Get Mystery Box with random crypto!

ዘማሪ ዲ/ን ፍፁም ከበደ

የቴሌግራም ቻናል አርማ zdfitsumkebe — ዘማሪ ዲ/ን ፍፁም ከበደ
የቴሌግራም ቻናል አርማ zdfitsumkebe — ዘማሪ ዲ/ን ፍፁም ከበደ
የሰርጥ አድራሻ: @zdfitsumkebe
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 22.71K
የሰርጥ መግለጫ

ዘማሪ ዲያቆን ፍፁም ከበደ

Ratings & Reviews

5.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

2

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 28

2022-09-02 13:12:37

219 viewsማኔ ቴቄል ፋሪስ, 10:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-02 09:00:29 ስለ ሚስጢረ ጥምቀት የቀረበ የጥያቄ መልስ




ጥያቄው

ጥምቀት ከእምነት በኋላ ነው የ40 80 ቀን ሕፃናት ደግሞ ለማመንና ምስጢራትን ለመመርመርና ያመኑትንም ለመመስከር አይችሉም ሳያምኑና ሳይመሰክሩ እንዴት ይጠመቃሉ የሚል ጥያቄ መናፍቃን ይጠይቃሉ ያነሳሉ ጥያቄ ይሄም ነው። በዚሕም ጥያቄ ከእኛ ከኦርቶዶክሳውያን  ዘንድ የሚጠይቁ አካላት አልጠፍም ጥያቄን ለማወቅ መጠየቅ ጥሩ ነው ላለማወቅ መጠየቅ አውቃለሁነት የታከለበት መጠየቅ የድንቁርና መጨረሻም መሆኑን ሳልጠቅስ ሳልናገር ማለፍ አልፈልግም ።


መልስ

በእርግጥ አንድ ሰው ለመጠመቅ እና በራሱ ፍቃደኛ መሆኑ ያስፈልጋል ። ሕፃናት ግን ይህን ለማወቅ ስለማይችሉ በወላጆቻቸው እምነት ይጠመቃሉ ። ይህም ቢሆን መጽሐፍ ቅዱሳዊ ነው ።

ለምሳሌ ፦ ቅዱስ ጴጥሮስን ከነ ቤተሰቡ ማጥመቁ ተጽፏል (የሐዋ 10፥24-48) ። እንዲሁም ቅዱስ ጳውሎስና ስላስ የታሰሩበት ወህኒ ቤት ጠባቂ ፣ ሊድያ እና ቅዱስ እስጢፍኖስም ከነ ቤተሰቦቻቸው መጠመቃቸው ተጽፏል( የሐዋ 16 ፥ 34  16፥15 1ኛ ቆሮ 1፥ 16። ከነ ቤተሰቦቻቸው ሲባል ደግሞ በቤተሰብ ውስጥ ልጆች ሊኖሩ እንደሚችሉ አያጠራጥርም። ይህም ልጆች በወላጆቻቸው እምነት እንደሚጠመቁ ያመለክታል።



ለሐዲስ ኪዳን  ጥላ /ምሳሌ/ በሆነችው  በብሉይ ኪዳን ዘመንም ለአብርሃም በተገባለት ቃል ኪዳን መሰረት ወንድ ልጅ በተወለደ በስምንተኛው ቀን ተገርዞ የእግዚአብሔር ወገን ይሆን እንደነበረ ተጽፏል (ዘፍ 7፥12። ቅዱስ ጳውሎስ ደግሞ ግርዛቱ የጥምቀት መሆኑን ተናግሯል (ቆላ 2፥11-14) ። እንግዲህ የስምንት ቀን ሕፃን ተገርዞ የእግዚአብሔር ወገን የሚሆን ከሆነ የ40 እና 80 ቀን ሕፃናት ተጠምቀው የእግዚአብሔር ልጆች የማይሆኑበት ምን ምክንያት ይኖራል? ቤተክርሰቲያን የህን ምሳሌ ሕፃናት በ40 እና በ80 ቀን ታጠምቃለች ።




ልጆች በወላጆቻቸው እምነት ሊድኑ እንደሚችሉ  ለማወቅ ደግሞ በወላጆቻቸው እምነት ከደዌ ስጋ የተፈወሱትን ማየት ይቻላል ።





ለምሳሌ ፦ የቅፍርናሆሞ መቶ አለቃ ልጁ የዳነው በአባቱ እምነት እንጂ በልጁ እምነት አልነበረም። (ማቴ 8፥5-13) አንዲሁም በማርቆስ ወንጌል ተራኳ የተፃፈላት ሴት ልጇ ከአጋንንት በሽታ ነፃ የወጣችው በእናቷ እምነት እንጂ በሕፃን ልጇ እምነት አልነበረም ። (ማር 7፥24-29)  ይህም የሚያመለክተን የወላጆች እምነት ለልጆችም ሊሆኖ እንደሚችል ነው። ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ደግሞ "ሕፃናትን ወደኔ ይመጡ ዘንድ ተው አትከልክሏቸው ፤ የእግዚአብሔር መንግሰት እንደዚህ ላሉት ናትና" ። አለ እንጂ ሕፃናት አያውቁምያና እሲኪያድጉ ዝም በሏቸዎ አላልም ። (ማር 10፥14) በሌላ ቦታ ደግሞ ሕፃን  አዋቂ ብሎ ሳይለይ " ሰው ከውኃና ከመንፈስ ካልተወለደ በቀር ወደ እግዚአብሔር  መንግስት ሊገባ አይችልም"  ብሏል (ዮሐ 3፥5)




እንግዲህ የእግዚአብሔር መንግስት ለሕፃን ለአዋቂም ከሆነ ያልተጠመቀም ወደ እግዚአብሔር መንግስት መግባት  የማይችል ከሆነ  ቤተ ክርስቲያን  ሕፃናትን ማጥመቋ ስህተቱ ምኑ ላይ ነው ? እግዚአብሔርን ማወቅና ማመንስ ቢሆን ሕፃንና አዋቂ በመሆን ብቻ ይሆናልን? ያማ ቢሆን እነ ኤርምያስ በሆድ ሳሉ ባልተመረጡ ፣ መጥምቀ መለኮት ቅዱስ የሆንስም በማኅፀን ሳለ ለክርስቶስና ለእናቱ ድንግል ማርያም ባልሰገደም ነበር። በተቃራኒው ደግሞ ተማሩ አወቁ የተባሉ ተመራማሪዎችና ፈላስፎች ግን ጣኦትን ባለመለኩና ሀልዎተ እግዚአብሔርን ባልካዱ ነበር ። ለዚህ ነው ጌታም "እኔ መረጥኋቹሁ እንጂ እናንተ አልመረጣችሁኝም" ያለው ዮሐ 15፥16 ስለሆነም ቤተክርስቲያን እግዚአብሔር የመረጠውን ለእግዚአብሔር ለመቀደስ ያሕል ሕፃናትን ታጠምቃለች ። ቤተ ሰቦቻቸውም ልጆቻቸውን ማስጠመቅ እና ሃይማኖታቸውን ማስተማር ብሎም ወደ ቤተክርስቲያን አምጥተው በአባቶች ማስባረክ እንደሚገባቸው ታስተምራለች ። ሕፃናቱ ካደጉና ሃይማኖታቸውን ተምረው ካወቁ በኋላ ግን  የወላጆቻቸውን እምነት ካልፈለጉ ወደፈለጉበት የመሄድ ፈቃድ አላቸው።


ዘማሪ ዲያቆን ፍፁም ከበደ


JOINE JOINE



https://t.me/zdfitsumkebe
https://t.me/zdfitsumkebe
https://t.me/zdfitsumkebe
686 views✞£iŧsûm✞, 06:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-01 23:45:39 በዚያን ጊዜ ተጠንቀቁ

ፍካሬ ኢየሱስ

ሰብል በደረሰ ግዜ አንበጣ፣ኩብኩባ የምድራቸውን ፍሬ የሚበላ መቅሰፍት ይልክባቸዋል

በየሀገሩ ፀብ፣ክርክር ይነሳል
እና የአባቶቻችን መልእክት........ ሙሉውን ለማንበብ
96 viewsማኔ ቴቄል ፋሪስ, 20:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-01 22:28:24
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስቅዱስ አሀዱ አምላክ
አሜን!!
# መፅሀፍ_ቅዱሳዊ_ጥያቄዎች
በዚህ ቻናል የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ አስተምህሮ የጠበቁ መፅሀፍ ቅዱሳዊ ጥያቄዎች ከነ መልሶቻቸው ይለቀቃሉ
እርሶም ለሌሎች እያጋሩ ቃለ እግዚአብሄርን አውቀው ያሳውቁ ።
405 viewsማኔ ቴቄል ፋሪስ, 19:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-01 16:28:29 ከአክራሪ እስልምና ወደ ክርስትና
#በእውነተኛ_ታሪክ_ላይ_የተመሰረተ
ክፍል 2
#ባለታሪክ_እና_ጸሀፊ
ናሕድ ማሕሙድ ሙቱዋሊ
#ተርጓሚ ዲ/ን ዳንኤል ክብረት

ናታኒም ቲዩብ SUBSCRIBE በማድረግ አገልግሎቱን ያበረታቱ ናታኒም ማለት የእግዚአብሔር ቤት ጠራጊ ታናሽ አገልጋይ ማለት ነውና።






1.1K viewsማኔ ቴቄል ፋሪስ, 13:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-01 14:06:55 + አባቶቻችን እንዲህ አሉ +

"በኃጢአት በወደቅህ ጊዜ ተስፋ ቆርጠህ ጸሎትህን እንዳታቆም። ንስሓ እስከምገባ ድረስ ብለህ ጸሎት ካቆምክ መቼም ንስሓ አትገባም። ምክንያቱም ጸሎት ራሱ የእውነተኛ ንስሓ መግቢያ በር ነው" ቅዱስ ቄርሎስ ሳድሳዊ

"ሰዎች አንድ ሰው ተነሥቶ ሌላውን ሲገድል ወንጀለኛ ነህ ይሉታል። አንድ ላይ ተሰባስበው ብዙ ሰዎችን ሲገድሉ ግን ውጊያ ይሉትና መግደላቸውን ጀግንነት ይሉታል" ቅዱስ ቆጵሮሳዊ

"ሰዎች የሚያብዱበትና እንደነሱ ያላበደ ሰው ሲያዩ "እንደኛ ስላልሆንክ አብደሃል" የሚሉበት ዘመን ይመጣል"
ቅዱስ እንጦንዮስ

"መካሪ አያስፈልገኝም የማለትን ያህል ታላቅ ትዕቢት የለም"
ቅዱስ ባስልዮስ

"ይህንን ካስታወስክ በሰው መፍረድ ታቆማለህ:: ይሁዳ ሐዋርያ ነበር:: ከጌታ ቀኝ የተሰቀለው ወንበዴ ነፍሰ ገዳይ ነበር" ቅዱስ ዮሐንስ ዘሰዋስው

"የክርስቲያኖች መሣሪያ በእጃቸው ሰይፍን መታጠቅ ሳይሆን እጃቸውን ወደላይ ለጸሎት መዘርጋት ነው"
ቅዱስ አትናቴዎስ ዘእስክንድርያ

"እግዚአብሔር ለአብርሃም "ከሀገርህ ውጣ ከወገኖችህ"ተለይ ብሎት ነበር። በዚህ ጥሪ እግዚአብሔር ሁላችንንም የተወለድንበት ዘር እንድንተው ይጠራናል። ሰማዕቱ ዮስጦስ (100 AD-165 AD)

"ክርስቶስ ጴጥሮስን "ሰይፍህን ወደ ሰገባው አስገባ" ሲለው ትጥቅ ያስፈታው ጴጥሮስን ብቻ ሳይሆን እንደ ጴጥሮስ በእርሱ የሚያምኑትን ሁሉ ነበር" ሊቁ ጠርጡለስ

‹‹ይጸልያል ነገር ግን የሌሎችን ጸሎትም ይሰማል፡፡ ያለቅሳል የሌሎችን ዕንባ ግን ያብሳል፡፡ ሰው ነውና አልዓዛር ወዴት እንደተቀበረ ጠየቀ፡፡ አምላክ ነውና አልዓዛርን ከሞት አስነሣ፡፡ እርሱ በርካሽ ዋጋ ያውም በሠላሳ ብር ብቻ ተሸጠ፡፡ ነገር ግን ዓለምን በውድ ዋጋ በከበረ ደሙ ገዛ፡፡ እንደ በግ ለመታረድ ተነዳ እርሱ ግን የእስራኤል እረኛ የዓለምም ሁሉ ጠባቂ ነበረ፡፡ እንደ በግ ዝም አለ ነገር ግን እርሱ በምድረ በዳ በሚጮኽ ሰው ድምፅ የተሰበከ ቃል ነበር፡፡ እርሱ የተሰቃየና የቆሰለ ነበር ፤ ሁሉንም በሽታና ቁስል ግን ይፈውስ ነበር›› ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘእንዚናዙ

"ለቤተ መቅደስህ ተክል ያደረግኸኝ፡፡ አቤቱ ሆይ የውጭ ተክል አታድርገኝ፡፡ የጽድቅ ተክል አድርገኝ፡፡ የኃጢአት አይደለም፡፡ የዕውነት ተክል አድርገኝ የሐሰት አይደለም የፍቅር ተክል አድርገኝ የጽል አይደለም፡፡

የመጻሕፍት መጀመሪያ የምትሆን ኦሪት ደመና የምትጋርደኝ፡፡ ከቅዱስ ወንጌል ፈሳሽ የምጠጣ ከጎንህ ከፈሰሰው ደም የምረካ ልሁን፡፡ በናትህ በድንግል ጸሎት የሃይማኖት አበባ ላብብ፡፡ የጽድቅ ፍሬን ላፍራ ከቅዱሳንህ ሐዋርያትም ከቃላቸው ፍሬ የተነሣ እስከ ዘለዓለሙ ድረስ የተባረከ የወይን ቦታ ልባል የጽድቅን ፍሬ የሚያስቀረውንም የኃጢአት እሾህ ጠምዝዘው ከደጁም አሜከላውን አረሙንም ሙጃውንም ንቀለው፡፡ አቤቱ ከኔም አርቀው ሥርዓትህን የሚሠሩትን ያበባቸውን ፍጻሜ እንዳፈራ አድርገኝ" ቅዱስ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
1.3K viewsወሰንየለው ባህሩ, 11:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-01 06:18:54
እንኳን ደስ አላችሁ በዩቲዩብ የምናውቀው ማኅቶት ቲዩብ አሁን ደግሞ በቴሌግራም መጥታል ለመቀላቀል ከስር ያለውን ሊንክ ንኩት።


@Mahtot_Tube
@Mahtot_Tube
4 views✞£iŧsûm✞, 03:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-01 06:17:09 ዘማሪ ዲያቆን ፍፁም ከበደ pinned «ተጀምሯል    ክፍል - 1 የወሊድ መቆጣጠሪያ የውርጃ አብዮት ክፍል - 1 ጋብቻ ምስጢር ነው ። ልጆች ደግሞ በረከት ናቸው። ትንሿ ቤተክርስቲያን ወይም ቤተ ሰብም የዋናዋ ቤተክርስቲያን ምእመናን መፍሪያ ናቸው። በቤተ ሰብ መንፈሳውያን ልጆች ተወልደው አድገው አባላት ወደ ዋናዋ ቤተክርስቲያን ይጨመራሉ ። የወደፈቱ ካህናት ፣ የወደፈቱ የመነኮሳት ፣ በአጠቃላይ…»
03:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 13:13:52 ከአክራሪ እስልምና ወደ ክርስትና
#በእውነተኛ_ታሪክ_ላይ_የተመሰረተ
ክፍል 1
#ባለታሪክ_እና_ጸሀፊ
ናሕድ ማሕሙድ ሙቱዋሊ
#ተርጓሚ ዲ/ን ዳንኤል ክብረት

ናታኒም ቲዩብ SUBSCRIBE በማድረግ አገልግሎቱን ያበረታቱ ናታኒም ማለት የእግዚአብሔር ቤት ጠራጊ ታናሽ አገልጋይ ማለት ነውና።






1.4K viewsማኔ ቴቄል ፋሪስ, 10:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 13:06:02
የክርስትና መሰረት  ዘውግ አይደለም *


በጎሳ (ዘውግ) አንድነት ላይ የተመሰረተ እና ይህን ተጠቅመው በሌሎች ላይ የበላይ ለመሆን የሚሰሩ ሰዎች የሚመሩት ሃይማኖትም ብዙ ተከታይ ሊኖሩት ይችላል ። ክርስትና በምድር ሁሉ የተበተኑ ፣ ከሁሉም ዘውጎች የተሰበሰቡ ፣ ምድራዊ ክብርን እና የበላይነትን የማይፈልጉ ፣ ለመግደል ሳይሆን የክርስቶስ ምስክሮች ሆነው ለመሞት እንደ በግ በተኩላዎች መካከል የተላኩ ሰዎች የሰበኩት ሃይማኖት በመሆኑ የዘውግ አንድነት እና የኃይል የበላይነት ከክርስትና አመሰራረት እና እሳቤ ጋር አይሄድም ። ክርስትና በምድራዊ ኃይል እና ስልጣን በሌሎች ላይ የበላይ መሆን መፈለግን ስለሚከለክል የዘውግ እና የኃይል አንድነት የክርስትና  ማኅበር ለመቀላቀል ጥሩ ምክንያት አይደለም ።

(የልቦና ችሎት በረከት አዝመራው )


ዘማሪ ዲያቆን ፍፁም ከበደ

JOINE JOINE


https://t.me/natanimtube
https://t.me/natanimtube
https://t.me/natanimtube
2.8K views✞£iŧsûm✞, 10:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ