Get Mystery Box with random crypto!

አጭር ቁምነገር….! ….ከእለታት አንድ ቀን ንጉስ አንበሳ ቀበሮን ይጠራውና > ይለዋል። ቀበሮም | 𝗙𝗔𝗡𝗔 𝗧𝗩 (ፋና)️ ️️

አጭር ቁምነገር….!

….ከእለታት አንድ ቀን ንጉስ አንበሳ ቀበሮን ይጠራውና << እጅግ በጣም እርቦኛል ፤ በአስቸኳይ  የምበላው ካላመጣህልኝ ፥  አንተን ነው ቀረጣጥፌ የምበላህ! >> ይለዋል። ቀበሮም ተደናግጦ ለአንበሳው ምግብ ፍለጋ ሲሄድ  ከአህያ ጋር ይገናኛል፡፡

ይሄኔ አህያን የጦስ ዶሮ ለማድረግ የማታለያ ሀሳብ የመጣለት ቀበሮ ፥ << አያ አህያ! ስፈልግህ አገኘሁህ፡፡ ንጉሳችን አንበሳ አንተን ንጉስ ሊያደርግህ ይፈልጋልና በአስቸኳይ  እንሂድ ! >> ብሎ በማሳመን አስከትሎት ይሄዳል፡፡

የተራበው አንበሳ አህያው ከአጠገቡ ሲደርስ ፥ ጊዜ ሳያጠፋ ተንደርድሮ ጆሮውን ግሽልጥ አድርጎ ይበላዋል፡፡ ይሄኔ አህያ ደሙን እያዘራ ሲሮጥ ከቀበሮ ጋር ይገናኛሉ፡፡

<< አታለልከኝ አይደል ! ልታስበላኝ ነበር የጠራኸኝ ! >> ይለዋል፡፡

<< ኧረ በፍፁም አላታለልኩህም አያ አህያ ፤ ጆሮህን የበላህኮ ስትነግስ ዘውዱን ለመድፋት አንዳያስቸግርህ ብሎ ነው !  በል አሁን እንመለስ በቶሎ ..>> ይልና አሳምኖ ይመልሰዋል፡፡

ድጋሜ አህያው ከአንበሳው ፊት ሲደርስ ተንደርድሮ ጭራውን ቆርጦ ይበላዋል፡፡ አሁንም አህያው ደሙን እያዘራ ሲሄድ ከደላላው ቀበሮ ጋር ይገናኛሉ፡፡

<< አያ ቀበሮ ምን በድዬህ ነው ግን ፥ ያታለልከኝ ? አሁንም ጭራዬን በላኝኮ!>>  ! >> ይለዋል፡፡

<< ኧረ በፍፁም አላታለልኩህም፡፡ ምነው አያ አህያ ? ለአንተው በደከምኩ ፤ አያ አንበሳ ጭራህን የቆረጠውኮ ፥ ከነገስክ በኃላ ዙፋኑ ላይ ስትቀመጥ እንዳያስቸግርህ አስቦ ነው፡፡ በል አሁን እንመለስ ..! >> ይልና በድጋሜ አሳምኖ ይወስደዋል፡፡

ይሄኔ አንበሳው አህያውን ደቋቁሶ ገደለው፡፡ ወደቀበሮውም ዘወር ብሎ << አህያውን አሳምነህ በማምጣትህ ጥሩ ሰርተሃል፡፡ በል አሁን ደግሞ አህያውን ገነጣጥለህ   ቆዳውን ፥ ጭንቅላቱን ፣ ልቡን ፤ ሳንባውና ጉበቱን ብቻ ለይተህ አምጣልኝ! >> ሲል አዘዘው፡፡

ቀበሮ የታዘዘውን ፈፅሞ ለአንበሳው ይዞ ቀረበ፡፡ ነገርግን ይዞ ከመጣው ስጋ ውስጥ ጭንቅላቱን  ስለበላው ሊገኝ አልቻለም፡፡ ይሄኔ አንበሳው በንዴት ጦፈ፡፡ << ጭንቅላቱን የት አባክ አስገብተኸው ነው ? >> ሲልም አፈጠጠበት፡፡

ቀበሮም የዋዛ አልነበረም << ጌታዬ! ጭንቅላት እኮ ቀድሞውኑ አልነበረውም፡፡ ጭንቅላት ቢኖረውማ  ፥ ጆሮና ጅራቱን ከቆረጥከው በኃላ ዳግም ተመልሶ ወደአንተ ጋር ይመጣ ነበርን ? >> ብሎ   በብልሃት በማሳመን ራሱን ከሞት አዳነ ይባላል፡፡

የሠው ልጅም በህይወት መስመሩ ለአንድ እና ለሁለት ጊዜ ሲሳሳት እንዲታረም ከሰጠችው እድል መማር ካልቻለ ፥  ከውድቀቱ በኃላ የመማር  እድሉ ጠባብ ነው