Get Mystery Box with random crypto!

በጋምቤላ ክልል ዲማ ወረዳ ታጣቂዎች በከፈቱት ተኩስ ኹለት የአካባቢው ሚሊሻዎች መገደላቸው ተገለጸ | 𝗙𝗔𝗡𝗔 𝗧𝗩 (ፋና)️ ️️

በጋምቤላ ክልል ዲማ ወረዳ ታጣቂዎች በከፈቱት ተኩስ ኹለት የአካባቢው ሚሊሻዎች መገደላቸው ተገለጸ በጋምቤላ ክልል በአኙዋ ብሔረሰብ ዞን በዲማ ወረዳ ለግዜው ማንነታቸው ያልታወቁ ታጣቂዎች በከፈቱት ተኩስ፤ ኹለት የአካባቢው ሚሊሻዎች ሕይወት ሲያልፍ አንድ ሚሊሻ መቁሰሉን የዲማ ወረዳ መንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት አስታወቀ፡፡

የጽ/ቤቱ ሃላፊ ኡኬሎ ኡጁሉ እንደገለጹት ከሆነ፤ በትናንትናው ዕለት ከጥዋቱ 2 :00 ላይ ለግዜው ማንነታቸው ያልታወቁ ታጣቂዎች በካችና ቀበሌ አካባቢ ገብተው በከፈቱት ተኩስ፤ በሰዓቱ ጸጥታ በማስከበር ላይ የነበሩ ኹለት ታጣቂዎች ሕይወታቸው ሲያልፍ አንድ ሚሊሻ ቆስሎ በሕክምና ላይ ይገኛል፡፡

ኡኬሎ አያይዘውም፤ ቅዳሜ ሰኔ 24/2015 ከቀኑ 3:00 አካባቢ ከካችና ቀበሌ ወደ ናምካዶ ቀበሌ በመጓዝ ላይ የነበረው አንድ ሞተረኛ በጥይት ተመትቶ ጉዳት እንደደረሰበት ገልጸዋል።

ሃላፊው አክለውም፤ በወረዳው ላይ የተሻለ ሰላም ቢኖርም ከቅርብ ግዜ ወዲህ በመንገድ ላይ ዝርፊያ የተሠማሩ ሽፍቶች በተደጋጋሚ ጥቃት እየፈፀሙ መሆኑን ገልጸው፤ የወረዳው መንግሥት ጥቃቱን ለማስቆም ከሚመለከታቸው የጸጥታ አካላት የአቅሙን ያህል እየሠራ መሆኑን መናገራቸውን የወረዳው የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ገልጿል፡፡