Get Mystery Box with random crypto!

𝗙𝗔𝗡𝗔 𝗧𝗩 (ፋና)️ ️️

የቴሌግራም ቻናል አርማ fana_televisions — 𝗙𝗔𝗡𝗔 𝗧𝗩 (ፋና)️ ️️ 𝗙
የቴሌግራም ቻናል አርማ fana_televisions — 𝗙𝗔𝗡𝗔 𝗧𝗩 (ፋና)️ ️️
የሰርጥ አድራሻ: @fana_televisions
ምድቦች: ዜና
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 12.32K
የሰርጥ መግለጫ

This is FANA Media and Communication Corporate’s official Telegram channel.
For more updates please visit
https://t.me/fana_televisions
#ሼር 🙏 #በማድረግ_አጋርነታችሁን_አሳዩን
ሀሳብ ወይም መረጃ ለማቀበል @FANA_TV_BOT
https://t.me/joinchat/WC9-gid0rxB-S4Ac

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 5

2023-04-27 13:11:02
[ Album ]
በትግራይ ክልል ከ1-12ኛ ክፍል ተማሪዎች ምዝገባ ተጀምሯል።
ሚያዝያ 19/2015 ዓ.ምሀሳብ አስተያየት መረጃ ካሎት @FANA_TV_BOT ያድርሱን
ቻናላችንን ይቀላቀሉ
@fana_televisions
@fana_televisions
1.6K views10:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-27 10:54:31 በአማራ ክልል ተነስቶ የነበረውን ውጥረት ተከትሎ ለእስር የተዳረጉ ሰባት ጋዜጠኞች በአስቸኳይ እንዲፈቱ ሲል አምኒስቲ ኢንተርናሽል አሳስቧል።
የጋዜጠኞቹ እስር የሚዲያ ነጻነት እና ሐሳብን በነጻነት የመግለጽ መብት ላይ የተወሰደ ጥቃት ነው ያለው ድርጅቱ፤ ድርጊቱን የፈጸመው የሚመለከተው የመንግሥት አካል ጋዜጠኞቹ በፍጥነት እንዲፈታ እና የቀረበባቸውን ክስ እንዲያነሳ ብሏል።

የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቱ፤ ‹‹ጋዜጠኞች እና የመገናኛ ብዙኀን ባለሞያዎች፣ ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ፤ ለሕዝብ ተገቢውን መረጃ እንዲያደርሱ እና የመንግሥት ኃላፊዎችን ተጠያቂ ማድረግ እንዲችሉ፣ ሥራቸውን ያለምንም ስጋት፣ ጣልቃ ገብነት እና ትንኮሳ ሊሠሩ ይገባል።›› ብሏል።ሀሳብ አስተያየት መረጃ ካሎት @FANA_TV_BOT ያድርሱን
ቻናላችንን ይቀላቀሉ
@fana_televisions
@fana_televisions
1.6K viewsedited  07:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-27 10:47:51 ህገወጥ የጵጵስና ሹመት ፈጽመዋል የተባሉ አካላት የቤተክርስትያን ንብረቶችን በማሸሸና ንዋየ ቅዱሳትን በመሸጥ ላይ ናቸው ተባለ
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን ቅዱስ ሲኖዶስ በሕገወጥ የጳጳሳት ሹመት ተሳትፈዋል ተብለው የተጠቀሱ አካላት አሁንም በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ሐረርጌ አገረ ስብከት ተገቢ ያልሆነ ተግባር እየፈጸሙ ነው ሲሉ የአካባቢው ነዋሪዎች ገለፁ።
ነዋሪዎች አክለውም፤ ለሀገረ ስብከቱ መንፈሳዊ አግልግሎት የሚውሉ ተሽከርካሪዎችን፣ በከብት መድለቢያ የደለቡ ሰንጋዎችን እንዲሁም የተለያዩ ንብረቶችን በማሸሽ ላይ ናቸው ብለዋል፡፡

ለአብነትም በጭሮ ከተማ ከሚገኙ አምስት አብያተክርስትያናት ሦስቱን በኃይል ሰብረው በመግባት የተቆጣጠሩት እነዚህ አካላት በምዳዬ ምጽዋት ውስጥ የሚገኙ ገንዘቦችን በመውሰድ እና የአብያተ ክርስትያናቱን ንዋየቅዱሳት አውጥተው በመሸጥ ላይ መሆናቸው ተገልጿል፡፡

ይህን ተከትሎም በአካባቢው የሚኖሩ የእምነቱ ተከታዮች በቅዱስ ሲኖዶሱ ተለይተው በተወገዙ አካላት አንገለገልም በማለታቸው የቤተክርስትያን አገልግሎት እያገኙ እንዳልሆነ ጠቁመዋል፡፡

ነዋሪዎቹ ይህን ተግባር እየፈጸሙ ያሉት አካላት እየታገዙ ያለው በመንግሥት የጸጥታ አካላት መሆኑን ጠቁመው፤ ድርጊታቸውን የሚቃወሙ አካላትን የማሰርና የማዋከብ ሥራ በመንግሥት አካላት እየተፈጸመ እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡

ከዚህ ጋር ተያይዞ መንግሥት ህግ እንዲያስከብር በተደጋጋሚ ብንጠይቅም ህገወጦችን ከማስቆም ይልቅ በተቃራኒው ጥያቄ ያቀረቡ አካላት ናቸው እስርና ወከባ እየተፈጸመባቸው ያለው ብለዋል፡፡

ስለሆነም በአካባቢው ያለው የመንግሥት መዋቅር ከቤተክርስትያን ላይ እጁን እንዲያነሳ ጠይቀዋል፡፡

የኦሮሚያና የብሔር ብሔረሰቦችን ሲኖዶስ እንመሰርታለን ያሉ አካላት ባለፈው ጥር ወር የ27 ኤጲስ ቆጶሳትን ሹመት ማከናወናቸው እና ይህን ተከትሎም በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን ቅዱስ ሲኖዶስ ውግዘት እንደተላለፈባቸው ይታወቃል(አዲስማለዳ)፡፡ሀሳብ አስተያየት መረጃ ካሎት @FANA_TV_BOT ያድርሱን
ቻናላችንን ይቀላቀሉ
@fana_televisions
@fana_televisions
1.5K viewsedited  07:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-27 10:43:13
[ Album ]
In the end
የአማራ ክልል ፕሬዚዳንት ዶ/ር ይልቃል ከፋለ እና ጌታቸው ረዳ በዚህ መልኩ መቀሌ ተገናኝተዋል።
ሚያዝያ 19/2015 ዓ.ም
=======≠========ሀሳብ አስተያየት መረጃ ካሎት @FANA_TV_BOT ያድርሱን
ቻናላችንን ይቀላቀሉ
@fana_televisions
@fana_televisions
1.5K views07:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-26 20:08:35 #ነዳጅ

የነዳጅ ግብይትን በዲጂታል የክፍያ ዘዴ ለማስፈጸም ከትናንት በስቲያ ጀምሮ መተግበር የጀመረው አሠራር፣ የአዲስ አበባ ከተማ ማደያዎችን እያጨናነቀ እና ለነዳጅ እጥረት መንስዔ እየሆነ እንዳለ ተገልጿል።

ተገልጋዮች ከመጠን በላይ የነዳጅ ግዥ እየፈጸሙ በመሆኑ፣ በአንዳንድ ማደያዎች የነዳጅ እጥረት እየተፈጠረ መሆኑ ታውቋል፡፡

የዲጂታል ክፍያ መተግበሪያውን ለመጠቀም የተፈጠረው ብዥታም በብዙ ማደያዎች ረዣዥም ሠልፎች እንዲታዩ ከማድረጉም በላይ ቶሎ ነዳጅ ቀድቶ ለመሄድ አዳጋች እንዲሆን አድርጎታል፡፡

የኢትዮጵያ ነዳጅ አዳዮች ማኅበር ፥ አሁን ያለው መጨናነቅ የተፈጠረው አገልግሎቱን ለማስጀመር በቂ ጊዜ ባለመሰጠቱና አሽከርካሪዎች አገልግሎቱ ከመጀመሩ በፊት እንዲዘጋጁ ባለመደረጉ ነው ብሏል።

" ይሄንን ሥጋታችንን ቀደም ብለን አሳውቀናል " ያለው ማህበሩ " አሁን ብዙዎች ወደ ሲስተሙ እየገቡ ቢሆንም ከሥጋት አንጻር የተሽከርካሪዎቻቸውን የነዳጅ ታንከር በመሙላት፣ ግዥ የሚፈጸሙ አሽከርካሪዎች ለነዳጅ እጥረት መንስዔ እየሆኑ ነው " ሲል አሳውቋል።

ድርጊቱ የነዳጅ እጥረት ሊያስከትል ይችላል ተብሎ እንደሚሠጋ የገለፀው የኢትዮጵያ ነዳጅ አዳዮች ማኅበር አሁንም ቢሆን ወደ ዲጂታል የግብይት ሥርዓቱ የማስገባቱ ሥራ እንደተጠበቀ ሆኖ፣ ከዚህ ጋር በተያያዘ ሊፈጠር የሚችለውን የነዳጅ እጥረት ለመቅረፍ ተጨማሪ የነዳጅ አቅርቦት ያስፈልጋል ብሏል።

" አሁን የሚታየው መጨናነቅ የተወሰኑ ቀናት ሊቀጥል የሚችል ቢሆን እንኳን መጨናነቁን ለማስቀረት የግድ መንግሥት በቂ ነዳጅ ወደ ከተማው እንዲገባ ማድረግ ይገባዋል፥ ይህንን ካላደረገ ዕድሉን አግኝተው ነዳጅ የሚቀዱ ተገልጋዮች፣ ከፍላጎታቸው በላይ እየቀዱ የሚቀጥሉ ስለሚሆን የነዳጅ አቅርቦቱ ላይ ተፅዕኖ ሊያሳድር ይችላል " ሲል ማህበሩ ጠቁሟል።

በሌላ በኩል ከዚሁ የነዳጅ ግብይት ጋር በተያያዘ ኢትዮ ቴሌኮም አሠራሩን ከመተግበር አንጻር ያለውን መጨናነቅ ለማስቀረት በሁሉም የአዲስ አበባ ከተማ ማደያዎች #ባለሙያዎችን በማሰማራት ለተገልጋዮች ድጋፍ እየሰጠ መሆኑን አስታውቋል፡፡

የትራንስፖርትና ሎጂስቲክ ሚኒስትር ደኤታው አቶ ኦዴኦ ሐሰን ፥ ይህን አገልግሎት ለመተግበር #መንገራገጮች ቢኖሩም፣ በአዲስ አበባ ከተማ የተጀመረው አዲስ አሠራር ከግንቦት 1 ቀን 2015 ጀምሮ በመላ አገሪቱ ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ እንደሚሆን አረጋጋጠዋል፡፡

የአገልግሎቱ መጀመር ዘመናዊ ግብይትን ከማሳለጥ ባለፈ ከነዳጅ ሥርጭት ጋር በተያያዘ ሲፈጠሩ የነበሩ ብልሹ አሠራሮችንና ብክነትን ከማስቀረት አኳያ፣ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ሚኒስትር ዴኤታው ገልጸዋል፡፡

ይህንን የገለፁት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የዲጂታል የነዳጅ ግብይት መተግበሪያዎቹን ይፋ ባደረገበት ስነ ስርዓት ላይ ተገኝተው ባሰሙት ንግግር ነው።

ምንጭ፦ ሪፖርተር ጋዜጣ
635 views17:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-26 10:27:27
የኪራይ ገቢ ግብር ማስከፈያ ምጣኔ
በድርጅቶች የሚከፈለው የኪራይ ገቢ ግብር መጣኔ 30% (ሰላሳ በመቶ) ነው፡፡
የተከራይ አከራዮች
የተከራይ አከራይ በግብር ዓመቱ ያገኘው ግብር የሚከፈልበት ገቢ ነው የሚባለው የተከራይ አከራይ በግብር ዓመቱ ከተቀበለው ጠቅላላ የኪራይ ገቢ ላይ ለዋናው አከራይ የሚከፍለው ኪራይ እንዲሁም ገቢውን ለማግኘት ያወጣቸው ሌሎች ወጪዎች ከተቀነሱ በኋላ የሚቀረው ገንዘብ ነው፡፡
ተከራይ የተከራየውን ቤት መልሶ እንዲያከራይ የሚፈቅድ የቤት ባለቤት ተከራዩ ግብሩን ሳይከፍል ቢቀር ስለእርሱ ሆኖ ግብሩን የመክፈል ኃላፊነት ይኖርበታል፡፡
የግለሰቦች የኪራይ ገቢ ግብር ማስከፈያ መጣኔዎች ከላይ በፎቶ የተጠቀሱት ናቸው።
ገቢዎች ሚኒስተር
ሚያዝያ 18/2015 ዓ.ም
1.2K views07:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-26 10:26:15 በታንዛኒያ ዛንዚባር ደሴት በኢትዮጵያ መንግስት እና በኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት መካከል የሰላም ውይይት ትናንት ተጀመረ
በታንዛኒያ የሰላም ድርድር ዛሬ ማለዳ መጀመሩን በስፍራው የነበሩ ምንጮች ለቢቢሲ ተናግረዋል። በውይይቱ ላይ የሁለቱም ወገኖች ተወካዮች ስድስት ሰዎች እየተሳተፉ መሆናቸውን ምንጮች ለቢቢሲ ተናግረዋል።

በመንግስት በኩል ወደ ታንዛኒያ የተጓዘው የልዑካን ቡድን አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን እና ዶ/ር ጌዲዮን ጢሞቲዮስ እንደሚገኙበት ቢቢሲ ዘግበዋል።

በኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት በኩል አንጋፋው የታሪክ ፕሮፌሰር መሃመድ ሃሰን እና የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት ዋና አዛዥ አማካሪ ሚስተር ጂሬኛ ጉዳታ እና አቶ አብዲ ጠሃ እና ሌሎችም መገኘታቸውን ቢቢሲ ዘግቧል።ሀሳብ አስተያየት መረጃ ካሎት @FANA_TV_BOT ያድርሱን
ቻናላችንን ይቀላቀሉ
@fana_televisions
@fana_televisions
1.1K viewsedited  07:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-25 11:31:39
አሳዛኝ
ትላንት ማታ 24/4/2023 በጉጂ አንድ የባጃጅ ሹፌር ለጊዜው የማይታወቅ) “አብረን እንዲሄድ” አሉት።  እምቢ ሲል ነብሱን ከነባጃጁ አብሮ አቃጠሉት::
1.7K views08:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-24 15:10:21 (ለ110  ችግር 110> መፍትሔዎች አሉን )

   >> የባህል  መድኃኒት
ህክምና
መስጫ  ተቋም ።

  >>ከምንሰጣቸው አገልግሎቶች ጥቂቶችን

በዝርዝር  ዕንመልከት።

   1> ለመፍትሔሥራይ (የጠላት ድግምት መሻሪያ)
   2>>ለቡዳ
    3>> ለቁራኛ
    4, #መጠብቅ (ከጠላት ከሚላክ ሟርት
      የሚጠብቅ )
     5 >>  ለጋኔን መከላከያ

6, ለማንኛውም ዓይነት በሽታ መፍትሔ
7, ለራእይ (በህልም የሚያሳይ)
8,  ለፀር (ለጠላት)
9, ዓቃቤ_ርእስ (ጠላት እንዳይጎዳን የሚጠብቅ)
10,  ለዘኢያገድፍ (ለትምህርት የማያስጠፋ የማያስረሳ)

   11,ለመክስተ_ምስጢር (ትምህርት የሚያጎብዝ)
    12, ለመፍትሔ_ሀብት(ሀብቱ በጠላት ድግምት ለተሰወረበት)
   13, ለህዝ  መስተፋቅር
   14 ;ለግርማ_ሞገስ (ሰው እንዲያከብረን እንዲወደን)
  15,ለመድፍነ_ፀር (ጠላት እንዳይናገረን እና
እንዲፈራ፡፡

>>>>> 16, ለሌባ(እንዳንሰረቅ እንዳንዘረፍ የሚጠብቅ)
>>>>> 17, የትዳር አጋር ላጣ ወይም ላጣች
የሚያስገኝ
>>>>> 18,ለምስያጥ ለገበያ (ገበያ እንዲቀናን እንድናገኝ)
>>>>> 19; መስተኃድር (ከብት ቢጠፋብን ሳይበሉ በሰላም እቤታቸው
የሚያመጣ)
>>>>> 20, መንድግ(በገበያ ገንዘብ ማግኛ)

  21, ለዓይነ_ጥላ (የፍራቻ መንፈስ ማስለቀቂያ)
22, ለልሳነ_ሰብእ
23, ለበረከት
24,ለእግረ_መልስ (ጥሎ ለጠፋ ሰው መመለሻ ማምጫ)
25,ምስሀበ_ነዋይ(ገንዘብ ማግኛ)

        26,ጸሎተ_ዕለታት ወይም የ7ቱ ቀን ጸሎት።
       27,ለጽሑፍ ለስእል ለከበሮ ለበገና ለክራር በእጂ ለሚሰሩ ነገሮች።
    28, ንባብ ስናነብ ቀልጣፋ የሚያረግ
   29, ለከበሮ
  30,ለመፍዝዝ (ጠላት እኛን ለማጥቃት      ሲሞክር አጠገባችን ሲደርስ
መጣላቱን አስረስቶ አፍዝዞ የሚያስቀር የማያስመታ)

➠31, ለሙግት
➠32,ለሰላቢ
➠33,ለስንፈት ወሲብ
➠34,ዘኢያወርድ ( ለወንዶች በፆታዊ ግንኙነት ወቅት የዘር ፍሬ ቶሎ
እንዳይወርድ የሚያረግ አግዶ የሚያቆይ)
➠35, ለመደንግፅ (የተጣላን ሰው እኛን ሲያይ እንዲደነግጥ እንዲፈራ
የሚያረግ)

        36,ለጥይት (ጥይት የማያስመታ)
        37, ለዱላ( ዱላ የማያስመታ)     
      38,መንስኤ_እስኪት
      (ለወንድ የመራቢያ አካሉ ለደከመ ላነሰ)
      39,ህገ_ጠብቅ (የትዳር አጋራችን
                         ወደሌላ እንዳይሄድ የሚያስር እንዳይዘሙት የሚከለክል)

40, ለአይነ_ሰብእ (ከሰው አይን የሚጠብቅ)
41;ለአዙሪት በሽታ
42; ለአስቸጋሪና ተመላላሽ ድግምት
43;ለሪህ/ ዩሪክ  አሲድ  በሽታ
44;ለመገጣጠሚያ ህመም

        45;ለጉልበት ድርቀት
       46; ለባት ህመም
      47;ለወገብ ህመም
      48;ለአንገትና ትከሻ ህመም
      49;ለጠነከረ ደረቅ ሳል

50;ለደም ግፊት
51;የሆድ መረበሽ
52;የከፋ የሆድ ድርቀት
53;በመኝታ ጊዜ ሽንት ለሚያመልጠው ሰው
54;የአእምሮ ጭንቀት፣ ድብርት፣
          መገለል፣እንቅልፍ ማጣት፡፡

     55; እንቅልፍ ማብዛት
   56;የተለየ የቆዳ ህመም
   57;ክብደት ለመቀነስ
  58;የእንቅርት በሽታ
  59;ለራስ ምታት

60; አይን አካባቢ ውጥረት ካለ
61; የሳይነስ ህመም
62;የሆድ ድርቀትና የሆድ ህመም
63;የወር አበባ ችግር ካለ
64;የወገብ መንሸራተት ካለ


➮65;ውጥረትና የአእምሮ ጭንቀት
➮66;ለከፍተኛ ራስ ምታት መዳረግ
67;ማስታወስ፣ንቃት፣ተነሳሽነት ለሌላቸው
➮68;ለድምፅ መታፈን
➮69;ከአጫሽነት ለመላቀቅ

            70;ራስን ስቶ መውደቅ
           71; ለአእምሮ ዝግመት     
             72;ለወር አበባ መቋረጥ
             73;ለወር አበባ መዛባት
            74; ለኪንታሮት በሽታ

>>75; ለስኳር ህመም
>>76;ለጨጓራ በሽታ
>>77;ለኩላሊት ህመም
>>78;ለጨብጥ/አባላዘር በሽታ
>>79;ለፌስቱላ ነቀርሳ

            
              80; ለጆሮ ህመም

            81 ለሌባ ገትር ወይም ሊሠርቅ የመጣን
             ሌባ  ወይም ዘራፊ  ገትሮ የሚያሥቀር

           82 ለዕፀ መሠውር  ከጠላት ወይም
                       ከማንኛውም ነገር ለመሠወር

            83 የመኖሪያ ቦታ ክፍል ይሆነኛል ወይስ
                          ዓይሆንም የሚለውን ለማቅ

             84 ገንዘብ ወስዶ አልሰጥም ላለሰው
            የገንዘብ ማስመለሻ

            85 የእርጅና መከላከያ መድኃኒት

86 ለወስፋት  በሽታ መፍትሔ

87 ለኮሶ በሽታ  መፍትሔ

88 ለአሜባ በሽታ መፍትሔ

89 ለጃርድያ በሽታ መፍትሔ

90 ለወባ በሽታ

      ➠91ለጉንፋን ህመም
    ➠92 ላብ ለሚበዛበት ሰው
    ➠93 ለውስጥና ለውጭ  የትኩሣት ህመም
    ➠94 ለፌራ በሽታ
    ➠95 ለኢንፍሉዌንዛ በሽታ

96 ለምች ህመም
97 በሽታው ለሚያገረሽበት ሰው
98 ለቸነፈር ህመም
99 ለሚጥለውና አረፋ ለሚያስደፍቅ በሽታ
100 ለዛር ውላጅ

101>ለሾተላይ በሽታ
102 >ለዕጀሰብእ በሽታ
103 >ለሚደነግጥ ህፃን
104 >በጣም ለሚከሣ ህፃን
105 >ለዕንቅልፍ ማጣት በሽታ

106 ➠ዕንቅልፍ ከመጠን በላይ ለሚበዛበት ሰው
107 ➠ለአጅል ህመም
108 ➠ላንገት ላይ ቁስል
109 ➠ለማንኛውም ዕባጭ
110 ➠ለአጥንት ውስጥ የሥጋ ደዌ

እነዚህንና ሌሎች የተለያዩ
        መፍትሔዎችን
      ዕንሰጣለን።

ሃሎ ይበሉ ለችግርዎ ፈጥነን መፍትሄ  ዕንሰጠዎታለን።
  ለበለጠ መረጃ በስልክ 0906702623           0906702623
ይደውሉ  ሙሉ መረጃ ያገኛሉ።
2.0K views12:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-22 12:54:02
ስምንተኛ ቀኑን በያዘው በዛሬው ቀን የRSF ወታደሮች በአልሁዳን እስርቤት ላይ ጥቃት በማድረስ እስረኞችን አስፈትተዋል ሲሉ የSAF ( Sudanese Armed Forces) ቃል አቀባይ ተናግረዋል።
360 viewsedited  09:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ