Get Mystery Box with random crypto!

𝗙𝗔𝗡𝗔 𝗧𝗩 (ፋና)️ ️️

የቴሌግራም ቻናል አርማ fana_televisions — 𝗙𝗔𝗡𝗔 𝗧𝗩 (ፋና)️ ️️ 𝗙
የቴሌግራም ቻናል አርማ fana_televisions — 𝗙𝗔𝗡𝗔 𝗧𝗩 (ፋና)️ ️️
የሰርጥ አድራሻ: @fana_televisions
ምድቦች: ዜና
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 12.32K
የሰርጥ መግለጫ

This is FANA Media and Communication Corporate’s official Telegram channel.
For more updates please visit
https://t.me/fana_televisions
#ሼር 🙏 #በማድረግ_አጋርነታችሁን_አሳዩን
ሀሳብ ወይም መረጃ ለማቀበል @FANA_TV_BOT
https://t.me/joinchat/WC9-gid0rxB-S4Ac

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 10

2023-04-03 17:05:09 አዲስ አበባ
በአዲስ አበባ ከተማ ኹለት ሰዎች በወንዝ ውስጥ ሕይወታቸው አልፎ ተገኙ
በአዲስ አበባ ከተማ ዛሬ መጋቢት 25 ቀን 2015 ከጠዋቱ 2:08 በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 11 ልዩ ቦታዉ 18 መንደር እየተባለ በሚጠራዉ አካባቢ በሚገኝ ወንዝ ዉስጥ አንድ ሰው ሕይወቱ አልፎ መገኘቱን የእሳት አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን አስታውቋል።

ከሌላ ቦታ ጎርፍ ያመጣዉ ዕድሜዉ 20 የሆነ ወጣት አስከሬን በአደጋ ጊዜ ሠራተኞች መውጣቱን ነው ኮሚሽኑ የገለጸው።

በተመሳሳይ ዛሬ ሰኞ ከጠዋቱ 3:28 በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 05 ሸንበቆ ሰፈር በሚገኘዉ ወንዝ ዉስጥ ዕድሜዉ 45 ዓመት የሆነ ሰዉ ሕይወቱ አልፎ መገኘቱን የኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ ንጋቱ ማሞ ለብስራት ሬድዮ ተናግረዋል። ግለሰቡ በዚያዉ አካባቢ ነዋሪ እንደነበረም ተመላክቷል።

የኹለቱንም ሰዎች አስከሬን አደጋ ጊዜ ሠራተኞች አዉጥተዉ ለፖሊስ ያስረከቡ ሲሆን፤ አሟሟታቸዉን በተመለከተ ፖሊስ እያጣራ መሆኑን ኮሚሽኑ አስታውቋል።
893 views14:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-03 17:04:19
ሩሲያ የፀጥታው ም/ቤት ፕሬዝዳንት በመሆኗ የተደናገጠችው ዩክሬን ሁኔታው “ የዓለም ህዝብን በጥፊ እንደመምታት ነው” ብላለች
ሩሲያ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት የሚያዝያ ወር ፕሬዳንት ስፍራን ተረክባለች።
ዩክሬን ለሩሲያ የፀጥታው ምክር ቤት የወሩ ፐሬዝዳንትነት ስፍራ እንዳይሰጣት ለማድረግ በርካታ ጥረቶችን ብታደርግም ሳይሳካ ቀርቷል ነው የተባለው።
የፀጥታው ምክር ቤት ፕሬዘዳንትንት በሩሲያ መያዝ ያስደገጣት ዩክሬን በበኩሏ፤ “የወሩ ምርጥ ቀልድ ነው” በማለት አጣጥላለች።
905 views14:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-02 22:34:53
[ Album ]
ታዋቂው የፕሮቴስታንት ፓስተር ተጠመቀ
ታዋቂው የፕሮቴስታንት ፓስተር የሆነው በቀድሞ ስሙ ፓስተር ቢኒያም ተብሎ የሚጠራው
በወላይታ ደብረ መንክራት አቡነ ተክለሃይማኖት ቤተክርስቲያን በመጠመቅ "ፍቅረ ኢየሱስ" በሚል ስመ ክርስትና ሐብተ ወልድን ተቀብሏል።https://t.me/fana_televisions
450 views19:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-02 16:54:58 ሩሲያ የተመድ የፀጥታው ምክር ቤት ፕሬዝዳንትነትን ተረከበች
በሩሲያ ፕሬዝዳንትነት የተበሳጨችው ዩክሬን “ዓለም አቀፉን ማህበረሰብ በጥፊ እንደመምታት ነው” ብላለች ሩሲያ በዩክሬን ጦርነት ከጀመረች ወዲህ የፀጥታው ም/ቤት ፕሬዝዳንት ስትሆን ለመጀመሪያ ጊዜ ነው

ሩሲያ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት የሚያዝያ ወር ፕሬዳንት ስፍራን ተረክባለች።

ዩክሬን ለሩሲያ የፀጥታው ምክር ቤት የወሩ ፐሬዝዳንትነት ስፍራ እንዳይሰጣት ለማድረግ በርካታ ጥረቶችን ብታደርግም ሳይሳካ ቀርቷል ነው የተባለው።

ሩሲያ ኃላፊነቱን መረከቧን ተከትሎ በተመድ የሩሲያ አምባሳደር ቫሲሊይ ናቤንዚያ፤ ሞስኮ በፕሬዝዳንትነት ጊዜወ የጦር መሳሪያ ቁጥጥርን ጨምሮ በበርካታ ጉዳዮች ላይ ክርክሮችን እደምታካሂድ አስታውቀዋል። በተጨማሪም የአንድ ሀገር የበላይነትን ስለሚያስቀረው አዲሱ የዓለም ስርዓት ላይ ውይይቶች እንደሚካሄዱም ገልጸዋል።

የፀጥታው ምክር ቤት ፕሬዘዳንትንት በሩሲያ መያዝ ያስደገጣት ዩክሬን በበኩሏ፤ “የወሩ ምርጥ ቀልድ ነው” በማለት አጣጥላለች።

የዩክሬን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዲሜትሪ ኩሌባ፤ “ሩሲያ የፀጥታው ምክር ቤት ፕሬዘዳንት መሆን በዓለም የደህንነት ስርዓት ውስጥ የዓለም የፀጥታ እና የደህንነት ስርዓት ውስጥ የሆነ ችግር ያሳያል” ብለዋል።

“ሩሲያ የፀጥታው ምክር ቤት ፕሬዘዳንት መሆን ዓለም አቀፉን ማህበረሰብ በጥፊ እንደመምታት ነው” ሲሉም ሁኔታውን ገልጸውታል።

የተባሩት መንግስታት የፀጥታው ምክር ቤት አምስት ቋሚ እና 10 ተለዋዋጭ በድምሩ 15 አባላት ያሉት ሲሆን፤ ሁሉም አባላት የምክር ቤቱን የፕሬዝዳንትነት ስፍራ በየወሩ እየተቀባበሉ ይመራሉ።

ሩሲያ ለመጨረሻ ጊዜ የፀጥታው ምክር ቤት የሆነችው በፈረንጆቹ የካትቲ ወር 2022 ላይ ነበር።https://t.me/fana_televisions
1.0K viewsedited  13:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-02 16:33:11 የአማራና ደቡብ ክልሎች ለሠራተኛ ደመወዝ መክፈል መቸገራቸውን የፓርላማ አባላት ተናገሩ
በአማራና በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልሎች የሚገኙ የመንግሥት ተቋማት በበጀት እጥረት ምክንያት ለሠራተኞቻቸው ደመወዝ ለመክፈል መቸገራቸውን፣ የክልሎቹ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት አስታወቁ፡፡

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት በየካቲት ወር 2015 ዓ.ም.፣ ለአንድ ወር ወደ መረጣቸው ሕዝብ በመሄድ ስላደረጉት ውይይትና ምክክር በተመለከተ፣ ከመንግሥት አስፈጻሚና ሕግ ተርጓሚ አካላት ጋር ሰኞ መጋቢት 18 ቀን 2015 ዓ.ም. ውይይት አድርገዋል፡፡

በመድረኩ ከደቡብ ክልል የፓርላማ አባላት በሕዝብ ውይይት ወቅት የተነሱ ጥያቄዎቹን ለአስፈጻሚ አካላት ያቀረቡት አቶ መለስ መና የተባሉ የምክር ቤት አባል፣ ‹‹የደቡብ ክልል የበጀት ችግር ራስ ምታት ሆኖብናል፤›› ብለዋል፡፡

ለመንግሥት ሠራተኞች የሦስትና የአራት ወራት ደመወዝ ያልከፈሉ ተቋማት መኖራቸውን የገለጹት አቶ መለስ፣ በዚህም ምክንያት የመንግሥት አጠቃላይ አገልግሎት እየወደቀ ነው ብለዋል፡፡ በመሆኑም መንግሥት ተገቢውን ጥናት አድርጎ መልስ መስጠት ካልተቻለ፣ በዚህ የኑሮ ውድነት የመንግሥት ሠራተኛው ልጆቹን ትምህርት ቤት መላክ የማይችልበት ደረጃ ላይ ይደርሳል ብለዋል፡፡

አቶ መለስ ችግሩ በሁሉም የደቡብ ክልል አካባቢዎች የተከሰተ መሆኑን፣ ችግሩ ሊከሰት የቻለበት ዋነኛውና ትልቁ ምክንያት ክልሉ እስከ አሥር ዓመት የሚደርስ የማዳበሪያ ዕዳ ስለነበረበት ገንዘቡ ደመወዝ ከመከፈሉ ቀድሞ ዕዳ እየተከፈለበት በመሆኑ ነው ብለዋል፡፡ ለዚህ ችግር በተለየ ሁኔታ መፍትሔ ያሻዋል ያሉት አቶ መለስ፣ ችግሩ በዚሁ ከቀጠለ ግን የተቋማት አገልግሎቶች ሊቆሙ እንደሚችሉ ጠቁመዋል፡፡

በተመሳሳይ የአማራ ክልል የፓርላማ አባላትን ወክለው በውይይቱ ወቅት ጥያቄ ያቀረቡት ወ/ሮ ታለፍ ይታወቅ የተባሉ የምክር ቤት አባል፣ በአማራ ክልል የገጠመው የበጀት እጥረት ደመወዝ መክፈል አለመቻል ብቻ ሳይሆን ተቋማዊ ቁመና ይዘው ለመቀጠል የማይችሉበት ደረጃ ላይ ደርሰዋል ብለዋል፡፡

ወ/ሮ ታለፍ እንዳሉት፣ በአማራ ክልል ችግሩ በተለየ ሁኔታ የተከሰተባቸው አካባቢዎች በሰሜን ወሎ ዞን፣ ደቡብ ወሎ ዞን ከለላ፣ ወረኢሉ፣ አልቡኮ፣ ኩታበር ወረዳዎች፣ በምሥራቅ ጎጃም ዞን እነማይ፣ አነዳድ፣ ደጀን፣ ጎንቻ፣ ሲሶ፣ ስናን፣ ብቸና ከተማዎች፣ በማዕከላዊ ጎንደር በበሁሉም ወረዳዎች፣ በአዊ ዞን ጃዊ ወረዳ፣ በምዕራብ ጎጃም ዞን ደንበጫ ከተማ፣ በሰሜን ሸዋ ዞን ጣርማ በርና አንጎላላ ወረዳ ይገኙበታል፡፡

በአማራ ከልል የሚታየው ችግር የተለያየ ዓይነት ገጽታ እንዳለው የገለጹት ወ/ሮ ታለፍ፣ በመንግሥት የተመደበው የሥራ ማስኬጃ በጀት በዋጋ ንረት ሳቢያ ማብቃቃት እንዳልተቻለና አንዳንድ ወረዳዎች እንደ ወረዳ ለመቀጠል የማይችሉበት ደረጃ ላይ መድረሳቸውን ተናግረዋል፡፡

ከዚሁ የበጀት እጥረት ባለፈ በሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት የደረሰውን ውድመት መልሶ ለማቋቋም በሚል መንግሥት ከ20 ቢሊዮን ብር መድቤያለሁ ቢልም፣ ድጎማው እንደ ክልል ሲፈተሽ የተሠሩ ሥራዎች እነዚህ ናቸው የሚል በተጨባጭ የተገኘ ገንዘብ እንደሌለ የገለጹት የፓርላማ አባሏ፣ ይህም በመሠረታዊነት የሕዝብ ጥያቄ ተነስቶበታል ብለዋል፡፡ በሌላ በኩል ይገነባሉ ተብለው በዕቅዱ የነበሩ የመንገድ ፕሮጀክቶች ሕዝቡ በምን ምክንያት እንደተሰረዙ ሳያውቅ፣ ተሰርዞብናል በሚሉ በርካታ አካባቢዎች ጥያቄ መቅረቡን አስረድተዋል፡፡

የምክር ቤት አባላቱ በየካቲት 2015 ዓ.ም. ከመረጣቸው ሕዝብ ጋር ውይይት ለማድረግ በነበረው ዕቅድ በ327 የውክልና ቦታዎች ውይይት ሲደረግ፣ በ127 ያህሉ በተለያዩ ምክንያቶች ውይይት ማድረግ እንዳልቻሉ በመንግሥት ተጠሪ ሚኒስትሯ ወ/ሮ መሠረት ኃይሌ ተገልጿል፡፡ የተነሳ ሲሆን ውይይት ከተደረገባቸው የውክልና አካባቢዎች መካከል 69 ያህሉ በፀጥታ ምክንያት መሆኑን አክለዋል፡፡

በፀጥታ ምክንያት ውይይት ከተደረገባቸው የውክልና ቦታዎች መካከል ኦሮሚያ ክልል ይገኝበታል ተብሏል፡፡(ሪፖርተር) dani mengistu
1.0K views13:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-02 13:54:32
አትሌት አበጀ አያና የፓሪስ ማራቶንን አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 24፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) አትሌት አበጀ አያና ዛሬ የተካሄደውን የፓሪስ ማራቶን አሸነፈ፡፡

አትሌት አበጀ ውድድሩን ያሸነፈው 2 ሰዓት ከ7 ደቂቃ ከ14 ሰከንድ በሆነ ጊዜ በመግባት ነው።
1.2K views10:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-02 11:56:23
[ Album ]
ከለውጡ በኋላ የተገኘውን ድልና ስኬት ለማስቀጠል ያለመ የድጋፍ ሰልፍ በኦሮሚያ ክልል እየተካሄደ ነው !

ከለውጡ በኋላ የተገኘውን ድልና ስኬት ለማስቀጠል ያለመ የድጋፍ ሰልፍ በክልሉ በሁሉም ዞኖችና ከተማ አስተዳደሮች በመካሄድ ላይ ይገኛል። እየተካሄደ በሚገኘው የድጋፍ ሰልፍ ህዝቡ ድልና ስኬቶችን የሚያንጸባርቁ መልዕክቶችን እያስተላለፉ ነው።

የድጋፍ ሰልፉ የሚካሄደው ከመጋቢት 24 ቀን 2010 ዓ.ም ወዲህ በክልሉ የተመዘገቡ ድልና ስኬቶችን ጠብቆ ለማስቀጠል እንደሆነ ተገልጿል።
1.2K views08:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-02 11:52:31
[ Album ]
ሁለት አይነት ሰልፍ
የአምስት ዓመቱ ጉዞ ያስገኛቸውን አዎንታዊ ውጤት በመደገፍ በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ ከተሞች ሰልፎች እየተካሄዱ ሲሆን
በተቃራኒው በአማራ ክልል የተለያዩ ከተሞች የተቃውሞ ሰልፎችን እያስተናገዱ ይገኛል።
#ሰላም_ለኢትዮጵያ
1.2K views08:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-01 16:10:50
የክልል ልዩ ሀይል
የሌሎች ክልሎች ልዩ ኃይሎች ትጥቅ ይፈታሉ፤ የኦሮሚያ ልዩ ኃይል ግን ሁኔታዎች ስለማይፈቅዱ ትጥቅ አይፈታም ተብሏል።

ትናንት በተደረገው ስብሰባ የተሃድሶ ኮምሽኑ ኃላፊ ተሾመ ቶጋ በሰጠው መግለጫ የኦሮሚያ ልዩ ኃይል አሁን ላይ ትጥቅ እንደማይፈታ ገልፆአል። በዋነኛነት ትኩረት የተደረገው ሌሎቹ ላይ ሲሆን የኦሮሚያ "ሁኔታዎች ሲመቻቹ" ነው ተብሏል። "ሁኔታዎች አልተመቻቹም" ብለዋል።
Video:VOA
1.7K views13:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-01 14:41:51
የቀድሞ የህወሓት ቃል አቀባይ ፣ የአሁኑ የትግራይ ግዜያዊ አስተዳደር ፕረዝዳንት ጌታቸው ረዳ በአዲስአበባ ከተማ በጠቅላይ ሚንስቴር ዐቢይ አህመድ አማካኝነት እንዲገነባ የተረገውን አብሮሆት ቤተ መፅሐፍትን ጎብኝቷል።
1.7K views11:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ