን ዝግጁ ናችሁ ወይ?" የሚል ጥያቄ ከምክር ቤቱ አባላት ተነስቷል።

ምክር ቤቱ የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የ11 ወራት አፈጻጸም ዝቅተኛ ነው ሲል ገልጾ፣ ባለበት የበጄት አጠቃቀም ችግር ለአብነትም ሥራ ላይ መዋል እያለበት ሳይውል የቀረ ከ1 ቢሊዮን ብር በላይ መኖሩን ጠቅሷል።

የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር በተለይም የመሰረታዊ ፍጆታዎች ዋጋ መናር በዓለም አቀፍ እና አገራዊ ችግሮች የተከሰተ መሆኑን ጠቅሶ፤ ችግሩን ለመፍታት የተለያዩ የመፍትሄ አማራጮችን ወስዶ እየሰራ መሆኑን ገልጿል።

እንዲሁም የፍጆታዎችን ዋጋ ለማረጋጋትና ህገወጥ ንግድን ለመቆጣጣር የተለያዩ እርምጃዎችን ወስጇለሁ ያለው ተቋሙ፤ በንግድ ስርዓቱ ላይ የሚታየው ችግር በንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ብቻ ሳይሆን በብዙ ተቋማት ርብርብ የሚፈታ መሆኑ ሊታወቅ ይገባል ብሏል።
2.6K views13:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-30 18:15:01
በፓስተር ዮናታን ንብረቶች ላይ ንብ ባንክየሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ አወጣ
"…ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ አ.ማ ላበደረው ንብረት የሐራጅ ሽያጭ አውጥቷል።

•አበዳሪው ወይም የመያዢያ ሰጪ ስም፣ አበዳሪው ቅርንጫፍ፣ የሚሸጠው ንብረት ዓይነትና የሚገኝበት ቦታ፣ የሐራጁ መነሻ በብር፣ የሐራጁ ቀንና ሰዓትም ተገልጿል።

1ኛ፥ አቶ ዮናታን አኪሊሉ አንጀሎ አራት ኪሎ ፕሪሚየም፣ በስማቸው የተመዘገበ ሀዋሳ ምሥራቅ ከተማ የሚገኝ 400 ሜትር ካሬ ቦታ ያለው ባለ 3 ወለል መኖሪያ ቤት፣ የሐራጁ መነሻ ዋጋ በብር። 22 ሚሊዮን፣ የሀራጁ ቀንና ሰዓት በ17/2015ዓም ከ4:00–6:00 ሰዓት

2ኛ፥ አቶ ዮናታን አክሊሉ አንጄሎ/ ዜብራ ሓላ/የተ/የግ/ማ / 4ኪሎ ፕሪምየም/ በዜብራ ግሪል ሓላ/የተ/የግ/ማ ስም የተመዘገበ ሀዋሳ ከተማ ምሥራቅ ክፍለ ከተማ የሚገኝ 1,271.83 ሜትር ካሬ ይዞታ ያለው ባለ 4/ባለ 2 እና ባለ 1 ወለል ለተለያዩ አገልግሎት የሚውሉ ህንፃ፥ የሐራጁ መነሻ ዋጋ በብር 30 ሚልዮን፣ የሐራጁ ቀንና ሰዓት 17/11/2011 ዓም። ከቀኑ 8:00 ሰዓት እስከ 11:00 ሰዓት

3ኛ፥ አቶ ዮናታን አክሊሉ አንጄሎ ዜብራ ግሪል ሓላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር፣ አበዳሪው ቅርንጫፍ 4ኪሎ ፕሪምየም፣ በዜብራ ግሪል ሓላ/የተ/የግ/ማ ስም እየተመዘገበ። አዲስ ከተማ ቦሌ ክፍለ ከተማ ውስጥ የሚገኝ 500 ካሜ ይዞታ ያለው መኖሪያ ቤት፣ የሐራጁ መነሻ 25 ሚልዮን የሐራጁ ቀንና ሰዓት 17/11/ 2015 ከ4:00 እስከ 6:00 ሰዓት።
2.5K views15:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-30 17:13:08 ወደ እርምጃ ሊገባ ነው
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የኦዲት ክፍተት በተገኘባቸው የመንግሥት መስሪያ ቤቶች ላይ የሕግ አስከባሪ አካላት የእርምት ርምጃ እንዲወስዱ አሳስቧል።
ምክር ቤቱ ይህን ማሳሰቢያ የሰጠው፣ የፌደራል ዋና ኦዲተር መሠረት ዳምጤ ያቀረቡትን የ2014 ዓ፣ም የኦዲት አፈጻጸም ሪፖርት ከገመገመ በኋላ ነው።

ዋና ኦዲተሯ ባቀረቡት ሪፖርት፣ 86 የመንግሥት መስሪያ ቤቶች ባለፉት ጥቂት ዓመታት በጠቅላላው ከ6 ነጥብ 8 ቢለዮን ብር በላይ ተመላሽ እንዲያደርጉ ቢነገራቸውም፣ ተመላሽ ያደረጉት ግን  0 ነጥብ 65 በመቶውን ብቻ እንደኾነ ገልፀዋል።
1.9K views14:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-29 10:07:23
ከ838 ግራም በላይ ወርቅ ሲያሸሹና ህገወጥ ጦር መሣሪያ ይዘው የተገኙ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሥር ዋሉ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 22፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ  ምዕራብ ኢትዮጵያና በጋምቤላ ክልሎች ከ838 ግራም በላይ የወርቅ ማዕድን ሲያሸሹና ህገወጥ ጦር መሣሪያ ይዘው ተገኝተዋል የተባሉ ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ሥር ማዋሉን የፀጥታና ደኅንነት የጋራ ግብረ-ኃይል አስታውቋል።

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ቢሮ ወረዳና በጋምቤላ ክልል ዲማ ወረዳ 20 ክላሽንኮቭ ከ934 መሰል ጥይቶች ጋር፣ 8 ሽጉጥ ከ54 መሰል ጥይቶች ጋር፣ ሁለት ኤፍ ዋን ቦንቦች እና አንድ ጂ ፒ ኤስ መያዛቸው ተገልጿል፡፡

ከዚህ ባለፈም 172 የተለያዩ የወርቅ ጌጣጌጦች፣ ከ838 ግራም በላይ የወርቅ ማዕድን፣ 7 የወርቅ ማቅለጫ ማሽኖች፣ 10 የወርቅ ሚዛን፣ ከ1 ሚሊየን 653 ሺህ ብር በላይ በአሶሳ ዞን ጉሙሩክ የፍተሻ ጣቢያ መያዛቸው ተጠቁሟል ።
2.3K views07:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-28 14:49:52
ለሸኔ የሽብር ቡድን የትጥቅ ድጋፍ ለማድረግ ሲጓዙ የነበሩ ሁለት ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሥር  ዋሉ

ለሸኔ የሽብር ቡድን የትጥቅ ድጋፍ ለማድረግ ሲጓዙ የነበሩ ሁለት ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሥር ማዋሉን የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ አስታውቋል።

ተጠርጣሪዎቹ ሰኔ 20 ቀን 2015 ዓ.ም መነሻቸውን ከአዲስ አበባ ከተማ ለቡ አድርገው አንድ ብሬን እና 263 የክላሽንኮቭ ጠመንጃ ጥይቶችን ጭነው ሲጓዙ ሆለታ ከተማን እንዳለፉ ነው በቁጥጥር ሥር የዋሉት።

ተጠርጣሪዎቹ ከህገ-ወጥ የጦር መሣሪያው በተጨማሪ ለእኩይ ዓለማቸው ማስፈፀሚያ ሐሰተኛ የአዲስ አበባ ከተማ የነዋሪ መታወቂያ፣ የልደት ምስክር ወረቀት፣ ልዩ ልዩ ማህተሞች እና ሀሰተኛ ሰነዶችን እንደያዙ በቁጥር ሥር ውለው ጉዳያቸው በምርመራ እየተጣራ እንደሚገኝ ተጠቁሟል።

ተጠርጣዎቹ በፀጥታና ደህንነት የጋራ ግብረ ኃይል በተደረገ ጠንካራ ክትትል በቁጥጥር ስር መዋላቸው ታውቋል።

ኅብረተሰቡም እነዚህ ህገወጥ መሣሪያዎች በሸኔ የሽብር ቡድን እጅ ቢገቡ ኖሮ በንፁሃን ዜጎቻችን ላይ የሚያደርሱት ጥፋት ከፍተኛ መሆኑን ተገንዝቦ መሰል የወንጀል ተግባራትን ሲመለከት ለፀጥታ አካላት በፍጥነት ጥቆማ በመስጠት እያደረገ ያለውን ተሳትፎ አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ ቀርቧል።
2.3K views11:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ