Get Mystery Box with random crypto!

𝗙𝗔𝗡𝗔 𝗧𝗩 (ፋና)️ ️️

የቴሌግራም ቻናል አርማ fana_televisions — 𝗙𝗔𝗡𝗔 𝗧𝗩 (ፋና)️ ️️ 𝗙
የቴሌግራም ቻናል አርማ fana_televisions — 𝗙𝗔𝗡𝗔 𝗧𝗩 (ፋና)️ ️️
የሰርጥ አድራሻ: @fana_televisions
ምድቦች: ዜና
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 12.32K
የሰርጥ መግለጫ

This is FANA Media and Communication Corporate’s official Telegram channel.
For more updates please visit
https://t.me/fana_televisions
#ሼር 🙏 #በማድረግ_አጋርነታችሁን_አሳዩን
ሀሳብ ወይም መረጃ ለማቀበል @FANA_TV_BOT
https://t.me/joinchat/WC9-gid0rxB-S4Ac

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 91

2022-07-19 09:27:05
በአማራ ክልል በኦሮሞ ልዩ ዞን የጅሌ ጥሙጋ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ የነበሩት አቶ አህመድ መሃመድ ከስልጣናቸው ተነስተዋል።ይሄ ሰውዬ በተደጋጋሚ በቪድዮ የተደገፈ መረጃ ተገኝቶበታል። ልዩ ሀይሉ ከጀርባ እንዲመታ አስተባብሯል ተብሏል።
የሰሞኑን ግጭት ላይ ተሳትፈዋል በሚል እርምጃ የተወሰደባቸው የጅሌ ጥሙጋ ወረዳ አመራሮች የሚከተሉት ናቸው።
1.አቶ አህመድ መሀመድ አብደላ....የወረዳ ዋና አስተዳዳሪ
2.አቶ አሊ መሀመድ አሊ .....የወረዳ ም/ዋና አስተዳዳሪ እና የትምህርት ጽ/ቤት ኀላፊ
3.አቶ ኡመር አሊዮ ኡመር .....የወረዳው ብልፅግ ና ፅ/ቤት ኀላፊ
4.ወ/ሮ ዘሀራ አብዱ ....የወረዳው የብልፅግና ፅ/ቤት የአደረጃጀት ኀላፊ
5.አቶ አሊ ሀሰን መሀመድ የወረዳው የሰላም እና የደህንነት ፅ/ቤት ኀላፊ የነበሩ 5 ከፍተኛ የወረዳው አመራሮች ናቸው።

ሀሳብ  አስተያየት መረጃ  ካሎት @FANA_TV_BOT ያድርሱን
ቻናላችንን ይቀላቀሉ
@fana_televisions
@fana_televisions
2.1K views06:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-13 07:38:57 ጥቆማ+ሼር
በዚህ ዘመን መረጃ ህይወት ነው፣ ስለዚህ እውነተኛ፣ ሚዛናዊ እና ፈጣን መረጃ ለማግኘት የዚህን ትክክለኛ የቴሌግራም ሊንክ ለሌሎች ወዳጅ ዘመድዎ ያጋሩ።
የውሸት አካውንት የከፈቱ ስላሉ ለሌሎች ጥቆማ ሲሰጡ ትክክለኛውን የፋና ቲቪ ቴሌግራም ገፅ ሊንክ ይጠቀሙ።
ትክክለኛው የቴሌግራም ቻናሌ ሊንክ ከስር ያለው ነው

https://t.me/joinchat/WC9-gid0rxB-S4Ac
5.4K views04:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-13 07:34:43
#መረጃ
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ለአንድ አመት ያህል በጉሙዝ ታጣቂዎች ቁጥጥር ስር የቆየችው ምዥጋ ወረዳ በመከላከያ ሰራዊት ቁጥጥር ስር ውላለች!!! መከላከያ ሰራዊቱ የተቀናጀ ሥራ እየሰራ መሆኑን ለማወቅ ችያለሁ።
ሰላም እደሩልኝ
ነገ ጠዋት ያልተሰሙ በርካታ መረጃዎች አሰባስቤ የምመለስ ይሆናል።


ሀሳብ  አስተያየት መረጃ  ካሎት @FANA_TV_BOT ያድርሱን
ቻናላችንን ይቀላቀሉ
@fana_televisions
@fana_televisions
4.5K views04:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-08 21:42:58 #AddisAbaba

ነገ የሚዘጉ መንገዶች !

የዒድ አል-አድሃ በዓል የሶላት ፕሮግራም ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ የትራፊክ መጨናነቅ እንዳይፈጠር ፡-

- ከቦሌ አየር መንገድ ፣ በሚሊኒዬም አዳራሽ ወደ ለገሃር የሚወስደው መንገድ ደንበል ሲቲ ሴንተር ወይም ኦሎምፒያ አደባባይ አካባቢ

- ከመገናኛ ፣ በሃያ ሁለት ወደ ለገሃር እንዲሁም ከቦሌ መድሃኔአለም ፣ በአትላስ ሆቴል ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ኡራኤል ቤተ-ክርስቲያን አካባቢ

- ከአራት ኪሎ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ባሻ ወልዴ ችሎት ወይም ፓርላማ መብራት

- ከፒያሣ ወደ ለገሃር የሚወስደው መንገድ ቸርችል ጎዳና ቴዎድሮስ አደባባይ

- ከተክለ ኃይማኖት ፣ በሜትሮሎጂ ወደ ለገሃር የሚወስደው መንገድ ሜትሮሎጂ መስሪያ ቤት አካባቢ

- ከተክለ ኃይማኖት ፣ በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል የሚወስደው መንገድ ጥቁር አንበሳ የኋላ በር አካባቢ

- ከሲኒማ ራስ በጎላ ሚካኤል ወደ ለገሃር የሚወስደው መንገድ ጎላ ሚካኤል መስቀለኛ

- ከጌጃ ሰፈር ፣ ጤና ጥበቃ፣ ብሄራዊ ቲያትር የሚወስደው መንገድ ጎማ ቁጠባ

- ከባሻ ወልዴ ችሎት ፣ በኦርማ ጋራዥ ወደ ፍል ውሃ መስኪድ የሚወስደው መንገድ ንግድ ማተሚያ ቤት

- ከጎፋ ፣ በቂርቆስ ቤተ-ክርስቲያን ወደ ለገሃር አዲሱ መንገድ የሚወስደው መንገድ ቂርቆስ ቤተ ክርስቲያን መስቀለኛው ላይ

- ከጦር ኃይሎች ፣ ልደታ ፣ ፖሊስ ሆስፒታል ሜክሲኮ አደባባይ

- ከሳሪስ በጎተራ ወደ መስቀል አደባባይ የቀድሞ አራተኛ ክፍለ ጦር ይለፍ ለሌላቸው ተሽከርካሪዎች ከለሊቱ 10፡00 ሰዓት ጀምሮ ዝግጅቱ እስከሚጠናቀቅ መንገዶቹ ዝግ ይሆናሉ፡፡ ከሳሪስ በጎተራ ወደ ለገሃር የሚመጡ ከባድ ተሽከርካሪዎችም ከአጎና ሲኒማ ማለፍ እንደማይችሉ ተገልጿል።

(አዲስ አበባ ፖሊስ)

ሀሳብ  አስተያየት መረጃ  ካሎት @FANA_TV_BOT ያድርሱን
ቻናላችንን ይቀላቀሉ
@fana_televisions
@fana_televisions

Reporter .FIRAOL
6.8K views18:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-05 09:18:44 ምክር ቤቱ አሸባሪው የሸኔ ቡድን በምእራብ ወለጋ በንጹሀን ዜጎች ላይ ያደረሰውን ጥቃት በፅኑ አወገዘ

አሸባሪው የሸኔ ቡድን በጸጥታ ሀይሎች በከፍተኛ ሁኔታ ጥቃት እየደረሰበት መሆኑን ተከትሎ ከጥቃቱ በመሸሽም በምእራብ ወለጋ ንጹሀን ዜጎች ላይ ያደረሰውን ጉዳት የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ኮንኗል።ቡድኑ በቄለም ወለጋ ዞን ውስጥ የሚገኙ ንጹሀን ዜጎች ላይ የፈጸመውን ጭፍጨፋም በእጅጉ የሚወገዝ መሆኑን አስታውቋል።

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በማህበራዊ ትስስር ገጹ ማምሻውን ባወጣው መግለጫ "በዜጎቻችን ላይ በደረሰው ስቃይ እና መከራ እያዘን ይህንን አሸባሪ ቡድን ለማስወገድ መላው ህዝባችን በተለይም የአካባቢው ማህበረሰብ ከጸጥታ ሀይላችን ጋር በመተባበር እስከመጨረሻው እንድናስወግደው" ሲልም ጥሪውን አቅርቧል።

ሀሳብ  አስተያየት መረጃ  ካሎት @FANA_TV_BOT ያድርሱን
ቻናላችንን ይቀላቀሉ
@fana_televisions
@fana_televisions
7.5K views06:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-04 22:09:34
በቄለም ወለጋ ሀዋገላን ወረዳ የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች ባደረሱት ጥቃት በርካታ ንጹሀን መገደላቸውን ተነገረ

በቄለም ወለጋ ዞን ሀዋ ገለን ወረዳ ፤ ለምለም ቀበሌ ዉስጥ መንደር 20 ተብሎ በሚጠራዉ አካባቢ በዛሬዉ እለት የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች በከፈቱት ጥቃት በርካታ ንጹሀን ዜጎች ህይወት እንዳለፈ ተነግሯል። በጥቃቱ በርካታ ህጻናት እና እናቶች መገደላቸዉንም የአካባቢው ነዋሪዎች ገልጸዋል። በጥቃቱ ምን ያህል ሰዎች ህይወታቸዉ እንዳለፈ በዉል ባይታወቅም ቁጥራቸዉ ከፍተኛ የሆነ ንጹሀን ሲገደሉ በርካታ ሰዎች የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል።

ጥቃቱን እስካሁን የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድም አረጋግጠዋል። " ጨፍጫፊዎቹ የሸኔ ቡድን " ናቸው ብለዋል። ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ፤ " የጸጥታ አካላት ከሚያደርሱበት ዱላ የፈረጠጠው የሸኔ ቡድን በምዕራብ ወለጋ በዜጎች ላይ አደጋ እያደረሰ በመሸሽ ላይ ነው " ብለዋል።

“በዜጎቻችን ላይ በደረሰው መከራ እያዘንን ይሄንን አሸባሪ ቡድን እስከመጨረሻው ተከታትለን ከሕዝባችን ጋር እናስወግደዋለን” ሲሉም ገልጸዋል


ሀሳብ  አስተያየት መረጃ  ካሎት @FANA_TV_BOT ያድርሱን
ቻናላችንን ይቀላቀሉ
@fana_televisions
@fana_televisions
6.0K views19:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-04 18:48:41 በማደያዎች የሚታዩ ረጃጅም ሰልፎችን ለማስቀረት በቀን ከ10 ሚሊዮን ሊትር በላይ ነዳጅ እየገባ ነው

የነዳጅ እና ኢነርጂ ቁጥጥር ባለስልጣን

ነዳጅ ለመቅዳት በማደያዎች የሚታዩ ረጃጅም ሰልፎችን ለማስቀረት በቀን ከ10 ሚሊዮን ሊትር በላይ ነዳጅ ከትናንት በስቲያ ጀምሮ ወደ አገር ውስጥ እንዲገባ እየተደረገ መሆኑን የነዳጅ እና ኢነርጂ ቁጥጥር ባለስልጣን አስታወቀ።

በአቅርቦት በኩል ክፍተት እንዳይኖርም ቀድሞ በቀን ይቀርብ ከነበረው 9 ሚሊዮን ሊትር ወደ 10 ሚሊዮን ሊትር ነዳጅ ማሳደጉን የባለስልጣኑ የነዳጅ ስታንዳርድ ጥራት ዳይሬክተር አቶ ለሜሳ ቱሉ በተለይ ለኢቢሲ ሳይበር ተናግረዋል።

ነዳጅ የጫኑ ቦቴ ተሽከርካሪዎች መንገድ ላይ መዘግየት እንዳይፈጠር እና ስርጭቱ ላይ ችግር እንዳይኖር ለማድረግ ኮሚቴ ተዋቅሮ በዘላቂነት ለመፍታት እየተሰራ ነው ብለዋል።

ባለፈው ሳምንት እንደሀገር 200 ነዳጅ የጫኑ ቦቴዎች ከጂቡቲ ተነስተው 18ቱ ሞጆ ወደብ መድረሳቸውን እና የተቀሩት ላይ አስተዳደራዊ እና ህጋዊ እርምጃ እንደተወሰዳባቸው አቶ ለሜሳ ገልጸዋል።

ሀሳብ  አስተያየት መረጃ  ካሎት @FANA_TV_BOT ያድርሱን
ቻናላችንን ይቀላቀሉ
@fana_televisions
@fana_televisions
5.0K views15:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-04 18:46:28
4.3K views15:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-03 23:38:34
#ነዳጅ
የአዲስ አበባ ከተማ ንግድ ቢሮ ከመንግስት የተሰጠውን መመሪያና ደንብ የጣሱ 8 የነዳጅ ቦቴዎችን ወረሰ

የአዲስ አበባ ከተማ ንግድ ቢሮ ስምንት የነዳጅ ቦቴዎችን መውረሱን አስታወቀ፡፡

ሆን ብለው የነዳጅ እጥረት እንዲከሰትና ከመንግስት የተሰጠውን መመሪያና ደንብ ችላ በማለት ከሕግ ውጪ ነዳጅ የጫኑ ቦቴዎች ወደ ከተማ እንዳይገቡ ያደረጉ ስምንት የነዳጅ ካምፓኒዎች ቦቴዎችን በዛሬው እለት በፀጥታ ሀይሎችና በህብረተሰቡ ጥቆማ በውረስ በነዳጅ ማደያዎች በኩል እንዲከፋፈል ማድረጉን ቢሮው አስታውቀዋል።

አቶ መስፍን አሰፋ የንግድ ቢሮ ምክትል ኃላፊ ይህንን አስመልክተው በሰጡት መግለጫ÷ ስምንት የነዳጅ ቦቴዎች ተደብቀው የተያዙት በፀጥታ ሀይሎችና በህብረተሰቡ ትብብር መሆኑን ገልጸዋል፡፡
ሕግ አክብረው በማይሰሩና በትክክል ስራቸውን በማይወጡ የነዳጅ ካምፓኒዎች ላይ እርምጃው ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ሃላፊው ተናግረዋል።
=========================

ዘጋቢ አብይ እና ዳኒ መንግስቱ

ሀሳብ አስተያየት መረጃ ካሎት @FANA_TV_BOT ያድርሱን
ቻናላችንን ይቀላቀሉ
@fana_televisions
@fana_televisions
4.3K viewsedited  20:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-03 23:38:04
#Update
#ayu #Ethiopia
የሱዳን መንገዶች በዚህ መልኩ ተከርችመው ውለዋል!
ቀጣዩ ዋናው ግዙፍ ተቃውሞ ከነገ ወዲያ ሰኔ 28 (July 5) እንደሚደረግ የታወቀ ሲሆን እስከዛው ግን ቀን በዚህ መልኩ እና በምሽት ተቃውሞ እንደሚካሄድ ታውቋል

ዘጋቢ አብይ እና ዳኒ መንግስቱ

ሀሳብ አስተያየት መረጃ ካሎት
@FANA_TV_BOT ያድርሱን
ቻናላችንን ይቀላቀሉ
@fana_televisions
@fana_televisions
3.7K viewsedited  20:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ