Get Mystery Box with random crypto!

𝗙𝗔𝗡𝗔 𝗧𝗩 (ፋና)️ ️️

የቴሌግራም ቻናል አርማ fana_televisions — 𝗙𝗔𝗡𝗔 𝗧𝗩 (ፋና)️ ️️ 𝗙
የቴሌግራም ቻናል አርማ fana_televisions — 𝗙𝗔𝗡𝗔 𝗧𝗩 (ፋና)️ ️️
የሰርጥ አድራሻ: @fana_televisions
ምድቦች: ዜና
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 12.32K
የሰርጥ መግለጫ

This is FANA Media and Communication Corporate’s official Telegram channel.
For more updates please visit
https://t.me/fana_televisions
#ሼር 🙏 #በማድረግ_አጋርነታችሁን_አሳዩን
ሀሳብ ወይም መረጃ ለማቀበል @FANA_TV_BOT
https://t.me/joinchat/WC9-gid0rxB-S4Ac

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 92

2022-07-03 23:36:46 ደራ
በኦሮሚያ ክልል ደራ ወረዳ ባቡ ድሬ፣አሙማ ግደን፣ እሮብ ገበያ፣ ግንደ በርበሬ በሚባሉ ቀበሌዎች ላይ ዛሬ ጠዋት ኦነግ ሸኔ በአዲስ መልኩ ጥቃት ለማድረስ ሞክሯል። በዚህም ከሸኔ በኩል አንድ መካከለኛ የኦነግ ሸኔ አመራር እና 4 አባላቶቹ ተገድለዋል። በቁጥጥር ሥር የዋሉም አሉ።
ከዚህ ጎን ለጎን ከኦነግ ሸኔ ጋር አብረዋል የተባሉ 50 የሚደርሱ ሰዎች በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተደረገባቸው ነው። አሁንም ህዝቡ የሚያደርገውን የማጋለጥ ስራ አጠናክሮ እንዲቀጥል ከፀጥታ መዋቅሩ ጥሪ ቀርቧል።
መረጃዎችን ማምሻዬን በስልክ ያገኘሁት ነው።
ዘጋቢ አብይ እና ዳኒ መንግስቱ

ሀሳብ አስተያየት መረጃ ካሎት
@FANA_TV_BOT ያድርሱን
ቻናላችንን ይቀላቀሉ
@fana_televisions
@fana_televisions
3.6K viewsedited  20:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-03 17:41:44 የዝንጀሮ ፈንጣጣ” እስካሁን በኢትዮጵያ አለመከሰቱን ጤና ሚኒስቴር ገለፀ

“የዝንጀሮ ፈንጣጣ” በኢትዮጵያ ተከስቶ ሁለት ሰዎች ተለይተዋል (ኳረንቲን ገብተዋል) የሚል መረጃ በሪፖርተር ጋዜጣ ወጥቶ በማህበራዊ ሚዲያ እየተሰራጨ መሆኑን የጠቀሰው ሚኒስቴሩ በሽታው በሌሎች ሀገራት ቢከሰትም በኢትዮጵያ እስካሁን የተያዘም ሆነ የተለየ ሰው አለመኖሩን አስታውቋል፡፡
ኃላፊነት የሚሰማቸው የሚዲያ ተቋማት ይህን መሰል ያልተረጋገጠና በሚመለከተው አካል ያልቀረበ መረጃን ከማሰራጨት እንዲቆጠቡም ነው ሚኒስቴሩ አሳስቧል፡፡

ወቅታዊ የጤና መረጃዎችን እንዲሁም የማህበረሰቡ የጤና ስጋት የሚሆኑ ወረርሽኞችን በተመለከተ ትክክለኛ መረጃ ከጤና ሚኒስቴር እና የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ብቻ ማግኘት እንደሚገባም ነው ሚኒስቴሩ ያሳሰበው፡፡

ሀሳብ  አስተያየት መረጃ  ካሎት @FANA_TV_BOT ያድርሱን
ቻናላችንን ይቀላቀሉ
@fana_televisions
@fana_televisions
3.8K views14:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-03 17:40:02
ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ኢትዮጵያን በውክልና ጦርነት ለማዳከም የሚፈልጉ ኃይሎችን ሴራ ሕዝቡ ሊገነዘብ ይገባል አሉ

ኢትዮጵያን በውክልና ጦርነት ለማዳከም የሚፈልጉ ኃይሎችን ሴራ ሕዝቡ ሊገነዘበው እንደሚገባ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ አሳሰቡ።

የ8ኛ ዕዝ በግዳጅ አፈፃፀማቸው ብልጫ ላሳዩ የሠራዊት ክፍሎችና አባላት የሜዳይ እና ዕውቅና መስጠት ሥነ-ሥርዓት አከናውኗል።

በመርኃ ግብሩ ላይ ሽልማት በመስጠት የሥራ መመሪያ ንግግር ያደረጉት የጥቁር አንበሳ ጀግና ከፍተኛ ሜዳይ ተሸላሚውና የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ አሸባሪው ሕወሓት ባልዋለበት ገድል ራሱን የሚያፅናና ውጊያን ሲያንቆለጳጵስ የሚውል ኃይል መሆኑን ገልፀው በበርካታ አውደ ውጊያዎች የደረሰበትን ሽንፈትና ኪሳራ ግን ማንሳት አይፈልግም ብለዋል።

በአሁኑ ሰዓትም በርካታ የውጭ ኃይሎች ሀገራችንን ለማዳከም ሰፊ የውክልና ጦርነት አውዶች መክፈታቸውን አንስተው የነዚህን ኃይሎች ሴራ ሕዝባችን በመገንዘብ ሊያከሽፈው ይገባል ብለዋል።

8ኛ ዕዝ አሸባሪውን የትሕነግ ኃይል ለመደምሰስ በታቀደው ዘመቻ ኅብረ ብሔራዊ አንድነት ላይ የሰራዊታችን ጠንካራ ክንድ በመሆን በቡድኑ ላይ ከፍተኛ የመመከትና የመደምሰስ ሥራውን ሰርቷል። የዕዙ የሰራዊት አመራርና አባላት በፈፀሙት ገድል ሀገር ከተደቀነባት የመፍረስ አደጋ መታደግ በመቻላችሁ ኩራት ሊሰማችሁ ይገባል ማለታቸውን ከመከላከያ ሰራዊት ያገኘነው መረጃ አመላክቷል፡፡

ሀሳብ  አስተያየት መረጃ  ካሎት @FANA_TV_BOT ያድርሱን
ቻናላችንን ይቀላቀሉ
@fana_televisions
@fana_televisions
3.7K views14:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-03 17:40:01 ከትግራይ ልዩ ኃይል የመጡ የሽብር ቡድኑ አባላት በቁጥጥር ሥር ዋሉ

ከትግራይ ልዩ ኃይል የመጡ የሽብር ቡድኑ ሁለት አባላት አቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ቱሉ ድምቱ አካባቢ 11:00 ሰዓት ላይ በቁጥጥር ሥር እንዲውሉ ተደርጓል።

በቁጥጥር ሥር የዋሉት
1ኛ. ዘመን ገ/እግዚአብሔር (የጥበቃ መምሪያ አባል የነበረ የፈንጂ ባለሞያ)
2 ኛ. ገ/ኪዳን ገ/ጻድቅ የልዩ ኃይሉ አባል ናቸው።የሽብር ቡድኑ አባላት ላይ ከፌደራል ፓሊስ ጋር በመሆን ምርመራ ተጀምሯል። ውጤቱን በቀጠይ እናሳዉቃለንም ብሏል።
ሀሳብ  አስተያየት መረጃ  ካሎት @FANA_TV_BOT ያድርሱን
ቻናላችንን ይቀላቀሉ
@fana_televisions
@fana_televisions
3.5K views14:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-02 15:26:59
4.0K views12:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ