2022-09-24 08:12:49
✞በዓለ መስቀል✞
ቤት ከነጉልላቱ ቅጽር ከነማዕዘንቱ መውረስ የሚችለው በኩር ነው፡፡ ሀገራችን የብሉይም የሐዲስም በኩረ አሚን ናትና የጽላት እና የመስቀል ወራሽ ናት፡፡
መስቀል ከመስከረም 10ቀን ተቀጸል ጽጌ ጀምሮ እስከ መስከረም 25ቀን በበዓልነት መስቀል ይከበራል፡፡
ይኸውም ወደኢትዮጵያ ከገባበት ከ ሦስት ዓመት ከሦስት ወር ባርኮተ ኢትዮጵያ በሁዋላ ግሸን አንባ እስከተቀመጠበት ድረስ ያለውን ያሳያል፡፡
መስቀል ለእኛ ለኢትዮጵያውያን ድርብ በዐል ነው በእሌኒ የተፈጸመው ታሪክ እና ወደሀገራችን የመጣበት ሲደመር በሰንበት ላይ ደብረ ዘይት ነው፡፡
ንዑስ ደመራ የህዝብ ነው ዐቢይ ደመራ ግን አጤ ደመራ ይባላል፡፡
1 ሕጨጌ ደመራ ፦የአቡኑ
2 ሐጤ ደመራ ፦የንጉሡ
3 እቴጌ ደመራ ፦የንግሥት
4 ባለጌ ደመራ ፦ የባለጊዜ ነው፡፡
በዋዜማው የሚቃጠለው ህዝበ ደመራ ይባላል በየመንደሩ የሚደረግ ህዝቡ በአቅራቢያው የሚያከብረው ነው፡፡ይህ ሥርዓት በሁሉም ቦታዎች ያለ ቢሆንም ይልቁንም በጎንደር እንደተጠበቀ ይገኛል፡፡
በ17ጧት አጤ ደመራ ይባላል ሁሉም በአንድነት ከንጉሥ ደመራ በመገኘት የሚከበር ነው፡፡
ደመራው ከተቀጸል ጽጌ ገብረ መስቀል ሐጼጌ ጀምሮ ለዘመናት በቅዱስ ቅብብሎሽ ነው የመጣው፡፡በተቀጸል ጽጌ የጌታ አክሊለ ሦክ አምሳል በጉንጉን አበባ ለንጉሡ ይሰጣል አሁን የንጉሡ አክሊለ ሶክ ተቀጸል ጽጌ ማረፊያ ቢያጣ በደመራው ይቀመጣል፡፡
ደመራ ትናንትን የምናይበት እውነት ነው
ዛሬም የምኖርበት አሁን ነው
ለነገም የምንመለከትበት ፍኖተ ህሊና ነው፡፡
ትናንት መሠረት፣ዛሬ ግድግዳ፣ ነገ ጣራ ነው፡፡ትናንት የሌለው ዛሬ የለውም፡፡ዛሬ የሌለውም ነገ ምናብ ነው፡፡
ደመራ፦ ወድሙር ኩሉ ንዋዮሙ፡፡
(መምሕር ገብረ መድኅን እንየው )
https://t.me/zdfitsumkebe
https://t.me/zdfitsumkebe
https://t.me/zdfitsumkebe
2.2K views✞£iŧsûm✞, 05:12