Get Mystery Box with random crypto!

በሐዋሳ ከተማ ግብረሰዶማዊነትን የሚያወግዝ ሰልፍ ተካሄደ በትናንትናው እለት በሲዳማና በደቡብ ክል | 𝗙𝗔𝗡𝗔 𝗧𝗩 (ፋና)️ ️️

በሐዋሳ ከተማ ግብረሰዶማዊነትን የሚያወግዝ ሰልፍ ተካሄደ
በትናንትናው እለት በሲዳማና በደቡብ ክልሎች መቀመጫ በሐዋሳ ከተማ የተመሳሳይ ጾታ ጋብቻ/ግብረሰዶማዊነትን/ እና ጽንስ ማቋረጥን የሚያወግዝ ሰልፍ ተካሒዷል።

ሰልፉን ያዘጋጁት በከተማዋ ከሚገኙ 22 የቃለ ሕይወት አጥቢያ ቤተ-ክርስቲያናት የተውጣጡ ምዕምናን ናቸው። ሠልፈኞቹ ከትላንት በስቲያ እሁድ በከተማዋ ዋና ዋና ጎዳናዎች እየተዘዋወሩ ባሰሙት መፈክር የተመሳሳይ ጾታ ጋብቻ እና ጽንስ ማቋረጥን አውግዘዋል።
ሠልፈኞቹ በተመሳሳይ ፆታዊ ግንኙነት እና በውርጃ ላይ ያላቸውን ተቃውሞ ያሰሙት የጹሁፍ መልዕክቶችን በማንገብና መፈክሮችን በማሰማት ነው ፡፡ ሠልፈኞቹ ካሰሟቸው መፈክሮች መካከል “ ግብረ ሶዶማዊነትን እንቃወማለን “ ፣ “ ጽንስ ሕይወት አለው “ ፤ “ ህይወትን መግደል ሀጢያት ነው “ የሚሉ ይገኙባቸዋል ፡፡

የተቃውሞ ሠልፉን ያካሄዱት በሀዋሳ ከተማ ከ22 የቃለ ህይወት አጥቢያ ቤተክርስቲያናት የተሰባሰቡ ምዕመናን መሆናቸውን ከሠልፉ አስተባባሪዎች አንዱ መጋቢ ፍፁምዘለቀ ይናገራሉ ፡፡
ሠልፉ ያስፈለገበት ምክንያትም አገር ፣ ከተማ ፣ ህዝብ እንዲነቃ ለማድረግ መሆኑን የገለጹት መጋቢ ፍፁም “ ህዝቡ ጉዳዩን እንደተራ ነገር ሊያየው አይገባም ፡፡ አስከፊነቱን ሊረዳ ይገባል ፡፡ አዲስ ነገር አይደለም እየተባለ በማህበረሰቡ ውስጥ ሥፍራ እያገኘ ወጣቶችንም ከመንገድ እያስቀረ ይገኛል ፡፡ ሠልፉ ህብረተሰቡ ይህን እንዲውያቅ ለማድረግ የታሰበ ነው “ ብለዋል፡፡
በዩቱብ ቻናላችንም አዳዲስ ያልተሰሙ መረጃዎችን እየለቀቅን ነው።