Get Mystery Box with random crypto!

ከ838 ግራም በላይ ወርቅ ሲያሸሹና ህገወጥ ጦር መሣሪያ ይዘው የተገኙ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሥር | 𝗙𝗔𝗡𝗔 𝗧𝗩 (ፋና)️ ️️

ከ838 ግራም በላይ ወርቅ ሲያሸሹና ህገወጥ ጦር መሣሪያ ይዘው የተገኙ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሥር ዋሉ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 22፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ  ምዕራብ ኢትዮጵያና በጋምቤላ ክልሎች ከ838 ግራም በላይ የወርቅ ማዕድን ሲያሸሹና ህገወጥ ጦር መሣሪያ ይዘው ተገኝተዋል የተባሉ ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ሥር ማዋሉን የፀጥታና ደኅንነት የጋራ ግብረ-ኃይል አስታውቋል።

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ቢሮ ወረዳና በጋምቤላ ክልል ዲማ ወረዳ 20 ክላሽንኮቭ ከ934 መሰል ጥይቶች ጋር፣ 8 ሽጉጥ ከ54 መሰል ጥይቶች ጋር፣ ሁለት ኤፍ ዋን ቦንቦች እና አንድ ጂ ፒ ኤስ መያዛቸው ተገልጿል፡፡

ከዚህ ባለፈም 172 የተለያዩ የወርቅ ጌጣጌጦች፣ ከ838 ግራም በላይ የወርቅ ማዕድን፣ 7 የወርቅ ማቅለጫ ማሽኖች፣ 10 የወርቅ ሚዛን፣ ከ1 ሚሊየን 653 ሺህ ብር በላይ በአሶሳ ዞን ጉሙሩክ የፍተሻ ጣቢያ መያዛቸው ተጠቁሟል ።