Get Mystery Box with random crypto!

𝗙𝗔𝗡𝗔 𝗧𝗩 (ፋና)️ ️️

የቴሌግራም ቻናል አርማ fana_televisions — 𝗙𝗔𝗡𝗔 𝗧𝗩 (ፋና)️ ️️ 𝗙
የቴሌግራም ቻናል አርማ fana_televisions — 𝗙𝗔𝗡𝗔 𝗧𝗩 (ፋና)️ ️️
የሰርጥ አድራሻ: @fana_televisions
ምድቦች: ዜና
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 12.32K
የሰርጥ መግለጫ

This is FANA Media and Communication Corporate’s official Telegram channel.
For more updates please visit
https://t.me/fana_televisions
#ሼር 🙏 #በማድረግ_አጋርነታችሁን_አሳዩን
ሀሳብ ወይም መረጃ ለማቀበል @FANA_TV_BOT
https://t.me/joinchat/WC9-gid0rxB-S4Ac

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 3

2023-06-03 12:20:45
በሕንድ የባቡር አደጋ ከ280 በላይ ሰዎች ሞቱ!

በሕንድ ምሥራቃዊ ኦዲሻ ግዛት፣ ባላሶሬ በሚባል አውራጃ ሁለት በተለያየ መስመር የሚዘወሩ ባቡሮች ተላትመው 288 ተሳፋሪዎች ሲሞቱ 850 የሚሆኑት ቆስለዋል።አደጋውን ተከትሎ 200 አምቡላንሶች ወደ ስፍራው የተንቀሳቀሱ ሲሆን ከአደጋው የተረፉ ተሳፋሪዎች የከፋ ጉዳት የደረሰባቸውን ሌሎችን ለማዳን ሲረባረቡ ታይተዋል።

አደጋው የደረሰው ትናንት ዐርብ ሲሆን አንድ የመንገደኞች ባቡር መስመሩን ስቶ ከወጣ በኋላ በሌላ ከተቃራኒ አቅጣጫ እየከነፈ ይመጣ በነበረ ባቡር መገጨቱን ተከትሎ ነው በርካታ ሰዎች ሊጎዱ የቻሉት።

ይህ አደጋ በሕንድ በዚህ 21ኛው ክፍለ ዘመን ከደረሱ የባቡር አደጋዎች የከፋው ነው ተብሏል።የአካባቢው ባለሥልጣናት የሟቾች ቁጥር አሁን ካለበት በብዙ ሊያሻቅብ እንደሚችል ሰግተዋል።የሕንድ የባቡር አስተዳደር እንዳለው በአደጋው ጉዳት የደረሰባቸው ኮሮማንዴል ኤክስፕረስ እና ሆውራሽ ሱፐርፋስት ኤክስፕረስ ባቡሮች ናቸው።
1.9K views09:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-02 22:11:25 በኦሮሚያ እና ቤንሻንጉል ጉምዝ አዋሳኝ ቦታዎች በእገታ እና ዝርፊያ ሕዝቡ እየተሰቃየ ነው
በኦሮሚያ እና ቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል አዋሳኝ ቦታዎች ከኑሮ ውድነቱ በተጨማሪ፤ አፈና እና ዝርፊያ በከፍተኛ መጠን ሕዝቡን እየጎዳ መሆኑን የአካባቢው ነዋሪዎች ለአዲስ ማለዳ ገለጹ፡፡
በዋናነት በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ወለጋ ዞንና በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ካማሺ ዞን መካከል የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች በአካባቢው የሚያደርጉት ውጊያ እና ዘረፋ ከፍተኛ ነው ተብሏል፡፡
በዚህም በኹለቱ አዋሳኝ ዞኖች የመንገድ የትራንስፖርት አገልግሎት ከተቋረጠ ከሦስት ወራት በላይ ማስቆጠሩን የገለጹት ነዋሪዎች፤ “በተደጋጋሚ ብንጠይቅም መፍትሔ የሚሰጥ አካል አላገኘንም” ሲሉ ተደምጠዋል፡፡

በተለይም ከካማሺ ወደ ኦሮሚያ ክልል ነጆ እና ጊምቢ ዞኖች የሚወስደው ዋናው መንገድ ሙሉ ለሙሉ መዘጋቱን እና ምንም ዓይነት እንቅስቃሴ አለመኖሩን ነው የተናገሩት፡፡
መሠረታዊ ፍጆታዎችን ጨምሮ አጠቃላይ የሚያስፈልጉ ቁሳቁሶች የሚገቡት በዚሁ መንገድ ቢሆንም፤ በመንገዱ መዘጋት የተነሳ ከየካቲት ወር ወዲህ መሠረታዊ የፍጆታ ምርቶች እየገቡ እንዳልሆነ ገልጸዋል፡፡

በዚህም ምክንያት በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ የኅብረተሰብ ክፍሎች ክፉኛ መጎዳታቸው ነው የተጠቀሰው፡፡
እንዲሁም የአካባቢው የአየር ጠባይ ቆላማ መሆን ከፍተኛ የወባ በሽታ ስርጭት እንዲኖር አድርጓል የተባለ ሲሆን፤ በትራንስፖርት መቋረጥ የተነሳ የመድኃኒት አቅርቦት ባለመኖሩ የሰው ሕይወት እየጠፋ እንደሆነ ተጠቁሟል፡፡
ነዋሪዎቹ አክለውም “የአገር መከላከያ ሠራዊት በኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች ላይ ተደጋጋሚ እርምጃ እየወሰደ ቢሆንም፤ እስካሁን ድረስ ግን መንገዱን ማስከፈት አልተቻለም” ሲሉ ገልጸዋል፡፡ “ለሚመለከተው አካል በተደጋጋሚ ብናመለክትም መፍትሔ ልናገኝ አልቻልንም” ሲሉም ተደምጠዋል፡፡
በአሶሳ በኩል የተወሰኑ እቃዎችን ወደ ምዕራብ ወለጋ ለማስገባት ጥረት የተደረገ መሆኑን በመጥቀስ፣ ዝናብ በመዝነቡ እና መንገዱ በመበላሸቱ እሱም ሳይሳካ ቀርቷል ነው የተባለው፡፡
የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች በተለይ በወለጋ አካባቢዎች በሚሰነዝሯቸው ጥቃቶች በርካታ ንፁሐን ዜጎች ሕይወታቸውን እንዳጡና ብዙዎችም እንደተፈናቀሉ ይጠቀሳል፡፡
2.2K views19:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-02 11:03:19
[ Album ]
የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች የ2015 ዓ.ም የተማሪዎች ምረቃ

የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች የ2015 ዓ.ም የተማሪዎች የምረቃ ስነ-ስርዓት ከሐምሌ 10 እስከ 17/2015 ዓ.ም ማካሄድ እንደሚችሉ የትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል፡፡

በምረቃ መርሃ ግብሩ ላይ የሚሳተፉ ተመራቂዎች የመውጫ ፈተናውን ያለፉ ተማሪዎች ብቻ እንደሚሆኑ በትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) ተፈርሞ ለሁሉም የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች፣ ለሁሉም የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እና ለሁሉም የክልል ትምህርት ቢሮዎች የተላከ ደብዳቤ ያሳያል፡፡
2.4K views08:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-20 12:47:51
Update
በመደወላቡ ዩንቨርስቲ 15 መምህራን ላይ የደረሰው የመኪና አደጋ ይሄን ይመስላል።
1.4K views09:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-18 20:02:36
የዩኒቨርሲቲ እጩ ተመራቂዎች መውጫ ፈተና ከፊታችን ሐምሌ 3 ቀን ጀምሮ ይሰጣል!

የዩኒቨርሲቲ ተመራቂ ተማሪዎች መውጫ ፈተና ከሐምሌ 3 እስከ ሐምሌ 13 ቀን 2015 ዓ.ም እንደሚሰጥ የትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል።የ2015 ዓ.ም የመውጫ ፈተና ለመውሰድ የተመዘገቡ በግልና በመንግስት ተቋማት የሚገኙ እጩ ምሩቃን በመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች የመፈተኛ ማዕከላት ፈተናውን እንደሚወስዱ ተገልጿል።

በ2014 ዓ.ም የሕግ መውጫ ፈተና ተፈትነው ማለፊያ ነጥብ ያላስመዘገቡ ተማሪዎችም በዚሁ ጊዜ ፈተናውን የመንግስት ዩኒቨርሲቲ የመፈተኛ ማዕከላት ውስጥ መውሰድ ይችላሉ ተብሏል።ትምህርት ሚኒስቴር የዩኒቨርሲቲ መውጫ ፈተናን ለመሥጠት የተለያዩ ዝግጅቶችን ሲያደርግ መቆየቱንም የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል።ሀሳብ አስተያየት መረጃ ካሎት @FANA_TV_BOT ያድርሱን
ቻናላችንን ይቀላቀሉ
@fana_televisions
@fana_televisions
2.1K viewsedited  17:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-18 19:42:03
የሚኒስትሮች ሶስተኛ ሩብ ዓመት የሥራ አፈጻጸም ግምገማ ተጀመረ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 10 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የሚኒስትሮች ሶስተኛ ሩብ ዓመት የሥራ አፈጻጸም ግምገማ በዛሬው ዕለት መጀመሩን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አስታወቁ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ÷"በተቋማዊ አሠራር ላይ ያለውን ሂደት ለመገምገም ባለን ቁርጠኝነት የሚኒስትሮችን የሩብ ዓመት የሥራ አፈጻጸም ግምገማ ጀምረናል" ብለዋል።

የግምገማ ሂደቱም በአጠቃላይ የ9 ወራት የማክሮ ኢኮኖሚውን እና የሴክተሮች ልዩ አፈጻጸምን ይዳስሳል ነው ያሉት።ሀሳብ አስተያየት መረጃ ካሎት @FANA_TV_BOT ያድርሱን
ቻናላችንን ይቀላቀሉ
@fana_televisions
@fana_televisions
1.8K views16:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-18 19:31:40
ጥበቃዎቻችን ምን ያህል ይታመናሉ
የተጣለባቸውን ኃላፊነት ወደ ጎን በመተው ከሚጠብቁት ተቋም ውስጥ ከ3 መቶ ሺ ብር በላይ የዋጋ ግምት ያላቸውን ንብረቶች የዘረፉ ሶስት የጥበቃ ሰራተኞች በእስራት ተቀጡ፡፡

የወንጀል ድርጊቱ የተፈፀመው ሚያዚያ 3 ቀን 2015 ዓ/ም ሌሊት የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ lab

አገኘሁ አዳነ፣ አበበ ዲንቃ እና ትዕግስቱ ዳዊት የተባሉት ሶስቱ የጥበቃ ሰራተኞች ኃላፊነታቸውን ወደ ጎን በመተው ከትምህርት ቤቱ ቤተ-ሙከራ እና ከመምህራን ክፍል የዋጋ ግምታቸው ከ3 መቶ ሺ ብር በላይ የሚያውጡ የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን በመዝረፍ ተሰውረው ነበር፡፡

የወልቂጤ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ባደረገው ብርቱ ክትትል ወንጀሉ በተፈፀመ 24 ሰዓት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ከነንብረቱ በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ ከተጣራባቸው በኋላ ክስ ተመስርቶባቸው ጉዳያቸው በፍርድ ቤት ሲታይ ቆይቷል፡፡

ጉዳዩን የተመለከተው የፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ምድብ ችሎት ተከሳሾቹ እያንዳንዳቸው በ6 ዓመት እስራት እንዲቀጡ ውሳኔ መተላለፉን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡

የጥበቃ ስራ ታማኝነትን የሚጠይቅ ሙያ በመሆኑ የተጣለባቸውን ኃላፊነት ወደ ጎን በመተው በመሰል የወንጀል ድርጊት ውስጥ ገብተው የሚገኙ የጥበቃ ሰራተኞች የህግ ተጠያቂነታቸው ድርብ መሆኑን ተገንዘበው ሊታቀቡ እና በተለይ የጥበቃ አገልግሎት የሚሰጡ ተቋማት ሰራተኛ ሲቀጥሩ ተገቢውን ጥንቃቄ በማድረግ የተጠናከረ ክትትል ሊያደርጉ ይገባል፡፡ሀሳብ አስተያየት መረጃ ካሎት @FANA_TV_BOT ያድርሱን
ቻናላችንን ይቀላቀሉ
@fana_televisions
@fana_televisions
1.7K views16:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-17 11:26:45
[ Album ]
መልካም ስራ ነው
ባለፈው ሳምንት በአፋር ክልል ካሳጊታ በጦርነቱ ወቅት ተቀብረው የነበሩ ፈንጂዎች እየፈነዱ በሰዉ ላይ ጉዳት እያደረሱ እንደነበር መዘገቤ ይታወሳል። በዚህም መከላከያ ሰራዊት ወደ ስፍራው በመንቀሳቀስ በተለያዩ አካባቢዎች በጦርነት ግዜ የተቀበሩ መሳርያዎችን እያሰሰ መሰብሰብ መጀመሩን የአፋር የመረጃ ምንጮቼ ገልፀዋል
2.1K views08:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-17 11:24:53
ሰበር
ህወሃትን እናድን በሚል ዶክተር ደብረፂዎን፣አለም ገበረዋሃድ እና ሞንጀሪኖ በትግራይ ያሉ ከተሞችን ተከፋፍለው ሰሞኑን ስብሰባ እያካሄዱ ነው
ዶክተር ደብረፂዎን የሽሬ አካባቢ ከተሞችን፣ሞንጀሪኖ የማይጨው አካባቢ ከተሞችን እና አለም ገ/ዋሀድ አድዋ ያሉ ከተሞችን ይዘው ስብሰባ እያደረጉ ነው። የስብሰባው አላማ ህወሃትን ህጋዊ ፓርቲ ለማድረግ እና ፓርቲውን ለመታደግ ነው ተብሏል። ጌታቸው ረዳ ብልፅግና ነው፣ እኛን ማማከር ትቷል .....የሚል ዘመቻ እንደጀመሩበት ታውቋል። ህወሃት በርካታ እናቶች ልጆቻቸውን የገበሩበት ድርጅት ነው ወደ ህጋዊ ሰውነት መመለስ አለበት፣ህወሃት ከፈረሰ ታላቋ ትግራይ የለችም... በማለት ወጣቶችን እየሰበሰቡ ማወያየት ጀምረዋል
1.9K views08:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-15 15:04:13 ደብረዘይት(ቢሾፍቱ)
ትናንት ለሊት ሰባት ሰዓት አካባቢ የተኩስ ድምፅ እንደነበር እና ከነዋሪዎቹ ባገኘሁ መረጃ መሰረት ተኩሱ ኦነግ ሸኔ ገብቶ እንደነበር እና ከፖሊሶች ጋር በተደረገ የተኩስ ልውውጥ አራት ፖሊሶች መሞታቸውን ገልፀዋል። አሁን በከተማዋ የኦሮሚያ ልዩ ሀይል በብዛት እንደገባ ገልፀውኛል(fana)።
l
2.6K viewsedited  12:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ