Get Mystery Box with random crypto!

መፀዳጃ ቤት አለምድ ብሎ በዳይፐር ብቻ የሚፀዳዳውን የ3 አመት ልጁን በቁጥጥር ስር ያዋለው ፖሊስ | 𝗙𝗔𝗡𝗔 𝗧𝗩 (ፋና)️ ️️

መፀዳጃ ቤት አለምድ ብሎ በዳይፐር ብቻ የሚፀዳዳውን የ3 አመት ልጁን በቁጥጥር ስር ያዋለው ፖሊስ አነጋጋሪ ሆኗል

ማይክል ሾንቦርድ የተባለው ግለሰብ በአሜሪካ፣ ፍሎሪዳ ግዛት በዴይቶና ፖሊስ መምሪያ የሚያገለግል ፖሊስ ነው።ይህ ሰው እንጀራው ከሆነው ፖሊስነት በተጨማሪ የአባትነት ሀላፊነትም አለበት።

እናም የ3 አመት ልጁ ግን እርሱ በፈለገው መንገድ ከዳይፐር ውጪ መፀዳዳት ሊለምድለት አልቻለም። በተደጋጋሚ ሞክሮ ሊሳካለት ባለመቻሉና ህፃኑ በለበሰው ልብስ ላይ ተፀዳድቶ በማግኘቱ ወደ ፖሊስ ጣቢያ ሊወስደው በቅቷል።

አባት ይህንን ድርጊት ከአንዴም ሁለቴ መፈፀሙ ብቻ ሳይሆን የጨቅላውን እጅ በካቴና ማሰሩም አስደንጋጭ ሆኗል።

ፖሊሱ ይህንን ተግባር ማከናወኑ የታወቀው በድንብ ልብሱ ላይ በተገጠመው ካሜራ ምክንያት ነው። ካሜራው ያስቀረው ምስል እና ድምፅ ላይ ህፃኑ በከፍተኛ መሸማቀቅ <<ሁለተኛ ልብሴ ላይ አልፀዳዳም>> ሲልም የሚደመጥ ሲሆን አባትም <<ይሄንን ነው መስማት የምፈልገው>> ሲል መልሶለታል።

ፖሊሱ ከዚህ ቀደም አንዲትን ህፃን ደብድቧል ባለው ሌላኛው ልጁ ላይ ተመሳሳይ እስር ፈፅሞ እንደነበርም ተነግራል። ሌላው አስገራሚ ጉዳይ ደግሞ ባለቤቱም በዚያው ተቋም መርማሪ ሆና የምትሰራ መሆኗን ዳጉ ጆርናል ፅፏል።

ይህ ሾንብሮድ የተባለው ፖሊስ የሚሰራበት መምሪያ ጉዳዩን በመመርመር ላይ ያለ ሲሆን የተወሰደ እርምጃ ስለመኖር አለመኖሩ ግን የታወቀ ነገር የለም።