2022-09-08 06:55:26
ጳጉሜ 3 ቅዱስ ቅዱስ ሩፍኤል
በቁስል ላይ የተሾመው ከከበሩ መላእክት አንዱ ቅዱስ ሩፋኤል ነው ሄኖ 6+3
መላእክት በተለያየ ተግባራት ላይ የተሾሙ ናቸው
መላእክት ስንል በሁለት ይከፈላሉ
ቅዱሳን መላእክትና ርኩሳን አጋንንት ተብለው
ቅዱሳን መላእክት በስራቸው ተቀድሰዋል ከብረዋል
ርኩሳን መላእክት በስራቸው ረክሰዋል ተዋርደዋል
ስራ ያረክሳል ስራ ይቀድሳል
የወደቁ መላእክት ርኩሳን እንላቸዋለን
የተቀደሱ መላእክትን ቅዱሳን እንላቸዋለን
ቅዱሳኑ በረቂቁ ዓለም ላይ ይኖራሉ መላእክት ረቂቃን ስለሆኑ በረቀቁ ሰማያት ላይ ይኖራሉ
ግዙፍ በግዙፍ ቦታ ይኖራል ረቂቅ በረቂቅ ቦታ ይኖራል ሰማያት ረቂቃን ናቸው ብሩሃን ናቸው መላእክትም ረቂቃን ብሩሃን ናቸው በሰማያት ይኖራሉ በመላእክት ዘንድ ጨለማ የለም
መጋቤ ሐዲስ ሄኖክ ፈንቴ
ፀሐይ ከሰማይ በታች ላሉ ፍጥረታት ታበራለች ለመላእክት አታበራም መላእክት ራ ሳቸው ብርሃን ናቸው ብርሀን ለጨለማ እንጅ ለብርሃን አይጠቅምም
አጋንንት ረቂቃን ቢሆኑም ቦታቸውን መዓርጋቸውን ክብራቸውን አጥተው ከመኖሪያቸው ከሰማያት ተባረው በጨለማው ዓለም ላይ ይኖራሉ ጨለማ ከጨለማ ጋር ተደምሮ ይኖራል
የእያንዳንዱ መልአክ የስራ ድርሻ አለው
አጋንንትን ደል በመንሳት ላይ የተሾመ መልአክ አለ
መካኖችን በማብሰር የተሾመ መልአክ አለ
መባርቅትን በማዘዝ የተሾመ መልአክ አለ
ደመናትን ውሃ አዝለው እንዲያዘንሙ የተሾመ መልአክ አለ
ዝናማትን መጥኖ በማዝነም የተሾመ መልአክ አለ
እጽዋት እንዲያለመልሙ እንዲያብቡ የተሾመ መልአክ አለ
ነፋሳት በምሕረት እንዲነፍሱ የተሾመ መልአክ አለ
ወንዞች ያለ ልክ ሞልተው ምድርን እንዳይደመስሱ የተሾመ መልአክ አለ
ሰው ያለጊዜው እንዳይጠፋ የተሾመ መልአክ አለ
በእንስሳት ላይ የተሾመ መልአክ አለ
በአራዊት ላይ የተሾመ መልአክ አለ
በአእዋፋት ላይ የተሾመ መልአክ አለ
ምድር የዘሩባትን እንድታበቅል የተሾመ መልአክ አለ
ቋንቋ ለመግለጥ የተሾመ መልአክ አለ
ሀገር ለመጠበቅ የተሾመ መልአክ አለ
ሕጻናትን በመጠበቅ ላይ የተሾመ መልአክ አለ
ቤተ ክርስቲያንን በመጠበቅ የተሾመ መልአክ አለ
በትዳር በማኅጸንና በቁስል ላይ የተሾመው መልክ ቅዱስ ሩፋኤል ነው
ሩፋኤል ማለት እግዚአብሔር ሐኪም ነው ማለት ነው
ቅ ሩፋኤል
መልአከ ከብካብ ይባላል
ሳራ ወለተ ራጉኤልን እና ጦብያ ወልደ ጦቢት አጋብቷልና
ፈታሔ ማኅጸን ይባላል
በሰይጣን የተዘጋው የሳራን ማኅጸን ፈቷልና ወላዶች ሲወልዱ በምጥ ጊዜ ማህጸንን የሚፈታ መልአክ ነው
ሰዳዴ አጋንንት ይባላል
አስማንድዮስን ከሳራ ጭን አውጥቶ አባሮታልና
, ፈዋሴ ዱያን ይባላል
የቆሰሉ ቁስለኞችን ይፈውሳልና
ምእራገ ጸሎት ይባላል
የዓመቱን ሁሉ ጸሎት የሚያሳርገው ቅዱስ ሩፋኤል ነውና
ከሳቴ አእይንት ይባላል
የታወረው የጦቢትን ዓይን አብርቷልና
❖ቅ ሩፋኤል ጳጉሜን 3 አራት መሰረታዊ ነገሮችን የፈጸመበት ዕለት ነው
1 አስማንድዮስን ከሳራ ጭን ድል ነስቶ ጦብያና ሳራን ያጋባበት የጦቢት እና የራጉኤልን ቤት የረዳበት ቀን ነው
አስማድዮስ የተባለው ሰይጣን ጸረ ትዳር ነው ሳራ ስታገባ ባሏን ይገልባት ነበር በየጊዜው ስታገባ እየገደለባት 7 ባሎች ሙተውባት በጭንቀት ትኖር ነበር ከዚህ በሇላ መልአኩ ቅ ሩፋኤል የአሳ ጉበት እጣን ጨምሮ ጦብያ እንዲያጥናት አዞት ጦብያ ሲያጥናት ከጭኗ አድሮ ቧሎቿን የሚገድልባት ሰይጣን አስማድዮስ እየጮኸ ከላዯ እንዲዎጣ ያደረገበት ቀን ነው
2 የታወረው የጦቢትን ዓይን ያበራበት ዕለት ነው
ጦቢት ደግ ሰው ነበርና የሞተ ሳይቀብር አይበላም ነበር ከዕለታት አንድ ቀን አንድ ሰው ተገሎ ዛፍ ስር ተጥሎ አየ ይህ ሰው የተገደለው በንጉሥ ነው
ነገሥታት ሥልጣናቸውን ለማቆየት ሲሉ የሚቃዎማቸውን ይገድላሉ እነሱ ለመኖር ሌላ ይገላሉ ንጉሡም እሱ በሥልጣን ለመኖር ነበር የገደለው
ሰው ፈርቶ መቅበር አልቻለም የከፍዎች ነገስታት ጭካኔ ከገደሉ በሇላ እንዳይቀበር ይከለክላሉ
ይህ ሰው እንዳይቀበር አዋጅ ወጥቶ ነበር ያን ጌዜ ጦቢት አጥቦ ሲገንዘው ወደላይ ቀና ሲል ወፍ ኩሷን ከዓይኑ ላይ ጥላበት ዓይኑ ጠፍቶ ነበር
መልአኩ ሩፋኤል የጦቢትን ልጅ ጦብያን ዓባትህን የአሳውን ሐሞት ዓይኑን ቀበው ብሎ አዞት ሲቀበው ዓይኑ በርቶለታል
3 በውሃ ላይ የታነጸችውን ቤተ ክረርስቲያኑን ያጸናባት ዕለት ነው
የቅዱስ ሩፋኤል ቤተ ክርስቲያን ከባህር ላይ ተሰርታ
አሳ አንበሪው ሊገለብጣት ሲል መልአኩ አሳ አንበሪውን በረምሁ ወግቶ እንዳትንቀሳቀስ ቁም ብሎ
በአሳ አንበሪው ላይ ቤተ ክረርስቲያኑ ጸንታ እንድትኖር ያደረገበት ዕለት ነው
4 የዓመቱን ጸሎት ወደአምላክ የሚአሳርግበት ዕለት ነው
ለአንድ ዓመተ ሙሉ የተጸለየው ጸሎት ቅድመ እግዚአብሔር የሚደርሰው ጳጉሜን ሶስት
በመልአኩ ቅዱስ ሩፋኤል ነው
ቀኑም ርኅወተ ሰማይ ይባላል የሰማይ መከፈት ቀን ማለት ነው ነገር ግን ሰማይ የሚዘጋ የሚከፈት ሁኖ አይደለም የተጸለየው ጸሎት ሰማያትን አልፎ ቅደመ እግዚአብሔር ስለሚደርስ ነው እንጂ
ጳጉሜን 3 ቅዱስ ሩፋኤል ከደረጋቸው ተዓምራት መካከል እነዚህ ናቸው የቅዱስ ሩፋኤል አማላጅነት አይለየን
(መጋቤ ሐዲስ ሄኖክ ፈንቴ)
የቻናሌ ቤተሰቦች እንኳን አደረሳቹ።
ዘማሪ ዲያቆን ፍፁም ከበደ
JOINE JOINE
https://t.me/zdfitsumkebe
https://t.me/zdfitsumkebe
https://t.me/zdfitsumkebe
484 views✞£iŧsûm✞, 03:55