Get Mystery Box with random crypto!

ጥበቃዎቻችን ምን ያህል ይታመናሉ የተጣለባቸውን ኃላፊነት ወደ ጎን በመተው ከሚጠብቁት ተቋም ውስ | 𝗙𝗔𝗡𝗔 𝗧𝗩 (ፋና)️ ️️

ጥበቃዎቻችን ምን ያህል ይታመናሉ
የተጣለባቸውን ኃላፊነት ወደ ጎን በመተው ከሚጠብቁት ተቋም ውስጥ ከ3 መቶ ሺ ብር በላይ የዋጋ ግምት ያላቸውን ንብረቶች የዘረፉ ሶስት የጥበቃ ሰራተኞች በእስራት ተቀጡ፡፡

የወንጀል ድርጊቱ የተፈፀመው ሚያዚያ 3 ቀን 2015 ዓ/ም ሌሊት የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ lab

አገኘሁ አዳነ፣ አበበ ዲንቃ እና ትዕግስቱ ዳዊት የተባሉት ሶስቱ የጥበቃ ሰራተኞች ኃላፊነታቸውን ወደ ጎን በመተው ከትምህርት ቤቱ ቤተ-ሙከራ እና ከመምህራን ክፍል የዋጋ ግምታቸው ከ3 መቶ ሺ ብር በላይ የሚያውጡ የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን በመዝረፍ ተሰውረው ነበር፡፡

የወልቂጤ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ባደረገው ብርቱ ክትትል ወንጀሉ በተፈፀመ 24 ሰዓት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ከነንብረቱ በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ ከተጣራባቸው በኋላ ክስ ተመስርቶባቸው ጉዳያቸው በፍርድ ቤት ሲታይ ቆይቷል፡፡

ጉዳዩን የተመለከተው የፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ምድብ ችሎት ተከሳሾቹ እያንዳንዳቸው በ6 ዓመት እስራት እንዲቀጡ ውሳኔ መተላለፉን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡

የጥበቃ ስራ ታማኝነትን የሚጠይቅ ሙያ በመሆኑ የተጣለባቸውን ኃላፊነት ወደ ጎን በመተው በመሰል የወንጀል ድርጊት ውስጥ ገብተው የሚገኙ የጥበቃ ሰራተኞች የህግ ተጠያቂነታቸው ድርብ መሆኑን ተገንዘበው ሊታቀቡ እና በተለይ የጥበቃ አገልግሎት የሚሰጡ ተቋማት ሰራተኛ ሲቀጥሩ ተገቢውን ጥንቃቄ በማድረግ የተጠናከረ ክትትል ሊያደርጉ ይገባል፡፡ሀሳብ አስተያየት መረጃ ካሎት @FANA_TV_BOT ያድርሱን
ቻናላችንን ይቀላቀሉ
@fana_televisions
@fana_televisions