Get Mystery Box with random crypto!

ዘማሪ ዲ/ን ፍፁም ከበደ

የቴሌግራም ቻናል አርማ zdfitsumkebe — ዘማሪ ዲ/ን ፍፁም ከበደ
የቴሌግራም ቻናል አርማ zdfitsumkebe — ዘማሪ ዲ/ን ፍፁም ከበደ
የሰርጥ አድራሻ: @zdfitsumkebe
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 22.71K
የሰርጥ መግለጫ

ዘማሪ ዲያቆን ፍፁም ከበደ

Ratings & Reviews

5.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

2

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 32

2022-07-06 11:38:53
የስደተኞች ምርኩዝ

...የመጀመሪያዎቹ የእስልምና ስደተኞች ወደ ኢትዮጵያ ሲመጡ ንጉሡ እንዲቀበሏቸው ካደረጉ ምክንያቶች አንዱ የስደተኞች ምርኩዝ ድንግል ማርያም ስላግባባቻቸው ነው።

መሐመድ ወገኖቹን ወደ ኢትዮጵያ እንዲሔዱና ከአሳዳጆቻቸው እንዲያመልጡ በመከራቸው መሠረት ወደ ኢትዮጵያ የመጡት የመጀመሪያዎቹ ሙስሊሞች በንጉሡ እልፍኝ ቀረቡ። ከእነርሱም ጃፋር አቡ ታሊብ የተባለው ንጉሡ ስለ እምነታቸው በጠየቁት ጊዜ ቀድሞ ጣዖት አምላኪዎች እንደ ነበሩ፣ ሰብአዊነት በጎደለው መልኩ ይገዳደሉ እንደ ነበርና ምግባራቸውም መልካም እንዳልነበር ገልጾ ነቢያቸው መሐመድ እስልምናን ካስተማራቸው በኋላ ግን በአንድ አምላክ ማምለክ እንደ ጀመሩ አስረዳቸው። ንጉሡም በኢየሱስ ክርስቶስ ያምኑ እንደሆንና ስለ እርሱ ምን እንደሚሉ በቅድሚያ ጠየቁት። ጃፋርም 'በእውነት ክርስቶስ ኢየሱስ፣ የማርያም ልጅ፣ የእግዚአብሔር መልእክተኛ፣ ወደ ማርያም የተላከ ቃሉና ከእርሱ የወጣ መንፈስ ነው' ሲል ከቁራን ጠቅሶ ተናገረ። በማስከተልም ንጉሡ ስለ ድንግል ማርያም ቢጠይቁት ከሉቃስ 1:47-55 የተገለበጠውን የቁራን ጥቅስ ጠቅሶ '(ነፍሴ ጌታን ታከብረዋለች፣) መንፈሴም በአምላኬ በመድኃኒቴ ሐሴት ታደርጋለች...' ብሎ መሰከረ። ንጉሡ ይህን ጸሎተ ማርያም በኢአማኒው አንደበት ሲሰሙ የጉንጫቸው ጺም በዕንባቸው እስኪርስ ድረስ በስሜት አለቀሱ... አብረዋቸው የነበሩት ጳጳሳትም እንዲሁ መጽሐፎቻቸው በዕንባቸው እስኪርሱ ድረስ አለቀሱ። ከዚህ በኋላም ንጉሡ ስደተኞቹን በደንብ እንዲጠበቁ አደረጉ።"

(ከ"የመሰጠት ሕይወት" ገጽ 113-114 የተወሰደ)

ዲያቆን ሕሊና በለጠ


https://t.me/ZDfitsumkebede
5.4K views✞£iŧsûm✞, 08:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-05 17:13:47 እንዴት እንጸልይ*??

የብዙዎች ጥያቄ መልስ ????

አንድ ሰው ለጸሎት ሲነሳ ዝም ብሎ እንደ ውሃ ደራሽ መሆን የለበትም፡፡ ለምን?እንዴት? መቼ? እጸልያለሁ የሚሉት ጥያቄዎች ሊመለሱ ይገባል። ስለ ጸሎት በምናስብበት ማናቸውም ጊዜ ልናስተወላቸው የሚያስፈልጉን ሁለት መሠረታዊ ነጥቦች አሉ፡- በእምነት መጸለይና በጥልቀት/በማስተዋል መጸለይ፡፡
እስኪ ሰፋ አድርገን እንመልከታቸው።

1. በእምነት መጸለይ
እግዚአብሔር አምላካችን ስለሚያስብልንና ስለሚወደን ልመናችንን እንደሚሰማንና የሚረባንን ነገር እንደሚያደርግልን፣ የተሻለውንም ነገር እንደሚሰጠን ልናምን ያስፈልገናል፡፡ ‘‘አምናችኹም በጸሎት የምትለምኑትን ዅሉ ትቀበላላችኹ፡፡’’ ማቴ 21፣22 ተብለናልና አምላካችን እግዚአብሔር የሚያስፈልገንን ሁሉ ሳንለምነው እንደሚሰጠንም እናምናለን፡፡ ‘‘ሳትለምኑት አባታችሁ የሚያስፈልጋችሁን ያውቃልና’’ ተብሎ እንደተጻፈ እግዚአብሔር አምላካችን እንኳን በለመንነው ነገር ይቅርና ባለመንነው በጎ ነገርም ላይ እርሱ ጻድቅና የታመነ ነው፡፡ (ማቴ 6፣8)፡፡ እስከ ሞት የወደደን እርሱ ደግሞ ሊሰጠን የማይወደውና የሚከለክለን ነገር እንደሌለ እናምናለን፡፡‘‘ለገዛ ልጁ ያልራራለት ነገር ግን ስለ ሁላችን አሳልፎ የሰጠው ያው ከእርሱ ጋር ደግሞ ሁሉን ነገር እንዲያው እንዴት አይሰጠንም?’’ ሮሜ 8፣32፡፡

በልጁ በኢየሱስ ክርስቶስ ሞት የወደደንና የታረቀን አባታችን እግዚአብሔር የበጎ ነገር ሁሉ ምንጭ፣ የመልካምነት ሁሉ መዝገብ፣ የቸርነት ሁሉ መገኛ ነውና የምንለምነውን ሁሉ ከእርሱ እንደምንቀበል አውቀን እንጸልያለን፡፡‘‘ለምኑ፥ ይሰጣችኹማል፤ ፈልጉ፥ ታገኙማላችኹ፤ መዝጊያን አንኳኩ፥ ይከፈትላችኹማል። የሚለምነው ዅሉ ይቀበላልና፥ የሚፈልገውም ያገኛል፥ መዝጊያንም ለሚያንኳኳ ይከፈትለታል። ወይስ ከእናንተ፥ ልጁ እንጀራ ቢለምነው፥ ድንጋይን የሚሰጠው ከእናንተ ማን ሰው ነው? ዓሣስ ቢለምነው እባብን ይሰጠዋልን? እንኪያስ እናንተ ክፉዎች ስትኾኑ ለልጆቻችኹ መልካም ስጦታ መስጠትን ካወቃችኹ፥ በሰማያት ያለው አባታችኹ ለሚለምኑት እንዴት አብልጦ መልካም ነገርን ይሰጣቸው?’’ (ማቴ 7፣7-11)፡፡


እግዚአብሔር አምላካችን ለፍጥረቱ ሁሉ መጋቢ፣ የሚያዝንና የሚራራ ስለሆነ የምንለምነውን ሁሉ እንደሚሰጠንና እንደሚያደርግልን አምነን እንጸልያለን፤ ይህ እምነት እንኳን ባይኖረን ‘‘አለማመኔን እርዳው’’ ብለን ልንጸልይ ያስፈልገናል፡፡ እግዚአብሔር አምላካችንም የእምነት ሰዎች ሊያደርገንና በፊቱ የእምነት ሰዎች ሆነን እናድግ ዘንድ ሊያግዘን ይቻለዋል፡፡(ማር 9፣24)፡፡

ሐዋርያትም በአንድ ወቅት መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ‘‘እምነት ጨምርልን’’ ብለውት ነበር፡፡ ሉቃ 17፣5፡፡ እርሱም በለመኑት ነገር ሁሉ ላይ የታመነ ነውና ሐዋርያቱን በእምነት አሳድጓቸዋል፣ አጠንክሯቸዋልም፡፡ እምነት በጸሎት ሕይወታችን ውስጥ ከእግዚአብሔር ኃይልን የምንቀበልበት ታላቅ መንፈሳዊነት ነው፡፡ የቱንም ያህል እግዚአብሔር እንደረሳን ቢሰማንና የዘገየ ቢመስለንም እርሱ ሁሉን የሚያደርግበት የራሱ ጊዜ አለውና በእምነት ጸንተን እንጸልያለን፣ በእምነታችንም ወስጥ ደግሞ የእርሱን ጊዜ በትዕግስት እንጠብቃለን፡፡ ጻድቅ ኢዮብ እንዴት እንደተፈተነ እናውቃለን፤ ሆኖም ግን እግዚአብሔርን ባለማመን፣ ተስፋ በመቁረጥና የእግዚአብሔርን ጊዜ ባለመጠበቅ አልደከመም፡፡ በብዙ መከራው ውስጥ እግዚአብሔርን በመጠበቁ ከፊተኛው ይልቅ የኋለኛውን እግዚአብሔር ለኢዮብ ሊባርክለት ወዷል፡፡

2. በጥልቀትና በማስተዋል እንጸልይ፡፡

ለጸሎት በእግዚአብሔር ፊት በምንቆምበት ጊዜ ሁሉ ከውስጣችን የምናወጣው ማናቸውም ቃልና የምናደርገው ማንኛውም ዓይነት እንቅስቃሴ በማወቅና በማስተዋል መሆን አለበት፡፡ ከልብ ፈንቅሎ የሚወጣ፣ ከመንፈሳዊነት ጥግ የሚመነጭ ጥልቅ ስሜት ያልተለየው፣ እውነተኛ መንፈሳዊ መሻትን የሚገልጽ እውነት እንዲኖረን ያስፈልጋል፡፡ ይህም ሲባል ጸሎታችን ኃጢአታችንን በመናዘዝና ጥፋታችንን በማመን የተደረገ (መዝ 50/ ምሳ 28፣13)፣ እግዚአብሔርን ተስፋ በማድረግና በመጠበቅ ውስጥ የሆነ (አንተ የመድኃኒቴ አምላክ ነህና በእውነትህ ምራኝ፥ አስተምረኝም ቀኑን ሁሉ አንተን ተስፋ አድርጌአለሁ መዝ 25፣5/ ሮሜ 8፣24-25)፣ በፍቅር የምንፈጽመው (1ኛ ቆሮ 13) ሊሆን ይገባል፡፡ ያለፍቅር የሚሆን ማናቸውም በጎ ነገር ሁሉ ከንቱ መሆኑ ተጽፏል፡፡ 1ኛ ዮሐ 3፣10 ላይም ወንድሙን የማይወድ ሁሉ ከእግዚአብሔር አይደለም ተብሎ ተጽፏልና ጸሎታችን ጠላቶቻችንን በመውደድ፣ ለሌሎች በማዘንና በመራራት ውስጥ ሆነን የምንጸልየው ሊሆን ይገባል። በመጽናት (ኤፌ 6፣18 በጸሎትና በልመናም ሁሉ ዘወትር በመንፈስ ጸልዩ፤ በዚህም አሳብ ስለ ቅዱሳን ሁሉ እየለመናችሁ በመጽናት ሁሉ ትጉ) እንደተባለ እግዚአብሔርን በመጽናት የምንጠብቅበትና የምንታገስበትም እንዲሆን ያስፈልገናል፡፡



ዲያቆን ወሰን የለው በሐሩ

https://t.me/ZDfitsumkebede
https://t.me/ZDfitsumkebede
5.2K views✞£iŧsûm✞, 14:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-05 09:58:50 የጥያቄ መልስ "ራዕይ ዮሐንስ"22-18



እንደ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን 81 መጽሐፍ ቅዱስ ሳታጎል ትቀበላለች ነገር ግን ሌሎች ዘመን አመጣሽ ቤተ እምነቶች 61 ነው ምንቀበለው ብለው ያስተምራሉ ለዚህ አስተምሕሮታቸው እንደ ማስረጃ አድርገው የሚያቀርቡ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ ( ራእ 22-18) " ማንም በዚህ ላይ አንዳች ቢጨምር እግዚአብሔር በዚሕ መፃሕፍ ላይ የተፃፍትን መቅሰፍቶች ይጨምርበታል ። ማንም በዚህ በትንቢት መጽሐፍ ከተፃፍት ቃሎች አንዳችን ቢያጎድል በዚሕ መፃፍ ከተፃፍት ከሕይወት ዛፍ እና ከቅድስቲቱ ከተማ እግዚአብሔር እድሉን ያጎልበታል " ሚለው ቃል በመጥቀስ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ጨምራለች ብለው ይሞግታሉ ። ነገር ግን ይሕን አባባል በጥሞና ስናጤ ነው የዮሐንስ ራዕይን ብቻ የሚመለከት እንጂ ሌሎቹን የማይመለከት ሆኖ እናገኘዋለን ። "በዚህ በትንቢት መፅሐፍ " አለ እንጂ ከዚሕ መጽሐፍ ቅዱስ ውጪ አላለም ። ይሕም ሚያሳየን የተጠቀሰው ምዕራፍ የዮሐንስ ራዕይን ብቻ ሚመለከት መሆኑን ነው ። መጽሐፍ ቅዱስም እንዲሁ አንድ ላይ ተጠረዞ ሆኖ የተገኘ ሳይሆን በተለያየ ዘመናት በተላያየ ግዜ የተፃፍ ናቸው ። ፀሐፊዎቹም የተለያዩ ናቸው እንጂ አንድ ሰው አንድ ግዜ ሁሉኑም የፃፍቸው አይደለም ።

ይህ ቃል የተጠቀሰበት የራሱ የሆነ ምክንያት አለው ክርስቲያኖች ክርስትናን ያስፍፋት በቀላል እንዳልነበር ከማናችንም የተሰወረ አይደለም ። [በተለይ የሮም ቤተክርሰቲያን በክርስትያኖች ላይ ያልመዘዙት ሰይፍ ። ያላሳረፍት የመከራ ዱላ አልነበረም ። በዘመነ ሰማእታት ክርስቲያኖች እንደሽንኩርት ሲቀረደዱ ቅዱሳት መጻሕፍትም የእሳት አዱኛ ሆነው ነበር ። ክርስትያኖች መከራውን አሳልፈው በእግዚአብሔር ሐይል ሰላም በሆነበት ግዚ ከቅዱሳት መጽሐፍ ሁሉም ሲገኙ የዮሐንስ ራዕይ ግን ይጠፍል ። በዚህም አዝነው ሳለ የዮሐንስ አፈወርቅ በግዞት ሳለ ግዚ ስለዚህ መጽሐፍ መቃጠል ያዝን ነበርና መጽሐፍ ቅዱሱን ዮሐንስ ሐዋርያ ፍጥሞ በተባለች ደሴት ያየውን አንድም ሳያስቀር እግዚአብሐር ገልጦለት ፅፎታል ። በዚህም በመዝጊያው ላይ መሳጠንቀቂያ አሰፈረበት ። (ዮሐንስ ሐዋርያ የያውን ሁሉንም እግዚአብሔር ገልጦልኝ ፃፍኩት ያጎደልኩትም የቀነስኩትም የለም ሲል )ሌሎች እንዳይጨምሩም እንዳይቀንሱም ይህን ቃል ጠቅሷል

ዲያቆን ፍፁም ከበደ



https://t.me/ZDfitsumkebede
https://t.me/ZDfitsumkebede
4.6K views✞£iŧsûm✞, 06:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-04 11:40:41
"ሦስት ነገሮችን እፈራለሁ"

ዛሬ (ሰኔ 27) በዓሉን የምናከብረው ሶርያዊው አባታችን ቅዱስ ያዕቆብ ዘሥሩግ: በልጅነቱ ከእናቱ ዕቅፍ ወርዶ ወደ ቤተ መቅደስ ሮጦ: ኋላም ካህኑ አቅፈው ካቆረቡት በኋላ "ሦስት ነገሮችን እፈራለሁ" ብሎ ነበር።

"አንሰ እፈርህ ሠለስተ ግብራተ ወይእቲ
ጸአተ ነፍስ እምሥጋ፤
ወተራክቦ ምስለ እግዚአብሔር፤
ወጸአተ ፍትሕ ላዕሌየ
-
ሦስት ነገሮችን እፈራለሁ። እኒህም
የነፍሴ ከሥጋዬ መለየት፤
ከእግዚአብሔር ጋር መገናኘትና
ፍርድ መስማት ናቸው" እያለ ማልቀስ ጀመረ።

የነፍስ ከሥጋ መለየት ቅዱሱን እንዲህ የሚያስፈራ ከሆነ እኛን ኃጥአኑን እንዴት ማስፈራት ይገባው ይሆን?

በእግዚአብሔር ፊት መቆምና እግዚአብሔርን ማግኘት ለምግባረ ሰናዩ ደራሲ እንዲህ የሚያስደነግጥ ከሆነ ለእኛ በየዕለቱ በክፉ ምግባር ለምናድፈው ምን ያክል የሚያንቀጠቅጥ ይሆን?

ሃይማኖቱና ምግባሩ የሰመረለት ይህ ቅዱስ በራሱ ላይ የሚሰማው ፍርድ እንዲህ የሚያርደው ከሆነ: እኛ ከእጅ ጣት ቁጥር የማይበልጥ መልካምነት ያለን የጽድቅ ምንዱባን ምን ያክል ልንፈራ ይገባን ይሆን?

የቅዱስ ያዕቆብ ዘሥሩግ በረከት አይለየን። ምግባራችንን ያቅናልን!


ዲያቆን ሕሊና በለጠ


https://t.me/ZDfitsumkebede
https://t.me/ZDfitsumkebede
5.5K views✞£iŧsûm✞, 08:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-03 11:02:36
"ዱባ እና ትውልዱ"

ዱባ፦ በቤተክርስትያንናችን አስተምህሮ ከቤተክርስትያን ቅጥር ውስጥ እንዲገባ አይፈቀድም ብለው ሲያስተምሩ ከአውደምሕረቱ ሚስጥሩን ለማወቅ ጓጉቼ እጠብቅ ይዣለው ዱባ ደግሞ ከምግብነት ባለፈ ትርጉም ይኖረው ይሆን!! በእርግጥ የኔ አለማወቅም ገና ብዙ ትምህርት ንባብ እንደሚያስፈልገው ትዝብት ጥሎልኝም አልፏል መለስ ከማለቴ እንዲህ እያሉ ሊያመሰጥሩ መደንርደሪያ ይዘሩ በትዝብት ጀምረዋል አንዳንዴ ከቤተክርስቲያን ዱባና ቅል ሲገባ ሳይ ይገርመኛል በተለይ የከተማ ደብራት ላይ ይስተዋላሉ ይህ አለማወቅ ነው አሉ ጮክ ብለው ቁጣም ምክርም አዘል በሆነ ቃል ። ዱባ ወጨው ብዙ ነው ሚጣለው ከውስጥ ማለት ነው ። ትውልዱና ዱባው ተመሳስለውብኛል ያው ናቸው ሚጣል ነገር ውስጣቸው በብዛት ከመብዛቱ የተነሳ ። ትውልዱ ክፍቱ ተጣይ ነው ፤ ለተፈጠረለት ሰዋዊ ማንነት መቆም ያልቻለ ትውልድ ተጣይ ነው ። ብቻ አደር ባይነቱ በሰፍው ምድር ላይ ምድሩ ሳይሆን እሱ አስተሳሰቡ ጠቦ መገኘቱ ተጣይ ነው ፤ ተነካው እንጂ ነካውብሎ አምኖ መቀበል የጎደለው ጉድለቱን ሚነገረው ሳይሆን ያልሆነውን ነህ እያለ ሚሞላው መፈለግ መሻቱ ሁሉ ተጣይ ነው። ሁለት ጆሮ ቢኖር አንዱ እራስ ማዳመጫ አንዱ የሌላውን ማዳመጫ መሆኑን መርሳት የቻለ ትውልድ ተጣይ ነው። ከዚህ አመለካከት እንወጣ ዘንድ ምክሬ ነው ጨረስኩ ።


ዲያቆን ፍፁም ከበደ

https://t.me/ZDfitsumkebede።
https://t.me/ZDfitsumkebede።
5.2K views✞£iŧsûm✞, 08:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-02 13:42:53
የቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርስቲ በተለያዩ ትምህርት ዘርፎች ከዲፕሎማ እስከ ሁለተኛ ዲግሪ ዘርፍ ያስተማራቸውን 530 ደቀ መዛሙርት አስመረቀ ።

የቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርስቲ ያስማራቸውን ተማሪዎች ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት :

ብፁዕ አቡነ ፊልጶስ የዩኒቨርስቲው ፕሬዚዳንት እና የደቡብ ኦሞ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት የክብር እንግዶች በተገኙበት የምረቃ ሥነ ሥርዓት ተከናውኗል ::

ተመራቂዎች ሁላቹሁ እንኳን ደስ አላቹሁ !!!

ምንጭ የኢኦተቤ መገናኛ ብዙኃን አገልግሎት


https://t.me/zdfitsumkebede
https://t.me/zdfitsumkebede
5.2K views✞£iŧsûm✞, 10:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-02 10:13:05 አትድገመው


በሕይወት ጉዞ ውስጥ ደጋግመን የምናደርጋቸው ብዙ ነገሮች ያሉትን ያክል የማይደገሙ ነገሮችም አሉ በቤተ ክርስቲያን ምሥጢራት ውስጥ የማይደገሙና የሚደገሙ ነገሮች መኖራቸውን ሁላችሁም ታውቃላችሁ።በያንዳንዳችንም ሕይወት ውስጥ የሚደገሙ እና የማይደገሙ ብዙ የሕይወት ምሥጢራት አሉ
ልደት ይደገማል፣ ሞት ይደገማል፣ መብል መጠጥ ይደገማል፣ ቁርባን ይደገማል በጎ ንግግር ይደገማል ሌላም የሚደገሙ ነገሮች ሊኖሩ ይችላሉ።
በል አንተም ደግመህ ደጋግመህ ተወለድ ከማኅፀነ አንስት በሥጋ፣ ከማኅፀነ ዮርዳኖስ በመንፈስ፣ ከማኅፀነ ኃጢአት በንስሐ፣ ከከርሰ መቃብር በትንሣኤ መወለድ ትችላለህ። ከዚያም በላይ ራስህን በመልካም ሥራ ውለድ እንጅ ከማንም በመወለድህ የምትኮራ አትሁን።
መወለድ መልካም ሰለሆነ ክርስቶስ እንኳን ሁለት ልደታትን ተወለደ
ይህ ሁሉ የልደት ድግግሞሽ ለምን ይመስልሃል? አንተ በሕይወት እንድትኖር እኮ ነው። ምክንያቱም ሞት የሚደገም ሆኖ ሳለ ሕይወት የማትደገም ስለሆች ነው ሕይወት አንዲት ናት አትደገምም ትዳር አይደገምም ክፉ ቃል አይደገምም
ምስጋና ግን ይደገማል ለዚህ ነው ጌታ በመጀመሪያ ስብከቱ ብቻ ዘጠኝ ጊዜ ብፁዓን ብፁዓን ብሎ ተናግሯል። ወንጌል በምስጋና ተጀምራ በምስጋና የምትፈጸም የምስጋና መጽሐፍ ናት።
አንተ ግን ርግማንን ትደግማለህ ስህተትን እንደ ጥሩ አጋጣሚ ትቆጥራለህ ባንድ ቀን ስህተት በዘመንህ ሁሉ በኅሊና ወቀሳ ሥር ትኖራለህ እባክህ ኃጢአት አይደገምም ይህን ብታደርግ ደጋግመህ ትሞታለህ ስህተትን ብትደግም ለዘለዓለም በማያቋርጥ ቅጣት ውስጥ ትኖራለህ
በነገራችን ላይ ስህተትን አትድገም ስል አንድ ጊዜ አድርግ ማለቴ አይደለም ያሰብከውን በገቢር ወይም በነቢብ አትድገመው ለማለት ነው።(ሊቀ ሊቃውንት ስምዓ ኮነ)



ዲያቆን ፍፁም ከበደ


https://t.me/zdfitsumkebede
https://t.me/zdfitsumkebede
5.1K views✞£iŧsûm✞, 07:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-01 08:34:33
የሴቷ ፈጣሪ

ጌታ እግዚአብሔር ወንድ ልጅ ለመፍጠር ብዙ አልደከመም። ከመሬት አፈር አንሥቶ አንድ ወንድ ፈጠረ!! ስሙንም አዳም አለው!! ሴት ሊፈጥር ሲል ጊዜው መሸበት። ከመፍጠር አረፈ። በሳምንቱ ሴት ሊፈጥር አስቦ ነበር። በወቅቱ ግን ደመ ግቡ ሴት ሊፈጥር ሲል ምክንያተ ስሕተት ሆና ታየችው። መፍጠር ቢታክተው ከወንድ ጎን ከፈላት። በቃ!!
ከዚህ በኋላ ብዙ ጠቢባን ተነሥተዋል። ሴት ልጅን ለመፍጠር ደክመዋል። ከዓለማየሁ ዋሴ በቀር ሴትን የፈጠረ የለም።
ወዳጄ ዶር ዓለማየሁ ግን ከዱዳሌብ አፈር ከሰማይ አየር ነሥቶ እንደ ሊጥ አቦካው። ከዚያ በብዕሩ እያጣቀሰ ይቺን ደመ ግቡ ሴት ፈጠረ። ስሟንም ሚተራሊዮን አለው!! ጌታም ይቺን ፍጥረት ሊያይ ከሰማይ ወረደ!! ዶክተሩ በመፍጠር እንደመሰለው ዐይቶ አደነቀ!!
(ማዕበል ፈጠነ የቅኔው ሊቅ )

እንዲህ አርጎ ስለ ገለፀው መጽሐፍ ጸሐፈ ሊቁ ያለውን ላካፍላቹሁ ወደድኩ ይበልጥ መጽሐፍን ብታነቡት ይህቺ ሴት ማን እንደሆነች ትገነዘባላቹሁ ያነበባቹሁም ድንቅስ አርጎ ገለፃት ብላቹሁ ትገረማላቹሁ!!! ።


ዲያቆን ፍፁም ከበደ

https://t.me/zdfitsumkebede
https://t.me/zdfitsumkebede
5.3K views✞£iŧsûm✞, 05:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-30 11:56:32 +++ የጀማሪ ጠባይ +++

መንፈሳዊ ሕይወትን ገና ስትጀምረው ለፍጹምነት ጥቂት የቀረህ ያህል ይሰማሃል። አንተ ጋር ያለው ደስታ እና ሰላም ሌሎች ጋር የሌለ ይመስልሃል። በዚህች ሁከት በሞላባት ዓለም አንተ ብቻ ክርስቶስን እንዳገኘኸው ታስባለህ። የቀረው ሕዝበ አዳም እንዲሁ በከንቱ ሲርመሰመስ የሚውል ባካና ሆኖ ይታይሃል። ታዝንለታለህ፣ አይይይ ይህ ኃጢአተኛ ሕዝብ ምን ይሻለዋል? ትላለህ።

የእውነተኛ መንፈሳዊ እድገት መገለጫ ግን ይህ አይደለም። ሰው ወደ እግዚአብሔር እየቀረበ ሲመጣ ከሌላው ሰው ይልቅ የራሱ ጉድለት ይታየዋል። መንፈሳዊነት የሚገልጥልህ ሰዎችን ተመልክተህ የምትፈርድበትን ውጫዊ ዓይንህን ሳይሆን ራስህን አይተህ የምትወቅስበት የውስጥ ዓይንህን ነው። መንፈሳዊ ሕይወትህ ሲጎመራ "አይ ሰው" ሳይሆን "አይ እኔ!" ያሰኝሃል። አባ ማቴዎስም እንዲህ ይላል "ሰው የበለጠ ወደ እግዚአብሔር ሲቀርብ ይበልጥ ኃጢአተኛ መሆኑ እየታየው ይመጣል። ነቢዩ ኢሳይያስ እግዚአብሔርን ካየ በኋላ ከንፈሮቼ የረከሱብኝና የጠፋሁ ሰው ነኝ እንዳለ።"

ከብቃት ደርሰህ መላእክት ሲወጡና ሲወርዱ ቢታዩህ እንኳን ሁሉ እንዳንተ ስለሚመስልህ እንደ ዮሐንስ ሐጺር "ሚካኤል ይበልጣል ወይስ ገብርኤል?" እያልህ ከአጠገብህ የቆመውን ትጠይቃለህ እንጂ "አይይ አንተ እንኳን ገና አልበቃህም። ብዙ ይቀርሃል" ብለህ ወዳጅህን አታናንቅም። ይልቅ "ለእኔ ብቻ ገልጦ ለሌላው እንዲሰውር የሚያደርገው ምንም ቁም ነገር የለኝም" በማለት ከወንድምህ የተሻልህ እንዳልሆንክ በፍጹም ልብህ ታምናለህ።

ለመንፈሳዊ ሕይወት አዲስ ስትሆን ገና ጥቂት ጸልየህ፣ ጥቂት ጾመህ፣ ጥቂት መጽውተህ ሳለ ግን ሩጫህን ወደ መጨረሱ የተቃረብህ ይመስልሃል። ጉዞህን በግማሽ እርምጃ ከመጀመርህ ከፍጻሜው ላይ የደረስህ ያህል ይሰማሃል። "እኔን ምሰሉ" ማለት ያምርሃል። ነገር ግን መንፈሳዊ ሕይወት የቱንም ያህል ብትሮጥበት ሁል ጊዜ እንደ ጀማሪ የሚያደርግ ረጅም ጎዳና ነው። ሰማንያ ዓመት በገዳም ሲጋደል የነበረው አባ ሲሶይ ነፍሱ ከሥጋው ልትለይ በቀረበች ጊዜ ብዙ መነኮሳት በአልጋው ዙሪያ ከበውት ሳለ ቅዱሱ "አምላኬ ሆይ፣ እባክህ ለንስሐ የሚሆን ጥቂት ጊዜን ስጠኝ?" እያለ በልቅሶ ሲማጸን ሰሙት። በዚህ የተገረሙት መነኮሳቱ አባ ሲሶይን "አባታችን አንተ እድሜ ልክህን በንስሐ የኖርህ መምህረ ንስሐ ሆነህ ሳለ እንዴት አሁን ጥቂት የንስሐ ጊዜን ትለምናለህ?" ቢሉት፣ ቅዱሱም "ልጆቼ ይህን መንፈሳዊ ጥበብ (ንስሐን) ገና አሁን መጀመሬ ነው" አላቸው።

ጌታ ሆይ መንፈሳዊ ሕይወት እኖር ዘንድ አስጀምረኝ፤ ገና ጀማሪ ሳለሁ ደርሻለሁ ከማለትም ሰውረኝ። እንድቆም አትፍቀድልኝ፤ ወደ አንተ ሳበኝ፣ አሳድገኝ።

ዲያቆን አቤል ካሳሁን
ሰኔ 22፣ 2014 ዓ.ም.
አዲስ አበባ


https://t.me/zdfitsumkebede
https://t.me/zdfitsumkebede
5.7K views✞£iŧsûm✞, 08:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ