Get Mystery Box with random crypto!

በማደያዎች የሚታዩ ረጃጅም ሰልፎችን ለማስቀረት በቀን ከ10 ሚሊዮን ሊትር በላይ ነዳጅ እየገባ ነው | 𝗙𝗔𝗡𝗔 𝗧𝗩 (ፋና)️ ️️

በማደያዎች የሚታዩ ረጃጅም ሰልፎችን ለማስቀረት በቀን ከ10 ሚሊዮን ሊትር በላይ ነዳጅ እየገባ ነው

የነዳጅ እና ኢነርጂ ቁጥጥር ባለስልጣን

ነዳጅ ለመቅዳት በማደያዎች የሚታዩ ረጃጅም ሰልፎችን ለማስቀረት በቀን ከ10 ሚሊዮን ሊትር በላይ ነዳጅ ከትናንት በስቲያ ጀምሮ ወደ አገር ውስጥ እንዲገባ እየተደረገ መሆኑን የነዳጅ እና ኢነርጂ ቁጥጥር ባለስልጣን አስታወቀ።

በአቅርቦት በኩል ክፍተት እንዳይኖርም ቀድሞ በቀን ይቀርብ ከነበረው 9 ሚሊዮን ሊትር ወደ 10 ሚሊዮን ሊትር ነዳጅ ማሳደጉን የባለስልጣኑ የነዳጅ ስታንዳርድ ጥራት ዳይሬክተር አቶ ለሜሳ ቱሉ በተለይ ለኢቢሲ ሳይበር ተናግረዋል።

ነዳጅ የጫኑ ቦቴ ተሽከርካሪዎች መንገድ ላይ መዘግየት እንዳይፈጠር እና ስርጭቱ ላይ ችግር እንዳይኖር ለማድረግ ኮሚቴ ተዋቅሮ በዘላቂነት ለመፍታት እየተሰራ ነው ብለዋል።

ባለፈው ሳምንት እንደሀገር 200 ነዳጅ የጫኑ ቦቴዎች ከጂቡቲ ተነስተው 18ቱ ሞጆ ወደብ መድረሳቸውን እና የተቀሩት ላይ አስተዳደራዊ እና ህጋዊ እርምጃ እንደተወሰዳባቸው አቶ ለሜሳ ገልጸዋል።

ሀሳብ  አስተያየት መረጃ  ካሎት @FANA_TV_BOT ያድርሱን
ቻናላችንን ይቀላቀሉ
@fana_televisions
@fana_televisions