Get Mystery Box with random crypto!

ለሸኔ የሽብር ቡድን የትጥቅ ድጋፍ ለማድረግ ሲጓዙ የነበሩ ሁለት ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሥር  ዋሉ | 𝗙𝗔𝗡𝗔 𝗧𝗩 (ፋና)️ ️️

ለሸኔ የሽብር ቡድን የትጥቅ ድጋፍ ለማድረግ ሲጓዙ የነበሩ ሁለት ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሥር  ዋሉ

ለሸኔ የሽብር ቡድን የትጥቅ ድጋፍ ለማድረግ ሲጓዙ የነበሩ ሁለት ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሥር ማዋሉን የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ አስታውቋል።

ተጠርጣሪዎቹ ሰኔ 20 ቀን 2015 ዓ.ም መነሻቸውን ከአዲስ አበባ ከተማ ለቡ አድርገው አንድ ብሬን እና 263 የክላሽንኮቭ ጠመንጃ ጥይቶችን ጭነው ሲጓዙ ሆለታ ከተማን እንዳለፉ ነው በቁጥጥር ሥር የዋሉት።

ተጠርጣሪዎቹ ከህገ-ወጥ የጦር መሣሪያው በተጨማሪ ለእኩይ ዓለማቸው ማስፈፀሚያ ሐሰተኛ የአዲስ አበባ ከተማ የነዋሪ መታወቂያ፣ የልደት ምስክር ወረቀት፣ ልዩ ልዩ ማህተሞች እና ሀሰተኛ ሰነዶችን እንደያዙ በቁጥር ሥር ውለው ጉዳያቸው በምርመራ እየተጣራ እንደሚገኝ ተጠቁሟል።

ተጠርጣዎቹ በፀጥታና ደህንነት የጋራ ግብረ ኃይል በተደረገ ጠንካራ ክትትል በቁጥጥር ስር መዋላቸው ታውቋል።

ኅብረተሰቡም እነዚህ ህገወጥ መሣሪያዎች በሸኔ የሽብር ቡድን እጅ ቢገቡ ኖሮ በንፁሃን ዜጎቻችን ላይ የሚያደርሱት ጥፋት ከፍተኛ መሆኑን ተገንዝቦ መሰል የወንጀል ተግባራትን ሲመለከት ለፀጥታ አካላት በፍጥነት ጥቆማ በመስጠት እያደረገ ያለውን ተሳትፎ አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ ቀርቧል።