Get Mystery Box with random crypto!

ዘማሪ ዲ/ን ፍፁም ከበደ

የቴሌግራም ቻናል አርማ zdfitsumkebe — ዘማሪ ዲ/ን ፍፁም ከበደ
የቴሌግራም ቻናል አርማ zdfitsumkebe — ዘማሪ ዲ/ን ፍፁም ከበደ
የሰርጥ አድራሻ: @zdfitsumkebe
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 22.71K
የሰርጥ መግለጫ

ዘማሪ ዲያቆን ፍፁም ከበደ

Ratings & Reviews

5.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

2

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 30

2022-08-23 14:15:59
ታላቅ መንፈሳዊ ጉባኤ



አይቀርም

vedio አውርደው ጥሪውን ይመለከቱ ዘንድ እናሳስባለን

በአዶላ ደብረ ገነት ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን ከሐምሌ 21 እስከ 24 ድረስ በተጋባዥ መምህራን እና ዘማርያን ተዘጋጅቶላችኋል። በዕለቱም የሃገረ ስብከታችን ሊቀ ጳጳስ የሆኑት ብፁዕ አቡነ ዜና ማርቆስ በጉባኤው ላይ በመገኘት ይባርኩናል አባታዊ ቃላቸውን ያስተላልፉልናል። ላልሰሙት እያሰማችሁ በጉባኤው በመገኘት ወንጌልን ይማሩ እግዚአብሔርን በዝማሬ በማመስገን በረከት ያግኙ። የፃድቁ አቡነ ተክለሃይማኖት በረከት ይደርብን። አሜን


Share share share
3.7K views✞£iŧsûm✞, 11:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-23 05:54:59





ድንቅ ዝማሬ share
3.3K views✞£iŧsûm✞, edited  02:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-22 19:21:04 አባቶቻችን፥ መሐሪው ጌታ እኛን የወደደበትን ዘላለማዊ ፍቅርንና ለእኛ ያደረገውን የማዳን ሥራ በመጽሐፈ ቅዳሴ፦ “ኦ እንተ አፍቀርካ ለዛቲ ዘመድነ - ይህችን ባሕርያችንን የወደድሃት ሆይ” በማለት አድንቀዋል። እኛም ለእመቤታችን የተደረገው (ለአምላክ እናትነት መመረጧ፥ ዘላለማዊ ድንግልናዋ፥ ከፍጡራን ማንም የማይስተካከለው ቅድስናዋ፥ ከሞት ተነሥታ ማረጓ) ለድኅነታችን (ለመዳናችን) የተደረገና የእኛን ሰብዓዊ ባሕርይ ልዩ ክብር (glory) የሚያንጸባርቅ ስለሆነ በዚህ ሁሉ ደስ ይበለን፥ ሐሴትም እናድርግ። በሔዋን የተዋረደው ሰብዓዊ ባሕርያችን በዳግሚት ሔዋን (በድንግል ማርያም) ስለከበረ እንደ አባቶቻችን ትምህርት እመቤታችንን፦ “ትምክሕተ ኵልነ/ ትምክሕተ ዘመድነ” እንበላት። 

ይህን እውነት ሲያመሰጥር፥ በሶርያዊው ቅዱስ ያዕቆብ ዘሥሩግ ስም የሚጠራው የኢትዮጵያውያን አባቶቻችን አኰቴተ ቊርባን፦ “ወካዕበ ተማኅፀነ በማርያም እምከ እንተ ይእቲ እግዝእትነ ወትምክሕተ ዘመድነ በወሊዶተ ዚአከ - ዳግመኛም በእናትህ በማርያም ተማፅነናል፤ ይህችውም አንተን በመውለድ እመቤታችንና የባሕርያችን መመኪያ ናት” ይላል (ቊ. 99)።

በመጨረሻም፥ ሄኖክ አካሄዱን ከእግዚአብሔር ጋር ስላደረገ አምላኩ እንደወሰደው (ዘፍ. 5፥24)፥ ለአምልኮተ እግዚአብሔር ቀናዒ የነበረው ነቢዩ ኤልያስም በእሳት ሰረገላና በዐውሎ ነፋስ ወደ ሰማይ አንደተነጠቀ (2 ነገ. 2፥ 11) ከመጽሐፍ ቅዱስ ያነበበ ሰው፥ የወላዲተ አምላክ ድንግል ማርያም ወደ መንግሥተ ሰማያት መወሰድ ጥያቄ ሊፈጥርበት አይገባም። “እነሆ፥ ሰማይ ከሰማያትም በላይ ያለው ሰማይ ይይዝህ ዘንድ አይችልም” (1 ነገ. 8፥27) የተባለለትን አምላክ፥ ድንግል ማርያም በማኅፀንዋ ተሸከመችው። ስለሆነም “ዳግሚት ሰማይ፥ ዳግሚት አርያም፥ ሰማይ ዲበ ምድር (በምድር ላይ ያለች ሰማይ)” ተባለች፤ ወንድሞቻችን ኦርቶዶክሳውያንም እንደ እኛ አባቶች፦ “O St. Mary, your womb is more spacious than the heavens” ብለው ዘመሩ። 

ስለዚህ የድንግል ማርያምን ወደ ሰማይ ማረግ (ዕርገት) እየተቃወሙ የትዕቢት ቃላትን ከመሰንዘር ይልቅ፥ ኦርቶዶክሳዊውን አስተምሕሮ በትሕትና በመማር፥ ዳግሚት ሰማይ (ድንግል ማርያም) በዕለተ እሑድ ከተፈጠረው ሰማይ ጋር ኅብረት በማድረጓ እጹብ እያልን እናድንቅ፤ ይህን ሁሉ ላደረገ አምላካችንም የከንፈራችንን ፍሬ የምስጋና መሥዋዕት አድርገን እናቅርብለት (ዕብ. 13፥15) ።

ማደሪያ መቅደሱን ያከበረ መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በቅድስት እናቱ ጸሎትና ልመና በሰማያውያንና ምድራውያን በረከቶቹ ሁሉ ይባርከን፤ ለቅዱሳን አባቶቻችን የሰጠውን የእመቤታችንን የእናትነት ጣዕምና ፍቅር ያብዛልን።

Dr.kesis Mebrtu kiros

https://t.me/akanim1wasen2
3.2K viewsወሰንየለው ባህሩ, 16:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-22 19:21:04 ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን):
“በውድዋ ላይ ተደግፋ ከምድረ በዳ የምትወጣ (የምታርግ) ይህች ማን ናት?”
                                                                                              መኃልየ መኃልይ ዘሰሎሞን 8፥5

በክርስትና ስም ከሚጠሩ ቤተ እምነቶች በተለየ መልኩ፥ “ቀጥተኛ መንገድ” የሚል ትርጉም ያለው የኦርቶዶክስ እምነትን የሚከተሉ አብያተ ክርስቲያን ለተቀደሰው ሐዋርያዊ ትውፊት (Holy Tradition) ትልቅ ቦታ አላቸው። ቅዱስ ትውፊት የምንለው ከቅዱሳን ሐዋርያት አባቶቻችን ዘመን ጀምሮ ከትውልድ ወደ ትውልድ ሲሸጋገር የመጣውን አስተምህሮ እና ሥርዓተ አምልኮ ሲሆን፥ መጽሐፍ ቅዱስም እኛ ዘመን የደረሰው በዚሁ የተቀደሰ የትውፊት ሰንሰለት ነው። ለዚህም ነው ኦርቶዶክሳውያን አበው፦ “መጽሐፍ ቅዱስ፥ በተቀደሰው የትውፊት ዛፍ ላይ የበቀለ መልካም ፍሬ ነው” የሚሉት።

የጥንቷ ቤተ ክርስቲያን፥ በምድረ ፍልስጥኤም በ5ኛው መቶ ክፍለ ዘመን መጨረሻ አካባቢ የወላዲተ አምላክ ድንግል ማርያምን በዓለ ዕረፍት ወፍልሰት ማክበር እንደጀመረች የሚጠቁሙ ታሪካዊ መረጃዎች አሉ። በዚሁ ዘመን “The Dormition and the Assumption of the body of St. Mary into Heaven” በሚል ርእስ ዙሪያ የሚያትቱ ጽሑፎች በተለያዩ የቤተ ክርስቲያን አባቶች ይጻፉ እንደነበር በቅርቡ የተደረጉ ጥናቶች ያመለክታሉ። ከነዚህ ጥናቶች መካከል ዓለም አቀፋዊ እውቅናን ያተረፈው የሚከተለው መጽሐፍ ነው፦ Stephen Shoemaker, Ancient Traditions of the Virgin Mary’s Dormition and Assumption, Oxford University Press, 2006. በፍልስጥኤም (Palestine) የተጀመረው “በዓለ ዕረፍታ ወፍልሰታ ለማርያም” ቀስ በቀስ ወደ ምዕራቡ ዓለም ደርሶ፥ በ8ኛውና 9ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ዓለም አቀፋዊ በዓል ለመሆን ችሏል። ይህን በዓል ኦርቶዶክሳውያን አብያተ ክርስቲያን August 15 ቀን ሲያከብሩት፥ ጥንታዊውን Julian Calendar የምትከተለው ቤተ ክርስቲያናችን ደግሞ ነሐሴ 16 (August 22) ቀን በታላቅ ድምቀት ታከብረዋለች።

“በውድዋ ላይ ተደግፋ ከምድረ በዳ የምትወጣ ይህች ማን ናት?” የሚለው የንጉሥ ሰሎሞን ዝማሬ፥ ሕይወቷን በሙሉ አምላኳን ያከበረች ነፍስ ከሥጋዋ ተለይታ ወደ፡ምትወደው ጌታ ስትሄድ የሚጠቀስ ጥቅስ ነው። ከዚህ በተሻለ መልኩ ግን፥ እመቤታችን ድንግል ማርያም በልጇ ኃይል ከሞት ተነሥታ፥ ንጽሕትና ቅድስት የሆነችውን ነፍሷን ውድ ልጇ በክብር ተቀብሎ ወደ መንግሥቱ ያሳረገበትን በዓል ለመዘከር ልንጠቀምበት እንችላለን። 

 እንዲያውም የግእዙ ንባብ፦ “መኑ ይእቲ ዛቲ እንተ ተዐርግ እም ገዳም አንተ ትትመረጐዝ በወልድ እኁሃ? - በውድዋ ላይ ተደግፋ ከምድረ በዳ የምታርግ ይህች ማን ናት?” ያላትን፥ “ሠናይት ከመ ወርኅ፥ ወብርህት ከመ ፀሐይ - እንደ ጨረቃ የተዋበች፥ እንደ ፀሐይም የምታበራ” በማለት ስለሚገልጻት፥ በፈቃድ ከሚሰራው የግል ኃጢአት ነጻ ለሆነችው ለቅድስቲቷ የእመቤታችን ነፍስ ዕርገት በእጅጉ የሚስማማ አገላለጽ ነው። ይህን መጽሐፍ ቅዱሳዊ አሳብ በሥነ-ሥዕል (iconography) ለማመልከት፥ ከስር የምትመለከቱት ኦርቶዶክሳዊ ሥዕል (icon)፥ ሐዋርያት የእመቤታችንን ሥጋ ለመገነዝ አንደተሰበሰቡና ጌታ በሕፃን ልጅ አምሳል በነጭ መጎናጸፊያ የተጠቀለለችውን የብፅዕትና ቅድስት እናቱን ነፍስ ታቅፎ ያሳያል። ጌታን በሕፃንነቱ እናቱ ቅድስት ድንግል ማርያም ታቅፈው እንደነበር፥ እርሱ ደግሞ በተራው በዕረፍቷ ቀን የእናቱን ንጽሕት ነፍስ ታቅፎ ወደ መንግሥቱ ዘላለማዊ ክብር አገባት።

በሞቱ ሞትን ድል የነሣልን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ፥ ከሞት በኋላ የሚጠብቀን ትንሣኤ በኵር እንደሆነ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ጽፎልናል (1 ቆሮ15፥20)። ይኸው ሐዋርያ ስለ ሙታን ትንሣኤ ሲጽፍ ሥጋዊ አካላችን ወደ አፈርነቱ ከተመለሰ በኋላ (በመበስበስ ከተዘራ በኋላ) መንፈሳዊ አካል ሆኖ በክብር አንደሚነሳ አስተምሮናል (1 ቆሮ 15፥ 42-50)። መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዳግም ለፍርድ ሲመጣ፥ “በጌታ የሚሞቱ ሙታን ብፁዓን ናቸው” እንደተባለ (ራእይ 14፡13) በምድራዊ ኑሮአቸው ክርስቶስን ለብሰው የኖሩ የእግዚአብሔር ልጆች የክብር ትንሣኤ ይነሳሉ። ለዚህም ነው ሐዋርያው፦ “ክቡር ሥጋውን እንዲመስል የተዋረደውን ሥጋችንን ይለውጣል” (ፊልጵ 3፥21) ሲል ስለሚጠብቀን ዘላለማዊ ክብር የነገረን።

እንግዲህ ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያናችን፦ “ወላዲተ አምላክ ማርያም ሞትን ድል ባደረገው በልጇ ኃይል ከሞት ተነስታ ወደ ልጇ መንግሥት አርጋለች” ብላ ስታስተምረን፥ የአምላካችን ልጆች የሆንን ሁላችን በእግዚአብሔር መንግሥት የሚጠብቀንን ክብር እመቤታችን ቀድማ አግኝታለች ማለቷ ነው።

 ጌታ በትንሣኤው በኵር እነደሆነን፥ ቅድስትና ብፅዕት እናቱ ደግሞ ወደ ሰማያዊው መንግሥት በመግባት ቀዳሚት (በኵር) ሆነችን። ንጉሡ ጌታችን ኢየሱስ ከመንግሥቱ የተለየበት ጊዜ ፈጽሞ እንደሌለ እናውቃለን፤ መንግሥቱ ያለው ንጉሡ ባለበት ቦታ ነውና። ሁላችን ተስፋ የምናደርገውና “ወደ ጌታህ ደስታ ግባ” (ማቴ 25፡22) የሚለው፥ በእርሱ ሕያዋን ሁነን በመንግሥቱ ለዘላለም የመኖራችን እውነታ (eschatological fulfillment) ከሁላችንም ቀድሞ ለቅድስተ ቅዱሳን ድንግል ማርያም ተደረገ። ከመለኮት ባህርይ ተካፋይ የሆንበትን (2 ጴጥ 1፥4) ምስጢር (theosis - ሱታፌ አምላክ) ከእግዚአብሔር በተሰጣት የተለየ ጸጋ በንጽሕና እና በቅድስና አጊጣ በሕይወቷ እውን ስላደረገችና ከቅዱሳን መካከል በንጽሕና የሚስተካከላት ስለሌለ፥ እመቤታችን ከቅዱሳኑ ሁሉ ቀድማ ወደ መንግሥተ እግዚአብሔር ገባች ቢባል ጥያቄ ሊፈጥርብን አይገባም። ደግሞም አምላክን በድንግልና ወልዳ ላሳገደች እመቤት የሚገባት የክብር ሰማያዊ ፍጻሜ ከዚህ ውጪ ሊሆን አይችልም።

እግዚአብሔር ወልድ ከእመቤታችን የነሳው ሥጋ የእኛ ሥጋ እነደሆነ ግልጽ ነው፤ በ318ቱ የኒቂያ ጉባኤ አባቶች ስም የተደረሰው የቤተ ክርስቲያናችን ቅዳሴ፦ “ተዘከር ሥጋ እንተ ነሣእከ እምቅድስት ድንግል እንቲአነ ሥጋ አኮ እምሰማያት ዘአውረድከ - ከቅድስት ድንግል የነሣኸው ሥጋ የእኛ ሥጋ እነደሆነ፥ ከሰማይ ያወረድኸው እንዳይደለ አስብ” እንዲል (ቊ. 121)። የመልአኩን ብስራት “ይኩነኒ በከመ ትቤለኒ” ብላ ከተቀበለችበት ቅጽበት ጀምሮ እግዚአብሔር አብ በልጁ በኩል ያደርግ ዘንድ ላሰበው የማዳን ሥራ ድንግል ማርያምን መሣሪያ አድርጓታል። ልዑል ማደሪያውን ቀድሶ፥ “ቅድስተ ቅዱሳን - Holy of Holies” የተሰኘች የአንድ ልጁ ማደሪያ ትሆን ዘንድ መረጣት። ስለዚህ የድንግል ማርያም ትንሣኤና ዕርገት በዋነኝነት የሚያመለክተው፥ እነ ቅዱስ ኤፍሬም፦ “አንቲ ውእቱ ደብተራ እንተ ተሰመይኪ ቅድስተ ቅዱሳን . . . መቅደስ ዘይኬልሉኪ ኪሩቤል” ብለው ያወደሷት የጌታ ንጽሕት መቅደስ በመንግሥቱ መክበሯን ነው። ይህ የመንግሥቱ ክብር (glorification) ደግሞ የእኛም ክብር ስለሆነ በዚህ የተቀደሰ ትውፊታው አስተምህሮ ደስ ሊለን እንጂ፥ በጭራሽ ሊከፋን አይገባም። 
2.6K viewsወሰንየለው ባህሩ, 16:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-22 09:20:23 እንኳን አምላክን በድንግልና ለወለደች ለእናታችን ለእመቤታችን ለድንግል ማርያም የእርገት በዓል አደረሰን።

"ድንግል አትለይኝ" ጥዑም ዝማሬ በዘማሪ ዲ/ን ኃይለ አብ ግርማ

ናታኒም ቲዩብ SUBSCRIBE በማድረግ አገልግሎቱን ይደግፉ ናታኒም ማለት የእግዚአብሔር ቤት ጠራጊ ታናሽ አገልጋይ ማለት ነውና።





2.9K viewsማኔ ቴቄል ፋሪስ, 06:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-22 06:12:12
✞ የማርያም ሞት ግን ሁሉን ያስደንቃል ✞


የእመቤታችን ትንሣኤ ብዙዎችን ማከራከሩ እንዴት ያሳዝናል? ክርስቶስ ‹ትንሣኤና ሕይወት እኔ ነኝ› ብሏል፡፡ እውነት ትንሣኤን ለወለደች እናት መነሣትዋ ትልቅ ነገር ነው? የሕይወት እናት ሕያው ሆነች ቢባል ያስቆጣልን? ሞትን የሞተው በልጅዋ አይደለምን? የሕይወትን እናት ሞት ይዞ አስቀራት ማለት ደስታ የሚሠጠው ለሞት አበጋዞች ነው፡፡ ‹‹አምላክ ያደረባት የምትናገር ታቦት ፈርሳ ቀርታለች ማለት ፣ ታቦተ ጽዮን ድንግል በሞት ፍልስጤም ተማርካ ቀርታለች›› ማለት የሚያስደስተው በማኅፀንዋ ፍሬ የተፈረካከሰው ዲያቢሎስ ነው፡፡ ለእኛ ለኦርቶዶክሳውያን የሚደንቀን መሞትዋ እንጂ መነሣትዋ አይደለም፡፡

ቅዱስ ያሬድ ‹‹የማርያም ሞት ግን ሁሉን ያስደንቃል›› እንዳለው ሕይወትን ያስገኘች ድንግል ፣ አምላክን የታቀፉ ክንዶች ፣ የእግዚአብሔር ዙፋን የሆኑ ጉልበቶች በሞት መሸነፋቸው ያስደንቀናል፡፡ መነሣትዋ ግን የምንጠብቀው ነው፡፡ አልዓዛርን ‹አልዓዛር አልዓዛር› ብሎ ያስነሣ ጌታ ፣ በዕለተ ዓርብ በሞቱ ብዙ ሙታንን ያስነሣ ጌታ እናቱን አስነሣ ሲባል የሚቆጡ እንዴት ያሉ ናቸው?
(ዲያቆን ሔኖክ ሐይሌ)


የቻናሌ ቤተሰቦች እንኳን አደረሳቹ ለእናታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ስጋዋ ላረገበት መታሰቢያ በዓል

ዘማሪ ዲያቆን ፍፁም ከበደ


https://t.me/zdfitsumkebe
https://t.me/zdfitsumkebe
https://t.me/zdfitsumkebe
3.0K views✞£iŧsûm✞, 03:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-20 17:27:27
"ካንቺስ ሌላ ድንግል ሆይ"


በዘማሪ ዲያቆን ፍፁም ከበደ

Vedio አውርደው ያድምጡ




ካንቺስ ሌላ ድንግል ሆይ ማላጂቱ
ካንቺስ ሌላ ድንግል ሆይ ወለላይቱ
ምን ዋጋ አለኝ ምንተስፍ
ምኑን ሰው ሆንኩ እኔ
አይኔ ነሽ ብርሃኔ (2-)


አዝ

አርፈ ተቀመጥ ዶኪማስ እመን
እናት አለችህ የምትታመን
ልጇ ወይን ነው እርሷም ወለላ
መጨነቅ የለም ካሁን በኋላ

አዝ

አይንሽ ልጅሽን ይመለከታል
እርሱም እናቴ እያለሽ ሞቷል
ወንድ ልጅ ወልደሽ አይኔ ባይበራ
የት ይሆን ነበር የኔስ መኖሪያ

አዝ

አፈገፈገ ሸሸጠላቴ
ፀሎትሽ ድሌ ፍቅርሽ ጉልበቴ
እማምላክ ልበል እሙ ነሽና
ካንድዬ ጋራ ነይ በደመና

አዝ
ፍሬሽ ቡርክ ነው አንቺም ቡርክት
አትጠገቢ ወለላይት
ፀጋን ተላብሰሽ ፀሀይ ለብሰሻል
ትውልዱ ሁሉ ተከትሎሻል




ዘማሪ ዲያቆን ፍፁም ከበደ


JOINE JOINE


https://t.me/zdfitsumkebe
https://t.me/zdfitsumkebe
https://t.me/zdfitsumkebe
12.9K views✞£iŧsûm✞, 14:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-20 02:46:00 + የሐዲስ ኪዳን ደብረ ሲና +

አይሁድ ‘እኛ የሙሴ ደቀ መዛሙርት ነን ፤ እግዚአብሔር ሙሴን እንደተናገረው እኛ እናውቃለን ይህ ሰው ግን ከወዴት እንደሆነ አናውቅም’ ብለው ክርስቶስን ሊያቃልሉ ሞክረው ነበር፡፡

ዛሬ በደብረ ታቦር የተከናወነውን ቢያውቁ ምን ይሉ ይሆን? እነርሱ ሕጉን እንጠብቃለን ብለው የሚመኩበትና የእርሱን ሕግ እየጠቀሱ ክርስቶስን ሊነቅፉ የሚሞክሩበት ሙሴ ዛሬ በታቦር ተራራ ከጌታ ፊት በፍርሃት ቆመ፡፡ አይሁድ ይህንን ቢያዩ ምን ይሉ ይሆን? ፈሪሳውያን ሆይ ወደ ደብረ ታቦር ብቅ ብትሉ የእርሱ ደቀ መዛሙርት ነን ብላችሁ የምትመኩበት ሙሴን የክርስቶስ ደቀ መዝሙር ሆኖ ታገኙታላችሁ፡፡ የሕግ ፍጻሜ ክርስቶስ የሕጉን ተቀባይ ሙሴን ጠርቶ እያነጋገረው ነው፡፡ ሙሴም በሲና ተራራ በዛፍ ላይ ሲነድ ካየው እሳት ጋር እየተነጋገረ ነው፡፡

አይሁድ ሆይ በጌታ ፊት በትሕትና ብትቀርቡ ኖሮ የት እንደተቀበረ እንኳን የማታውቁትን ሙሴ ለማየት በታደላችሁ ነበር፡፡ የሙሴን መጻሕፍት በቃላችሁ የምታውቁ ሕግ አዋቂዎች ሆይ እናንተ ቁጭ ብላችሁ ክርስቶስ ለሦስት ትሑታን ዓሣ አጥማጆች ሙሴን እያሳያቸው ነው፡፡ ‘ኤልያስ ይመጣል’ የምትሉ ጻፎች ሆይ የክርስቶስ ደቀ መዛሙርት ብትሆኑ ኖሮ ኤልያስን በታቦር ተራራ ባያችሁት ነበር፡፡ ደብረ ታቦር ብትገኙና ኤልያስን ብታዩት ኖሮ መስቀሉ ሥር ቆማችሁ ኤሎሔ ሲል ስትሰሙ ‘ኤልያስን ይጠራል ያድነው ከሆነ እናያለን’ ብላችሁ ባልሰማ ጆሮአችሁ ከፈጣሪ ጋር አትጣሉም ነበር፡፡

ደብረ ታቦር የሐዲስ ኪዳን ደብረ ሲና ሆነች፡፡ ሙሴ ሕዝቡን ከተራራ በታች ትቶ ከኢያሱና ከወንድማማቾቹ አብዩድና ናዳብ ጋር ወደ ሲና ተራራ ይወጣ እንደነበር ክርስቶስም ከጴጥሮስና ከወንድማማቾቹ ያዕቆብና ዮሐንስ ጋር ወደ ታቦር ተራራ ወጣ፡፡ ሙሴ በሲና በደመና መካከል የእግዚአብሔርን ድምፅ እንደሰማ በታቦርም የአብ ቃል ተሰማ፡፡ የታቦር ድምፅ ግን እንደ ሲና ‘ባሪያዬ ሙሴ’ የሚል ሳይሆን ‘የምወደው ልጄ’ የሚል ነበር፡፡ ሙሴ በሲና ተራራ ባየው የእግዚአብሔር ክብር ምክንያት ፊቱ እስራኤል ተሸፈንልን እስኪሉት ድረስ አበራ፡፡ የታቦር ተራራው ግን የተለየ ነበር ፤ ብርሃኑ ከውስጡ የፈለቀው ጌታ ፊቱ ከሙሴ ይልቅ አበራ በልብሱ እንዳይሸፍነው ልብሱም ብርሃን ነበረና ተማሪዎቹ ወደቁ፡፡

ታቦር እንዴት ያለች ‘እግዚአብሔር የወደዳት’ ተራራ ናት? [ደብር ዘሠምሮ እንዲል] ሐዋርያትና ነቢያት በአንድነት ቆመው የሚተያዩባት ፤ ብሉይና ሐዲስ የተዋወቁባት ፤ ጥላና አካል የተጋጠሙባት ይህች ተራራ እንዴት የተመረጠች ናት? ‘ታቦርና አርሞናዔም በስምህ ደስ ይላቸዋል’ እንደተባለ ነቢያትና ሐዋርያትን በግራ በቀኙ አድርጎ በሰማያዊ አባቱ ‘የምወደው ልጄ’ ተብሎ ሲጠራ ስሙን ሰምታ ታቦር ምንኛ ደስ ይላት ይሆን? የሰናፍጭ ቅንጣት ታህል እምነት አጣን እንጂ ነቅለን ወደ ሀገራችን ከምናስገባቸው ተራሮች አንዱ ታቦር በሆነ ነበር፡፡

በታቦር ተራራ ሐዋርያትና ነቢያት በአንድ ወንበር ከሊቀ ሊቃውንት ክርስቶስ ትምህርት ተምረው ተመለሱ፡፡ ሐዋርያቱ የነቢያት ጌታ መሆኑን ሲማሩ ነቢያቱ ደግሞ የሐዋርያት አምላክ መሆኑን አወቁ፡፡ ነቢያት ደክመው የዘሩትን ከሚያጭዱ አጫጆች ሐዋርያት ጋር ተዋወቁ፡፡
ነቢያት አምላክነቱን ያውቃሉ ፤ ሐዋርያት ደግሞ ሰውነቱን ያውቃሉ፡፡ በታቦር ተራራ ግን አዲስ ትምህርት ተማሩ፡፡ ቅዱስ ኤፍሬም እንዲህ ይላል ፦ ‘‘ነቢያቱ አይተውት የማያውቁትን ሰውነቱን አይተው ተደሰቱ ፤ ሐዋርያቱ አምላክነቱን አይተው ተደሰቱ’’

ሐዋርያት ደነገጡ ፤ እነርሱ ባልነበሩበት በዮርዳኖስ የተናገረውን የእግዚአብሔር አብን ድምፅ በታቦር ተራራ ሰሙ ፤ ጴጥሮስ ‘አንተ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ ነህ’ ያለው በሰማይ ያለው አብ ገልጦለት ነበረ ፤ አሁን በልቡ ያንን ቃል ያስቀመጠውን የአብን ድምፅ ሰምቶ ዓለቱ ስምዖን በፍርሃት ወደቀ፡፡ የጌታን ፊት አብርቶ ሲያይ ሳያይ ያመነውን አምላክነቱን አወቀ፡፡ ‘ሐዋርያት በአንድ ቀን ሁለት ፀሐይ ወጥቶ አዩ ፤ አንደኛው የተለመደችው ፀሐይ ስትሆን ሁለተኛው ደግሞ የሚያበራው የጌታ ፊት ነበር’ ይላል ቅዱስ ኤፍሬም፡፡ እውነትም ስሙን ለሚፈሩ ሐዋርያት የጽድቅ ፀሐይ ክርስቶስ በታቦር ተራራ ላይ ወጣላቸው፡፡

ቅዱስ ኤፍሬም በታቦር ተራራ ነቢያትና ሐዋርያት መገናኘታቸውን እንዲህ ሲል ያደንቃል ፦
‘የብሉይ ኪዳን ጸሐፊዎች የሐዲስ ኪዳን ጸሐፊዎችን አዩ ፤ ቅዱሱ ሙሴ ቅዱስ ጴጥሮስን አየው የአብ እንደራሴ የወልድን አገልጋይ ተመለከተው፡፡ የብሉይ ኪዳኑ ድንግል ኤልያስ የሐዲስ ኪዳኑን ድንግል ዮሐንስን አየው፡፡ በእሳት ሰረገላ ላይ የተሳፈረው ኤልያስ ወደ እሳታዊው ክርስቶስ ደረት የተጠጋውን ዮሐንስን አየው፡፡ የታቦር ተራራ የቤተ ክርስቲያን ምሳሌ ሆነ ፤ ክርስቶስም ሁለቱን ኪዳናት አዋሐዳቸው!’

ሐዋርያት ወድቀው ‘የምወደው ልጄ ይህ ነው እርሱን ስሙት’ የሚል ቃል ከሰሙ በኋላ ሲነሡ ከክርስቶስ ብቻ በቀር ማንንም አላዩም፡፡ በእርግጥም ‘የምወደው ልጄ ይህ ነው’ ተብለው ማሳሰቢያ ከተሠጣቸው በኋላ ቀና ሲሉ ማግኘት ያለባቸው ‘የሚወደው ልጁን’ ክርስቶስን ብቻ ካልሆነ አዋጁ ስለማን እንደሆነ ግራ ይገባቸው ነበር ይላል ማር ኤፍሬም፡፡

ሐዋርያት ቀና ሲሉ ሙሴ የለም ፤ ኤልያስም የለም፡፡ ለነገሩ ከሙሴም ከኤልያስም የሚልቀው ጌታ ከእነርሱ ጋር ካለ ምን ይፈልጋሉ? ባልወለደው ፈርኦን የልጅ ልጅ ተብሎ ከተጠራው ሙሴ ይልቅ ባልወለደው ዮሴፍ የዮሴፍ ልጅ ተብሎ የተጠራው ክርስቶስ ከእነርሱ ጋር ነው፡፡ ከፈርኦን ሰይፍ ተርፎ እስራኤልን ነጻ ካወጣው ሙሴ የሚበልጠው ከሔሮድስ ሰይፍ ተርፎ ዓለምን ነጻ ያወጣው ክርስቶስ ከእነርሱ ጋር አለ፡፡ እናቱ ሞግዚቱ ሆና ካሳደገችው ሙሴ በላይ ‘እናትና ገረድ ማርያም ደስ’ ብሏት ያሳደገችው ክርስቶስ አይሻላቸውም? ግብፃዊውን ገድሎ ለማንም አትናገሩ ከሚለው ሙሴ ይልቅ ዕውራንን አብርቶ ለምፃምን አንጽቶ ፊቱ እንደ ፀሐይ አብርቶ ለማንም አትናገሩብኝ የሚለው ክርስቶስ አብሮአቸው ካለ ምን ይፈልጋሉ፡፡ ‘የቆምህበት ሥፍራ የተቀደሰች ናትና ጫማህን ከእግርህ አውልቅ’ ተብሎ ከተነገረው ሙሴ ይልቅ ‘የጌታ እግር በሚቆምበት እንሰግዳለን’ ‘የጫማህን ጠፍር እንኳን ልፈታ አይገባኝም’ እየተባለ የተዘመረለት ክርስቶስ ከእነርሱ ጋር ነውና ለሦስቱ ደቀ መዛሙርት የሙሴ መሔድ አላስደነቃቸውም፡፡

ኤልያስንም ስላላዩ አላዘኑም ፤ በእሳት ሰረገላ ከሔደው ኤልያስ በላይ ልብሱ እሳት ቀሚሱ እሳት የሆነው አምላክ ከእነርሱ ጋር ነው፡፡ ኤልያስ ለደቀ መዝሙሩ ወደ ሰማይ ሲሔድ መጎናጸፊያውን ትቶለት ሔዶ ነበር፡፡ የሐዋርያት መምህር ክርስቶስ ግን ሲያርግ ልብሱን አልወረወረላቸውም፡፡ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እንዳለ እርሱ ሲያርግ ለደቀ መዛሙርቱ የተወላቸው ልብሱን ሳይሆን ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን ነው፡፡ ስለዚህ ኤልያስ ቢሔድ ሙሴም ቢሰወር ደቀ መዛሙርቱ ጌታችንን ከብበው ከታቦር ተራራ በደስታ ወረዱ፡፡

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ

https://t.me/akanim1wasen2
3.5K viewsወሰንየለው ባህሩ, 23:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-19 09:09:16
ቅዱስ ኤፍሬም በታቦር ተራራ ነቢያትና ሐዋርያት መገናኘታቸውን እንዲህ ሲል ያደንቃል ፦
‘የብሉይ ኪዳን ጸሐፊዎች የሐዲስ ኪዳን ጸሐፊዎችን አዩ ፤ ቅዱሱ ሙሴ ቅዱስ ጴጥሮስን አየው የአብ እንደራሴ የወልድን አገልጋይ ተመለከተው፡፡

የብሉይ ኪዳኑ ድንግል ዮሐንስ የሐዲስ ኪዳኑን ድንግል ዮሐንስን አየው፡፡ በእሳት ሰረገላ ላይ የተሳፈረው ኤልያስ ወደ እሳታዊው ክርስቶስ ደረት የተጠጋውን ዮሐንስን አየው፡፡ የታቦር ተራራ የቤተ ክርስቲያን ምሳሌ ሆነ ፤ ክርስቶስም ሁለቱን ኪዳናት አዋሐዳቸው!


በታቦር ተራራ ላይ የጌታችን ልብስ እንደ ፀሐይ አበራ ፣ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ "ከፀሐይም በላይ ነው ፣ ፀሐይ አይቶ የወደቀ የለም የጌታችንን ልብስ ሲያዩ ግን የወደቁት ያበራው ከዚያ በላይ ስለሆነ ነው" ይላል።



ዘማሪ ዲያቆን ፍፁም ከበደ



JOINE JOINE


https://t.me/zdfitsumkebe
https://t.me/zdfitsumkebe
https://t.me/zdfitsumkebe
3.8K views✞£iŧsûm✞, 06:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-15 11:48:39
የአለቃ ገ/ሐናን #ታሪካቸውን እና እማይጠገቡ #ቀልዶቻቸውን ማግኘት ማንበብ ለምትፈልጉ ከታች ባሉት ሊንኮች ይቀላቀሉን

https://t.me/joinchat/aLHyVIpQPIBhYzQ0
277 viewsማኔ ቴቄል ፋሪስ, 08:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ