Get Mystery Box with random crypto!

𝗙𝗔𝗡𝗔 𝗧𝗩 (ፋና)️ ️️

የቴሌግራም ቻናል አርማ fana_televisions — 𝗙𝗔𝗡𝗔 𝗧𝗩 (ፋና)️ ️️ 𝗙
የቴሌግራም ቻናል አርማ fana_televisions — 𝗙𝗔𝗡𝗔 𝗧𝗩 (ፋና)️ ️️
የሰርጥ አድራሻ: @fana_televisions
ምድቦች: ዜና
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 12.32K
የሰርጥ መግለጫ

This is FANA Media and Communication Corporate’s official Telegram channel.
For more updates please visit
https://t.me/fana_televisions
#ሼር 🙏 #በማድረግ_አጋርነታችሁን_አሳዩን
ሀሳብ ወይም መረጃ ለማቀበል @FANA_TV_BOT
https://t.me/joinchat/WC9-gid0rxB-S4Ac

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 4

2023-05-15 14:50:26
ይደመጥ
2.4K viewsedited  11:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-15 14:48:20
#ኮንስትራክሽን

አስገዳጁ ረቂቅ አዋጅ . . .

የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ማኔጅመንት ኢንስቲትዩት ፤ ትላልቅ #ተቋራጮች ከአነስተኛ የግንባታ ተቋራጮች ጋር በጥምረት እንዲሠሩ #የሚያስገድድ ረቂቅ አዋጅ መዘጋጀቱን አስታውቋል።

ረቂቁ በከተማና መሰረተ-ልማት ሚኒስቴር ቀርቦ እንደሚገመገም ተገልጿል።

ረቂቁ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት #እንዲጸድቅ ሲደረግ በኮንስትራክሽን ዘርፉ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለማረም በአገሪቱ የሚገኙ ትላልቅና ዋና ዋና ተቋራጮች ከአነስተኛ ትናንሽ ተቋራጮች በጥምረት እንዲሠሩ ዕድሉን የሚፈጥር ነው ተብሏል።

ረቂቅ ህጉን #በአስገዳጅነት እንዲዘጋጅ የተደረገው አነስተኛ አቅም ያላቸው ተቋራጮች ሰፊ ልምድና አቅም ካላቸው ተቋራጮች ጋር በመሥራት ልምድ እንዲያገኙና ክህሎታቸውን እንዲያሳድጉ በማሰብ ነው ተብሏል።

አነስተኛ ደረጃ ያላቸው ተቋራጮች ያልተገባ ተግባር ሲፈጽሙ ተጠያቂ እንዲሆኑ እና #ክፍያ ላይም ምንም ዓይነት ችግር እንዳይገጥማቸው የሚያስችል ሕግ መሆኑ ተገልጿል።

አዋጁን በማርቀቅ ሂደት ፦
- የሕንፃ አማካሪ ድርጅቶች፤
- የሕንፃ ተቋራጭ ማህበራት፤
- በአገሪቱ ያሉ ዩኒቨርሲቲዎች፤
- ፕሮጀክት ያላቸው አካላት፤
- የገንዘብ ሚኒስቴር፤
- የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር
- በኮንስትራክሽን ዘርፉ የሚሠሩ የተለያዩ ባለድርሻ አካላት እንደተሳተፉበት ተመላክቷል።

የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ማኔጅመንት ኢንስቲትዩት ፤ አነስተኛ ደረጃ ያላቸው የግንባታ ተቋራጮች እራሳቸውን ብቁ አድርገው መንግሥት በሚያሰማራቸው የተለያዩ ፕሮጀክቶች ላይ ድርሻ ይዘው ለመሥራት ከወዲሁ ዝግጅት ያድርጉ ብሏል።
2.2K views11:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-15 14:46:47
Inbox ከባህርዳር
ሰላም fana በአሁኑ ሰዓት የባህርዳር ዙሪያ አርሶ አደር በርዕሰ መስተዳደር ጽ/ቤት ፊት ለፊት ሰላማዊ ሰልፍ በማድረግ ላይ ይገኛሉ። የፀጥታ አካላት ሰልፈኞቹን ለመበተን ጥረት እያደረጉ ነው። የሰልፉ ዓላማ መጪው የእርሻ እና የአዝመራ ወቅት በመሆኑ የግብርና አቅርቦት እንዲሟላላቸው ለመጠየቅ ያለመ ነው። በክልሉ አሁንም የማዳበሪያ እጥረት እንዳለ እና ማዳበሪያ በነጋዴዎች እጅ መግባቱ ዋጋው በጣም እንደተወደደባቸው ይገልፃሉ።
ለዚህ መረጃ ማጠናከሪያ ይሆናችሁ ዘንድ ይህን መረጃ አንብቡት
https://t.me/ayuzehabeshaofficial/11074
1.8K views11:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-15 11:57:29 ከሐምሌ ወር ጀምሮ በመላ አገሪቱ የመብራት አገልግሎት ክፍያ በዲጂታል እንደሚከናወን ተገለጸ
በአዲስ አበባ የክፍያ ሥርዓቱ ከዚህ ወር ጀምሮ የሚፈፀም ይሆናል። ከሐምሌ ወር ጀምሮ በአገር አቀፍ ደረጃ የመብራት አገልግሎት ክፍያ በዲጂታል ሥርዓት እንደሚከናወን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አስታወቀ፡፡ በአዲስ አበባ ከዚህ ወር ጀምሮ የድህረ መብራት ክፍያ ሙሉ በሙሉ በዲጂታል ይሆናል ተብሏል፡፡

እስካሁን 30 በመቶ ብቻ የሚሆን ተገልጋይ የድህረ ክፍያ በዲጂታል የክፍያ አማራጭ የሚከፍል ሲሆን፤ በአዲስ አበባ ከዚህ ወር ጀምሮ ሙሉ በሙሉ የድህረ ክፍያ አገልግሎት ተጠቃሚዎች በዲጂታል እንዲከፍሉ እንደሚደረግ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር መላኩ ታዬ ለኢፕድ ገልጸዋል።

በቀጣይም በመላ አገሪቱ የሚገኙ አገልግሎት መስጫዎች ከተያዘው ዓመት ሐምሌ አንድ ጀምሮ ድህረ ክፍያ አገልግሎቱን ሙሉ በሙሉ በዲጂታል አማራጭ እንዲያደርጉ ይደረጋል ያሉት መላኩ፤ አብዛኞቹ ደንበኞች የድህረ ክፍያ ተጠቃሚዎች መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አገልግሎቱን ቀልጣፋ፣ ፈጣን እና ቀላል ለማድረግ የኢትየጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የተለያዩ አማራጮችን ተግባራዊ ማድረግ መጀመሩን ያስታወቀ ሲሆን፤ ከአማራጮቹ መካከልም ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጋር በመሆን ያስጀመረው በሲቢኢ ብር፣ በሞባይል ባንኪንግ፣ ዳይሬክት ዴቢት እንዲሁም ቴሌ ብር ዋንኞቹ ናቸው ብሏል፡፡

በዚህም መሰረት ደንበኞች የተጠቀሙበትን የኤሌክትሪክ ፍጆታ ሂሳብ በተዘረጉ የክፍያ አማራጮች (በሞባይል ባንኪንክ፣ በሲቢኢ ብር እና ቴሌ ብር) በመጠቀም ክፍያ መፈጸም እንደሚችሉም አገልግሎቱ ገልጿል።
2.1K views08:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-12 22:01:47
[ Album ]
#Eritrea
ኤርትራ ከኢትዮጵያ የተገነጠለችበትን 32ኛ ዓመት በዓል እያከበረች ነው።
2.8K views19:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-29 12:08:19 አጭር ቁምነገር….!

….ከእለታት አንድ ቀን ንጉስ አንበሳ ቀበሮን ይጠራውና << እጅግ በጣም እርቦኛል ፤ በአስቸኳይ  የምበላው ካላመጣህልኝ ፥  አንተን ነው ቀረጣጥፌ የምበላህ! >> ይለዋል። ቀበሮም ተደናግጦ ለአንበሳው ምግብ ፍለጋ ሲሄድ  ከአህያ ጋር ይገናኛል፡፡

ይሄኔ አህያን የጦስ ዶሮ ለማድረግ የማታለያ ሀሳብ የመጣለት ቀበሮ ፥ << አያ አህያ! ስፈልግህ አገኘሁህ፡፡ ንጉሳችን አንበሳ አንተን ንጉስ ሊያደርግህ ይፈልጋልና በአስቸኳይ  እንሂድ ! >> ብሎ በማሳመን አስከትሎት ይሄዳል፡፡

የተራበው አንበሳ አህያው ከአጠገቡ ሲደርስ ፥ ጊዜ ሳያጠፋ ተንደርድሮ ጆሮውን ግሽልጥ አድርጎ ይበላዋል፡፡ ይሄኔ አህያ ደሙን እያዘራ ሲሮጥ ከቀበሮ ጋር ይገናኛሉ፡፡

<< አታለልከኝ አይደል ! ልታስበላኝ ነበር የጠራኸኝ ! >> ይለዋል፡፡

<< ኧረ በፍፁም አላታለልኩህም አያ አህያ ፤ ጆሮህን የበላህኮ ስትነግስ ዘውዱን ለመድፋት አንዳያስቸግርህ ብሎ ነው !  በል አሁን እንመለስ በቶሎ ..>> ይልና አሳምኖ ይመልሰዋል፡፡

ድጋሜ አህያው ከአንበሳው ፊት ሲደርስ ተንደርድሮ ጭራውን ቆርጦ ይበላዋል፡፡ አሁንም አህያው ደሙን እያዘራ ሲሄድ ከደላላው ቀበሮ ጋር ይገናኛሉ፡፡

<< አያ ቀበሮ ምን በድዬህ ነው ግን ፥ ያታለልከኝ ? አሁንም ጭራዬን በላኝኮ!>>  ! >> ይለዋል፡፡

<< ኧረ በፍፁም አላታለልኩህም፡፡ ምነው አያ አህያ ? ለአንተው በደከምኩ ፤ አያ አንበሳ ጭራህን የቆረጠውኮ ፥ ከነገስክ በኃላ ዙፋኑ ላይ ስትቀመጥ እንዳያስቸግርህ አስቦ ነው፡፡ በል አሁን እንመለስ ..! >> ይልና በድጋሜ አሳምኖ ይወስደዋል፡፡

ይሄኔ አንበሳው አህያውን ደቋቁሶ ገደለው፡፡ ወደቀበሮውም ዘወር ብሎ << አህያውን አሳምነህ በማምጣትህ ጥሩ ሰርተሃል፡፡ በል አሁን ደግሞ አህያውን ገነጣጥለህ   ቆዳውን ፥ ጭንቅላቱን ፣ ልቡን ፤ ሳንባውና ጉበቱን ብቻ ለይተህ አምጣልኝ! >> ሲል አዘዘው፡፡

ቀበሮ የታዘዘውን ፈፅሞ ለአንበሳው ይዞ ቀረበ፡፡ ነገርግን ይዞ ከመጣው ስጋ ውስጥ ጭንቅላቱን  ስለበላው ሊገኝ አልቻለም፡፡ ይሄኔ አንበሳው በንዴት ጦፈ፡፡ << ጭንቅላቱን የት አባክ አስገብተኸው ነው ? >> ሲልም አፈጠጠበት፡፡

ቀበሮም የዋዛ አልነበረም << ጌታዬ! ጭንቅላት እኮ ቀድሞውኑ አልነበረውም፡፡ ጭንቅላት ቢኖረውማ  ፥ ጆሮና ጅራቱን ከቆረጥከው በኃላ ዳግም ተመልሶ ወደአንተ ጋር ይመጣ ነበርን ? >> ብሎ   በብልሃት በማሳመን ራሱን ከሞት አዳነ ይባላል፡፡

የሠው ልጅም በህይወት መስመሩ ለአንድ እና ለሁለት ጊዜ ሲሳሳት እንዲታረም ከሰጠችው እድል መማር ካልቻለ ፥  ከውድቀቱ በኃላ የመማር  እድሉ ጠባብ ነው
784 views09:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-27 21:23:42 ተጨማሪ
ከአቶ ግርማ የሺጥላ በተጨማሪ በመኪናው ውስጥ ከነበሩት ጠባቂዎቻቸው እና ቤተሰቦቻቸው ውስጥ አራት ሰዎች ሞተዋል። ቤተሰቦቻቸውን ጭመር ነበር ወደ መሃልሜዳ ይዘው የሄዱት። ሲመለሱ ነው ጓሳ በተባለ አካባቢ ጥቃቱ የተፈፀመው(አዩዘሀበሻ)። ነፍስ ይማር ሀሳብ አስተያየት መረጃ ካሎት @FANA_TV_BOT ያድርሱን
ቻናላችንን ይቀላቀሉ
@fana_televisions
@fana_televisions
1.8K viewsedited  18:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-27 21:21:23
ሰበር አሳዛኝ ዜና
የአማራ ክልል የብልፅግና ሃላፊ እና ስራ አስፈፃሚ አባል አቶ ግርማ የሺጥላ ከመሃልሜዳ ሲመጡ ጓሳ በተባለ አካባቢ በተተኮሰባቸው ጥይት መገደላቸውን ከቅርብ ባልደረቦቻቸው አረጋግጫለሁ። መሃልሜዳ ሆስፒታል ለህክምና ቢገቡም ህይወታቸውን ማትረፍ አልተቻለም(አዩዘሀበሻ)።ሀሳብ አስተያየት መረጃ ካሎት @FANA_TV_BOT ያድርሱን
ቻናላችንን ይቀላቀሉ
@fana_televisions
@fana_televisions
1.7K viewsedited  18:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-27 13:18:56 በታይላንድ ገንዘብ ያበደሯትንና ፍቅረኛዋን ጨምሮ 12 ጓደኞቿን መርዛ የገደለችዉ ግለሰብ በቁጥጥር ስር ዋለች

የታይላንድ ፖሊስ 12 ጓደኞቿን በሲአናይድ መርዝ ገድላለች የተባለችውን ሴት በቁጥጥር ስር ማዋሉን አስታዉቋል፡፡ሳራራት ራንጊሱታፖርን የተባለችዉ ተከሳሽ በባንኮክ ከተማ የተያዘች ሲሆን የቅርብ ጓደኛዋ ሞት ጥያቄ ማስነሳቱ በቁጥጥር ስር እንድትዉል ምክንያት ሆኗል።በዚሁ ወር መጀመሪያ ላይ ከሳራራት ጋር በጉዞ ላይ እያለች ህይወቷ ማለፉ በተጎጂ ቤተሰቦች ላይ ጥርጣሬ አድሮባቸው ነበር።ፖሊስ ሳራራት የቀድሞ የወንድ ጓደኛዋን ጨምሮ ሌሎች 11 ሰዎችን እንደገደለች ይፋ አድርጓል፡፡ፖሊስ ድርጊቱን የፈጸመችዉ በገንዘብ ምክንያት መሆኑን ገልጿል፡፡ ሳራራት የቀረበባት ክሶች በሙሉ ግን ውድቅ አድርጋለች። የታይላንድ ፍርድ ቤት ግን የዋስትና መብቷን ዉድቅ አድርጓል፡፡

ከሁለት ሳምንት በፊት ከጓደኛዋ ጋር ከባንኮክ በስተ ምዕራብ ወደምትገኘው ራትቻቡሪ ግዛት በማቅናት የቡድሂስት ሀይማኖት ስነስርዓት በማቅናት ተሳትፈዉ ነበር ሲል ፖሊስ ተናግሯል።ብዙም ሳይቆይ ጓደኛዋ በወንዙ ዳርቻ ህይወቷ አልፎ ተገኘች፡፡የአስከሬን ምርመራ ሲደረግ በሰውነቷ ውስጥ የሳያንይድ መርዝ መገኘቱን ፖሊስ ተናግሯል። ወድቃ በተገኘችበት ወቅት ስልኳ፣ ገንዘብ እና ቦርሳዋ ጠፍቷል።

ሌሎች ተጎጂ ናቸው የተባሉት ሰዎች በተመሳሳይ ሁኔታ መሞታቸውን የገለጹት ባለስልጣናት፣ ተጨማሪ መረጃ ግን አልገለጹም። ግድያውን ሳራራት በ2020 መጀመሯን ተናግረዋል።ከሟቾቹ መካከል የሳራራት የቀድሞ ፍቅረኛዋ እና ሁለት ሴት የፖሊስ መኮንኖችን አሉበት፡፡

ፖሊስ በዚህ ድምዳሜ ላይ የደረሰዉ ሳራራት ከአንዲት ሴት ጓደኛዋ 250,000 ባህት ወይም 7,300 ዶላር ትበደራለች፡፡ታዲያ ጓደኛማቾቹ አብረዉ ምሳ ከበሉ በኋላ ግን አበዳሪዋ ራሷን ስታ ትወድቃለች፡፡ግን በህይወት ትተርፋለች የዚህችዉ ወጣት ቤተሰቦች ወድቃ በነበረ ጊዜ ጌጣጌጥ እና ገንዘብ መጥፋቱን ተናግረዋል ሲል ፖሊስ ለምርመራዉ ዱካ ሆኖታል፡፡ነገር ግን የጓደኛዋ ቤተሰቦቿ ሳራራት እንዲህ አድርጋለች ብለዉ ፈጽመዉ አልጠረጠሩም ነበር ያሉት የፖሊስ መኮንኖቹ፣ ይህንን ማስረጃ መሰብሰብ ፈታኝ እንደነበረበት ገልጿል፡፡አንዳንድ አስክሬኖች ተቃጥለዋል ሲል ፖሊስ ተናግሯል።

ሲአናይድ የተሰኘዉ መርዝ በከፍተኛ መጠን ጥቅም ላይ ከዋለ ከአስክሬን ላይ ሊታወቅ ይችላልለ፡፡መርዙ የልብ ድካም ሊያስከትል የሚችልና የሰውነት ኦክሲጅን ከሴሎች ላይ በመዉሰድ የመግደል አቅም አለዉ፡፡በታይላንድ ከፍተኛ ቁጥጥር የሚደረግበት ሲአናይድ ያለ አግባብ ይዞ የተገኘ ሰዉ የሁለት ዓመት እስራት ይጠብቃቸዋል።
1.9K views10:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-27 13:18:21
1.6K views10:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ