Get Mystery Box with random crypto!

𝗙𝗔𝗡𝗔 𝗧𝗩 (ፋና)️ ️️

የቴሌግራም ቻናል አርማ fana_televisions — 𝗙𝗔𝗡𝗔 𝗧𝗩 (ፋና)️ ️️ 𝗙
የቴሌግራም ቻናል አርማ fana_televisions — 𝗙𝗔𝗡𝗔 𝗧𝗩 (ፋና)️ ️️
የሰርጥ አድራሻ: @fana_televisions
ምድቦች: ዜና
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 12.32K
የሰርጥ መግለጫ

This is FANA Media and Communication Corporate’s official Telegram channel.
For more updates please visit
https://t.me/fana_televisions
#ሼር 🙏 #በማድረግ_አጋርነታችሁን_አሳዩን
ሀሳብ ወይም መረጃ ለማቀበል @FANA_TV_BOT
https://t.me/joinchat/WC9-gid0rxB-S4Ac

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 6

2023-04-21 21:43:29
Amazing
በአሜሪካ በዶሮዎችን ጸብ ምክንያት የሰዎች ህይወት ማለፉ ተገለጸ
ከሶስት ቀናት በፊት እስከ 200 ሰዎች ይከታተሉት በነበረ የዶሮ ፍልሚያ ውድድር ላይ በተፈጠረ ግጭት ሁለት ሰዎች ሲሞቱ ሶስት ሰዎች ደግሞ ከባድ የአካል መጉደል አጋጥሟቸዋል ተብሏል።

እንደ ኤፒ ዘገባ ከሆነ ግድያውን ፈጽመዋል የተባሉ ተጠርጣሪዎች በፖሊስ የተያዙ ሲሆን ለግጭቱ ምክንያት እስካሁን ይፋ አልሆነም።

በሀዋይ አውራ ዶሮዎችን እርስ በርስ ማፋለም እና ከተመልካቾች ገቢ መሰብሰብ የተለመደ ቢሆንም የሀገሪቱ ህግ ግን ይህንን እንደማይፈቅድ ተገልጿል።

በአሜሪካ ህዝብ በተሰበሰበባቸው ስፍራዎች ላይ ተኩስ መክፈት እየጨመረ የመጣ ሲሆን በ2022 ብቻ ከ30 ሺህ በላይ አሜሪካዊያን ህይወታቸውን አጥተዋል።

የአሜሪካ ፖለቲከኞች ለሟቾች ቁጥር መጨመር የጦር መሳሪያ ቁጥጥሩ ዝቅተኛ መሆኑን በዋና ምክንያትነት በመጥቀስ ህጉ እንዲጠብቅ በማሳሰብ ላይ ናቸው።

ሁሌ ምርጫ በደረሰ ቁጥርም የጦር መሳሪያ ህግ ጉዳይ ዋነኛ አጀንዳ በመሆን ይታወቃል።
Via አል-ዐይን

#fanaFamily

ሀሳብ  አስተያየት መረጃ  ካሎት @FANA_TV_BOT ያድርሱን
ቻናላችንን ይቀላቀሉ
@fana_televisions
@fana_televisions
1.1K viewsedited  18:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-21 21:42:32
የሩስያ ተዋጊ ቡድን ዋግነር ሚሳኤሎችን ለሱዳን ፈጣን ድጋፍ ሃይሎች (RSF) ለማቅረብ ማቀዱ ተሰማ
በአጎራባች ሊቢያ እና በመካከለኛው አፍሪካ ሪፐብሊክ የሚንቀሳቀሰው የዋግነር ሀይል ከክሬምሊን ጋር የተቀናጀ ቅጥረኛ ቡድን በሱዳን ለሚገኘው አርኤስኤፍ በትከሻ የሚተኮሱ ማንፓድ ፀረ-አይሮፕላን ሚሳኤሎችን ለመላክ አቅርበዋል ሲሉ የአሁኑ እና የቀድሞ የአሜሪካ ባለስልጣናት ለዎል ለስትሪት ጆርናል ተናግረዋል።
ለአርኤስኤፍ መሪ ቅርብ የሆኑት ጄኔራል መሀመድ ሃምዳን ዳጋሎ ለጋዜጣው እንደተናገሩት የአሜሪካ መንግስትን ላለመቃወም የጦር መሳሪያ አቅርቦትን ለጊዜው አልተቀበሉትም ሲል የዘገበው ዘቴሌግራፍ ነው።
ሲ ኤን ኤን በበኩሉ ዋግነር የአየር  ሚሳኤሎችን ለ RSF በማቅረቡ በዋና ከተማይቱ ካርቱም፣በዳርፉር እና በሌሎችም ስፍራዎች ከከሱዳን ወታደራዊ ሃይሎች በላይ የአየር ወታደራዊ ሃይሉን በከፍተኛ ሁኔታ አሳድጎ እንደነበር ዘግቧል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ የእስራኤል ባለስልጣናት ከሄመንቲ እና ቡርሃን  የትኛውን መደገፍ እንዳለባቸው ክርክር ውስጥ መግባታቸው ታውቋል

#fanaFamily

ሀሳብ  አስተያየት መረጃ  ካሎት @FANA_TV_BOT ያድርሱን
ቻናላችንን ይቀላቀሉ
@fana_televisions
@fana_televisions
987 viewsedited  18:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-21 16:27:30 የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ይቅርታ ጠየቀ
የዒድ ሰላት ለመስገድ ከቤታችሁ ወጥታችሁ ላመለጣችሁ የከተማችንና አካባቢው ሙስሊሞች በሙሉ!!
ዛሬ በነበረው የኢድ ሰላት ፕሮግራም ላይ ለመታደም ጥሪያችንን አክብራችሁ በአንድነት  አምራችሁና ደምቃችሁ ግዙፉ የከተማችን ውበት ሆናችሁ በመዋላችሁ የተሰማንን ታላቅ ደስታ እንገልፃለን።

የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት በድጋሚ እንኳን ለ1444 ዓ.ሂ  የኢድ አልፊጥር በዓል  በሰላም አደረሳችሁ እያልን በዛሬው እለት የተሰገደው የኢድ ሰላት በሰላም፣በደስታ መጠናቀቁ ቢያስደስትም የዒድ ሰላት ከዚህ ቀደም ሲሰገድበት ከነበረው ሰአት ቀድሞ በመሰገዱ የዒድ ሰላት ላመለጣችሁ የከተማችን ሙስሊሞች ይቅርታ እንጠይቃለን።

በትናንትናው እለት ከፌደራል መጅሊስ ጋር በጋራ በሰጠነው መግለጫ ሸሪአውን በጠበቀ መልኩ በእለቱ ንግግሮች እንደማይኖሩና በማለዳ ሰግደን እንደምንበተን ለህዝባችን ገልፀን ቢሆንም በእለቱ የተገኙት ሚድያዎች በአብዛኛው በሚባል መልኩ ትኩረት ሰጥተው ባለማስተላለፈቸው እና ከሚዲያዎቹ በተጨማሪ ሌሎች አማራጮችን በሰፊው  ባለመጠቀማችን ችግሩ እንዲፈጠር ምክንያት እንደነበሩ ተረድተናል።

በተጨማሪም ከዚህ ቀደም ሲሰገድበት የነበረውን ሂደትን ለማሻሻል በሚል መልካም እሳቤ በተፈጠረ ክፍተት ሰላት ላመለጣችሁ ሁሉ ታላቅ ይቅርታ እየጠየቅን በቀጣይ የሚስተካከል መሆኑን ህዝባችን እንዲገነዘብ እያልን፣
በበጎና ገንቢ በሆነ መልኩ አስተያየታችሁን ለለገሳችሁን የከተማችን ነዋሪዎች ምስጋና እያቀረብን በዓሉ የሰላም የደስታ፣የመተዛዘን፣የመረዳዳት እንዲሆን መልካም ምኞታችንን ለመግለፅ እንወዳለን።

#fanaFamily

ሀሳብ  አስተያየት መረጃ  ካሎት @FANA_TV_BOT ያድርሱን
ቻናላችንን ይቀላቀሉ
@fana_televisions
@fana_televisions
1.3K viewsedited  13:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-21 09:20:15
#ዒድ_አልፈጥር 

ውድ የእስልምና እምነት ተከታይ የሆናችሁ ቤተሰቦቻችን በሙሉ እንኳን ለ1444ኛው የዒድ አልፈጥር በዓል አደረሳችሁ፤ አደረሰን። ዒድ ሙባረክ !

በዓሉ የሰላም ፣ የአንድነት ፣ የፍቅር እና የመተሳሰብ ይሆን ዘንድ እንመኛለን።

በዓሉን ስታከብሩ የተቸገሩት ፣ ያጡትን ፣ በችግር ላይ የወደቁትን ፤ በሰላም እጦት የሚሰቃዩትን ፣ በጦርነት እና በግጭት ወገን ዘመዶቻቸውን ከጎናቸው የተነጠቁትን ፣  ከሞቀው ቄያቸው ተፈናቅለው ሜዳ ላይ የቀሩ ወገኖቻችን በማሰብ ይሆን ዘንድ አደራ እንላለን።

ሀገራችንን ፈጣሪ ይጠብቅልን!!
መልካም በዓል !



#fanaFamily

ሀሳብ  አስተያየት መረጃ  ካሎት @FANA_TV_BOT ያድርሱን
ቻናላችንን ይቀላቀሉ
@fana_televisions
@fana_televisions
1.6K views06:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-20 16:07:20 የጠቅላይ ሚኒስቴርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጽህፈት ቤቶች ሊከሰሱ ነዉ ተባለ

ከአንድ አመት ከስድስት ወር በፊት በኬኒያ የታገተው የአቶ ሳምሶን ተ/ሚካኤል  ቤተሰቦች በሁለቱ ተቋማት ላይ ክስ ሊመሰርቱ እንደሆነ አስታዉቀዋል፡፡

በሳምሶን ጉዳይ  የውጭ ጉዳይ እና የጠቅላይ ሚኒስትር ጽፈት ቤት የሰጡት ትኩረት አነስተኛ ነው ያሉት ቤተሰቦቹ፤ ክስ ሊመሰሩት መሆኑ ተናግረዋል፡፡

አቶ ሳምሶን ተ/ሚካኤል ባለቤት ወ/ሮ ሚለን ሃለፎም እስካሁን በመስራቤቶቹ በኩል እየተሰጠን ያለው መረጃ ለዜጋ የሚመጥን አይደለም ብለዋል፡፡

ከዚህ በፊት የተሰጠን ምላሽ እና አሁንም እየተሰጠን ያለው ተመሳሳይ ነው ብለዋል፡፡

በኬኒያ የሚገኝው የኢትዮጵያ ኤምባሲ በግለሰቡ ዙርያ ምርመራ እያካሄድን ነው ከማለት ውጭ የሚሰጠን ተስፋ የለም ሲሉ ተናግረዋል፡፡

በፌደራል እንደዚሁም በኦሮሚያ ክልል ማንኛውም ፍርድ ቤት ጠበቃና የህግ አማካሪ የሆኑት ዶ/ር ዳባ ጩፋ የአቶ ሰምሶን ጉዳይ እልባት አለማግኝት በኬኒያ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ድክመት ነው ብለዋል፡፡

ኤምባሲው ልክ እንደ መንግስት የዜጎችን ደህንነት ማረጋገጥ ሲጠበቅበት ነገሩን በቸልታ እያለፈው ይገኛል ብለዋል፡፡

የአቶ ሳምሶን ቤተሰቦች ጉዳዩን በተደጋጋሚ ለውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እና ለጠቅላይ ሚኒስትር ጽፈት ቤት ቢያቀርቡም አንድም ውጤት አለማምጣቱትን ነው የገለጹት፡፡

በመሆኑም የአቶ ሳምሶን ተ/ሚካኤል   ቤተሰቦች በሁለቱ ፅሕፈት ቤቶች ላይ ክስ በመክፈት የልጃቸዉን አድርሻ ለማግኘት እየተንቀሳቀሱ እንደሆነ በሰጡት መግለጫ አስታዉቀዋል፡፡                      
ሀሳብ  አስተያየት መረጃ  ካሎት @FANA_TV_BOT ያድርሱን
ቻናላችንን ይቀላቀሉ
@fana_televisions
@fana_televisions
2.4K viewsedited  13:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-18 20:39:12
40 ሺ ብር የወጣበት ሰንጋ 53ሺ ብር ሚያወጣ ወርቅ ሆዱ ውስጥ ተገኘ።
በአርሲ ዞን ጢዮ ወረዳ ዶንሾ ቀበሌ  ለበዓል  ከታረደ ሰንጋ ሆድ ውስጥ   18.5  ግራም ወርቅ  ተገኝቷል።   ለባለቤቶቹ  53 ሺ ብር  ገቢ  አስገኝቶ ከወጣበት በላይ አስገቷል ተብሏል።

ይህ ነገር በሳይንስ እንዴት ይታያል ለሚለው ጥያቄ በኦሮሚያ ግብርና ቢሮ አሰላ የሚገኘው የእንስሳት ጤና ጥበቃ ማዕከላዊ የእንስሳት ጤና ጥበቃ የእንስሳት ሐኪም ዘሰጡት አስተያየት።

"በረሃማ አካባቢ የሚኖሩ ከብቶች ትንንሽ ማዕድናት ያላቸውን ተክሎች ስለሚመገቡ ከቆይታ ብዛት ወደ  ወርቅ ይለወጣል. ብለዋል ። "

ሀሳብ  አስተያየት መረጃ  ካሎት @FANA_TV_BOT ያድርሱን
ቻናላችንን ይቀላቀሉ
@fana_televisions
@fana_televisions
814 views17:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-18 10:58:23 ለፋሲካ በዓል ልብስ አልተገዛልኝም በሚል ያኮረፈዉ ወጣት ራሱን አጠፋ


በደቡብ ክልል ደቡብ ኦሞ ዞን ደቡብ አሪ ወረዳ ለበዓል ልብስ አልተገዛልኝም በሚል ከቤተሰቦቹ ተጨቃጭቆ መግባባት ያልቻለዉ  ወጣት በገመድ እራሱን ሰቅሎ ህይወቱን ማጥፋቱ በደቡብ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን የሚዲያ ክፍል ኃላፊ ምክትል ኮማንደር ታጁ ነጋሽ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።


በደቡብ አሪ ወረዳ ባላመር ቀበሌ ነዋሪ የሆነዉ   ይህ ወጣት ለ2015  ዓ.ም የትንሳኤ  በዓል ልብስ እንዲገዛለት ለወላጆቹ ጥያቄ ያቀርብላቸዋል።

ወላጆቹምኃ ቀደም ሲል የሚለብሳቸዉ ልቦሶች አፅድቶ በመልበስ የዘንድሮዉን በዓል አክብሮ እንዲዉልና በሱ ጥያቄ ሳይሆን አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ አዳዲስ ልብሶችን ቤተሰብ ይገዛልሀል የሚል ተስፋ አስቆራጭ ምላሽ ይሰጠዋል።  ይህ  ወጣት በወላጆቹ እምቢታ ተናዶ እራሱን እንደሚያጠፋ ዝቶ ከቤተሰቦቹ ጋር ከስምምነት ሳይደርስ ይለያያል።

ወጣቱ እራሱን ለማጥፋት ቢዝትም ቤተሰብ እንዲህ አይነቱ ተግባር ሊፈፅም ይችላል የሚል ጥርጣሬ ባይኖራቸውም ሚያዝያ 08 ቀን 2015 ዓ.ም ከቀኑ 12:00 ሰዓት ላይ  ወጣቱ እራሱን በገመድ ሰቅሎ  ህይወቱ ማለፉን ኮማንደር ታጁ ነጋሽ ጨምረው ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።
ሀሳብ  አስተያየት መረጃ  ካሎት @FANA_TV_BOT ያድርሱን
ቻናላችንን ይቀላቀሉ
@fana_televisions
@fana_televisions
1.3K viewsedited  07:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-17 18:47:39
የመጨረሻ ግብዣ…

በ10 ሺህዎች የምትቆጠሩ የፋና ቲቪ ወደ ቻናሉ Join ሳታደርጉ መረጃውን ብቻ አይታችሁ እንደምትመለሱ እያየን ነው።መረጃውን ፈልጋችሁ ቤተሰብ መሆንን ጠልታችሁ አይሆንም።የመጨረሻ የምንጠይቃችሁ አሁኑኑ Join እያላችሁ ወደ ቻናሌ ግቡ።ካልሆነ መረጃዎቹ እናንተ ጋር እንዳይታዩ ለአባላቱ ብቻ እንዲደርሱ ለማድረግ ይቻላል።ስለሆነም በጣም የማከብራችሁ ወዳጆቼ መረጃዎችህን ማየት እንፈልጋችሁ ካላችሁ አሁኑኑ Join በማለት ቤተሰብ ሁኑ
  

ሀሳብ  አስተያየት መረጃ  ካሎት @FANA_TV_BOT ያድርሱን
ቻናላችንን ይቀላቀሉ
@fana_televisions
@fana_televisions
1.5K viewsedited  15:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-17 18:45:58
የጎዳና ላይ ኢፍጧር ዛሬ በመቀሌ

ሀሳብ  አስተያየት መረጃ  ካሎት @FANA_TV_BOT ያድርሱን
ቻናላችንን ይቀላቀሉ
@fana_televisions
@fana_televisions
1.5K views15:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-16 08:23:37
ሱዳን ለምትገኙ ኢትዮጵያዊያን በሙሉ
ለሊቱን ጋብ ብሎ የነበረው ጦርነት ዛሬ ጠዋት እንደገና ተቀስቅሷል። የንፁሃን ሞት 60 ደርሷል።
በወታደራዊው ሃይል ተጨማሪ የኤርያል ጥቃት ማለት በአየር ላይ ጥቃት ስለሚኖር ሲቪሎች መንቀሳቀስ የለባችሁም ሲል ትናንት ማምሻውን መመሪያ አውጥቷል እና ባላችሁበት ሁኑ።
እቤት ውስጥም ይሁን ግቢ ውስጥ ቁማቹ አትንቀሳቀሱ ተባራሪ ጥይት እንዳያገኛቹ።
አያድርስና ጉዳት ሲደርስባች እታች ካሉ ሆስፒታሎች ለናንተ ቀረብ ያለው ጋ የህክምና እርዳታ ማግኘት ትችላላቹህ።
ወደ ሆስፒታል ከመሄዳቹ በፊት በተቀመጠው ስልክ ደውላቹ መመዝገብ እና በቂ ሃኪሞች መኖራቸውንም ማረጋገጥ ግድ ይላቹሃል(አዩዘሀበሻ)።
ሚያዝያ 8/2015 ዓ.ም
1.3K viewsedited  05:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ