Get Mystery Box with random crypto!

ወደ እርምጃ ሊገባ ነው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የኦዲት ክፍተት በተገኘባቸው የመንግሥት መስሪ | 𝗙𝗔𝗡𝗔 𝗧𝗩 (ፋና)️ ️️

ወደ እርምጃ ሊገባ ነው
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የኦዲት ክፍተት በተገኘባቸው የመንግሥት መስሪያ ቤቶች ላይ የሕግ አስከባሪ አካላት የእርምት ርምጃ እንዲወስዱ አሳስቧል።
ምክር ቤቱ ይህን ማሳሰቢያ የሰጠው፣ የፌደራል ዋና ኦዲተር መሠረት ዳምጤ ያቀረቡትን የ2014 ዓ፣ም የኦዲት አፈጻጸም ሪፖርት ከገመገመ በኋላ ነው።

ዋና ኦዲተሯ ባቀረቡት ሪፖርት፣ 86 የመንግሥት መስሪያ ቤቶች ባለፉት ጥቂት ዓመታት በጠቅላላው ከ6 ነጥብ 8 ቢለዮን ብር በላይ ተመላሽ እንዲያደርጉ ቢነገራቸውም፣ ተመላሽ ያደረጉት ግን  0 ነጥብ 65 በመቶውን ብቻ እንደኾነ ገልፀዋል።