Get Mystery Box with random crypto!

ዘማሪ ዲ/ን ፍፁም ከበደ

የቴሌግራም ቻናል አርማ zdfitsumkebe — ዘማሪ ዲ/ን ፍፁም ከበደ
የቴሌግራም ቻናል አርማ zdfitsumkebe — ዘማሪ ዲ/ን ፍፁም ከበደ
የሰርጥ አድራሻ: @zdfitsumkebe
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 22.71K
የሰርጥ መግለጫ

ዘማሪ ዲያቆን ፍፁም ከበደ

Ratings & Reviews

5.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

2

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 31

2022-07-14 14:09:00
ክርስቶስ ድንቅ ነው

አንዱ ካየው የሰው እንዲህ ማነስ ትዝብት የተነሳ ለወዳጁ የልቡን እንዲህ ይለዋል አንድ ሰው ይገርመኛል እህ ከማለቱ ሊሰማው እንደቃጣ ገብቶታል ደገመው አንድ ሰው ይገርመኛል። የእርሱ ሞልቶለት ባልመጉደሉ አምላኩን ከማመስገን ይልቅ በኔ ከሙላት አንሶ መታየቱ ያስፈነጥዘዋል የኔ ማነስ እንጂ የእርሱ ሞልቶ መፍሰስ ደስታውን አለማምጣቱ አንድ ሰው ይገርመኛል። እርሀቤ ጥጋቡ የሆነለት በሽታዬ ጤንነቱ የሆነለት አንድ ሰው ይገርመኛል ። እንባዬ መታበሱ አልዋጥ ያለው የኔን እንባ ዘወትር ቀድቶ ሚጠጣው ያ ሰው ይገርመኛል ። ሳስበው ለራሱ አለመኖሩ የእኔን ውጣ ሳይሆን ውረድ መመልከቱ መዝጎቦ ጠባሳዬን ቆጥሮ መቅለሙ አንድ ሰው ይገርመኛል ።
ግን ሰው የሆነው ክርስቶስ ያስደንቀኛል ዶሮ ጫጩቶቿን በክንፏ እንደምሰበስብ አንተንም ከጠላት ቀስት እሰበስብሀለው እያለ ዘወትር እንደ ልቤ ካለው በዳዊት ቃል በኩል ሹክ ሲለኝ ። እየተራበ ለአንድ ጊዜ አይደለም ዘላለማዊ ምግብ እንደ ሰጠኝ ሚያሳውቀኝ ክርስቶስ ይደንቀኛል ። በእሱ መከራ ድካም የኔን ጥንካሬን መመለሱ ። በእርሱ ጥማት የኔን የዘላለም ጥምን ማርካት መቻሉ በእውነት ሰው የሆነ እውነት ክርስቶስ ይደንቀኛል። በእርሱ ቁስል ቁስሌ መዳኑ ምሰጠው እንዳች ሳይኖረኝ ሁሉን የሰጠኝ ሰው የሆነ ክርስቶስ እውነት ያሰደንቀኛል ።
ከአምላኬ ቸርነት አንፃር የጠላቴ ክፍት ሚዛን የማይደፍ ሆኖ መታየቱ በእውነት እኔ ይደንቀኛል በእውነት ክርስቶስ ሰው የሆነ ያስደንቀኛል ። ብሎ ዝም ከማለቱ ወዳጁ የደነቀህ ሰው የሆነ እውነት ክርሰቶስ ድንቅ ነው ብሎ ጨረሰው እርእሱን ።


ዘማሪ ዲያቆን ፍፁም ከበደ
ሐምሌ 7 /2014
1.8K views✞£iŧsûm✞, 11:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-12 10:59:46

3.0K viewsማኔ ቴቄል ፋሪስ, 07:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-12 07:34:11
እንኳን ፤ለብርሃናተ ዓለም ቅዱስ ጴጥሮስ ወጳውሎስ በዓለ ዕረፍት እንዲሁም ለሐዋርያት (የሰኔ) ጾም ፍቺ አደረሳችሁ፡፡

ዲያቆን ፍፁም ከበደ
3.0K views✞£iŧsûm✞, 04:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-12 06:16:54 ቅዱስ ጳውሎስ

ጳውሎስ ማለት ንዋይ ህሩይ ማለት ነው። ሐዋ. ፱፡ ፲፭ (9፡15) አንድም ብርሃን ማለት ነው። ዘዳ.፲፬፡፪ አንድም መድቅዕ ማለት ነው። ቀዳሚ ስሙ ሳዖል ነው። ሳዖል ማለት ጸጋ እግዚአብሔር የበዛለት ማለት ነው።8 ትውልዱ ከነገደ ቢኒያም ነው። ፊሊ. ፫፡፭ አባቱ ዮስአስ ይባላል።

የተወለደው ጌታ በተወለደ በ፭ (5) ዓመት በጠርሴስ ነው። ከ፲፭ ዓመቱ ጀምሮ ኢየሩሳሌም በታላቅ እህቱ ቤት ተቀምጦ ከመምህር ገማልያል ሕገ ኦሪትን ተምሯል። በወንጌል ያመነው ጌታ ባረገ በ፰ኛው ዓመት ነበር። ጌታም በደማቆ መብረቅ ጥሎበት ሳኦል ሳኦል ስለምን ታሳደኛለህ ብሎ ታርቆታል። ከ፸፪ (72) አርድእት አንዱ የሆነው ሐናንያ ጌታ በራዕይ ታይቶት ጳውሎን አስተምረህ አሳምነህ አጥምቀው አለው። እርሱም በእጁ ገና አይኑ በዳሰሰው ጊዜ አይኑን አሳውሮት የነበረው እንደ ቅርፊት ወድቆለታል። ሐዋ.፱፡፩-፲፱ (9፡1¬-19)

ከዚያ በኋላ በክርስቶስ እመኑ እያለ አስተምሯል። ብዙዎችንም አስተምዎ አጥምቋል። ሐዋ. ፲፬፡፰-፲፰ ብዙውንም አሳምኗል። በወይኒም ታስሮ በነበረበት ወቅት ብዙ ሰዎችን አሳምኗል። ጳውሎስ ግን ተቸገረና ዘወር ብሎ መንፈሱ፤ ከእርስዋ እንድትወጣ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም አዝሃለሁ አለው፤ በዚያም ሰዓት ወጣ።

ጌቶችዋም የትርፋቸው ተስፋ እንደ ወጣ ባዩ ጊዜ ጳውሎስንና ሲላስን ይዘው ወደ ገበያ በሹማምት ፊት ጐተቱአቸው፤ ወደ ገዢዎችም አቅርበው። እነዚህ ሰዎች አይሁድ ሆነው ከተማችንን እጅግ ያናውጣሉ። እኛም የሮሜ ሰዎች ሆነን እንቀበላቸውና እናደርጋቸው ዘንድ ያልተፈቀደልንን ልማዶች ይናገራሉ አሉ።

ሕዝቡም አብረው ተነሡባቸው፥ ገዢዎቹም ልብሳቸውን ገፈው በበትር ይመቱአቸው ዘንድ አዘዙ፤ በብዙም ከደበደቡአቸው በኋላ ወደ ወኅኒ ጣሉአቸው፥ የወኅኒውንም ጠባቂ ተጠንቅቆ እንዲጠብቃቸው አዘዙት። እርሱም የዚህን ዓይነት ትእዛዝ ተቀብሎ ወደ ውስጠኛው ወኅኒ ጣላቸው፥ እግራቸውንም በግንድ አጣብቆ ጠረቃቸው። በመንፈቀ ሌሊት ግን ጳውሎስና ሲላስ እየጸለዩ እግዚአብሔርን በዜማ ያመሰግኑ ነበር፥ እስረኞቹም ያደምጡአቸው ነበር ድንገትም የወኅኒው መሠረት እስኪናወጥ ድረስ ታላቅ የምድር መንቀጥቀጥ ሆነ፤ በዚያን ጊዜም ደጆቹ ሁሉ ተከፈቱ የሁሉም እስራት ተፈታ።

የወኅኒውም ጠባቂ ከእንቅልፉ ነቅቶ የወኅኒው ደጆች ተከፍተው ባየ ጊዜ፥ እስረኞቹ ያመለጡ መስሎት ራሱን ይገድል ዘንድ አስቦ ሰይፉን መዘዘ። ጳውሎስ ግን በታላቅ ድምፅ ሁላችን ከዚህ አለንና በራስህ ክፉ ነገር አታድርግ ብሎ ጮኸ። መብራትም ለምኖ ወደ ውስጥ ሮጠ፥ እየተንቀጠቀጠም ከጳውሎስና ከሲላስ ፊት ተደፋ፤ ወደ ውጭም አውጥቶ። ጌቶች ሆይ፥ እድን ዘንድ ምን ማድረግ ይገባኛል? ኣላቸው።
እነርሱም በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ እመን አንተና ቤተ ሰዎችህ ትድናላችሁ አሉት።

ለእርሱና በቤቱም ላሉት ሁሉ የእግዚአብሔርን ቃል ተናገሩአቸው። በሌሊትም በዚያች ሰዓት ወስዶ ቍስላቸውን አጠበላቸው፥ ያን ጊዜውንም እርሱ ከቤተ ሰዎቹ ሁሉ ጋር ተጠመቀ፤ ወደ ቤቱም አውጥቶ ማዕድ አቀረበላቸው ፥ በእግዚአብሔርም ስላመነ ከቤተ ሰዎቹ ሁሉ ጋር ሐሤት አደረገ። ሐዋ. ፲፮፡፲፰-፴፬ (16፡18-34) ሕሙማንንም ሕሙም መስሎ አስተምሯል። ፩ቆሮ.፱፡፳፪ (1ቆሮ.9፡22) ፲፬ መልዕክታትንም ጽፏል።

ከዚህ በኋላ በ69 ዓ.ም ሮም ሲያስተምር ኔሮን ቄሣር አስጠሩት ሲል በንጉሱ ፊት ሲቀርብ መስቀሉን ይዞ ቀረበ። ንጉሱ ተቆጥቶ በሰይፍ ቅጡ አለ። በመጎናጸፊያም ሸፍኖ ሰይፎታል። ደሙም ሰማየ ሰማይ ወጥቶ ቀተሉኒ በዓመጻ እያለ ተካሷቸዋል። ሲያልፍም የ72 ዓመት አረጋዊ ነበር። ከቅዱስ ጴጥሮስ ጋር የሞቱት በአንድ ቀን ነበር ።ይህም ሐምሌ 5 ነው።ብረክታቸው ይደርብን

ዲያቆን ፍፁም ከበደ

Share share share
3.0K views✞£iŧsûm✞, 03:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-11 18:32:19

2.6K viewsማኔ ቴቄል ፋሪስ, 15:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-11 18:19:59

3.0K viewsማኔ ቴቄል ፋሪስ, 15:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-10 09:24:23
" በሁለት ወገን ድንግል "


እመቤታችን ከተወደደ ልጇ ጋር የተሳለውን ሥዕል አድኅኖን እና በተለምዶ የሉሲፈር ሥዕልን የማመሳሰል ነገር አለ። የእመቤታችን ሥዕል ተበርዟል የሉሲፈርን የጣት አቀማመጥ ለእመቤታችን እና ለጌታችን ተመሳሳይ የጣት አቀማመጥ ተሥለዋል በማለት ብዙዎች ዘንድ ግርታን ፈጥሯል። እውነታው ግን ሁለቱም ፈጽመው የማይገናኙ ሆነው እናገኛቸዋለን።

በሥዕሉ ላይ ጌታችን እና እመቤታችን የጣታቸው አቀማመጥ ይሄን ይመስላል።

✞ ጌታ ጣት ወደ ላይ መሆን ትርጉም ✞

የጌታችን ሁለት ጣቱን ወደላይ አድርጎ ዓለምን ሲባርክ እንመለከታለን። በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን መሠረት ትርጓሜው እንዲህ ነው። ጣቱን ወደላይ ማድረጉ ልዕልናውን ወይም ልዑል አምላክ፥ ሰማያዊ አምላክ መሆኑን ያስረዳል። ሁለቱ ጣቶቹ ሁለት ልደት መሆኑን ያስረዳሉ።

✞ የእመቤታችን ጣት ወደታች መሆን ትርጉም ✞

የእመቤታችን ጣት ደግሞ ወደታች መሆኑ ምንም እንኳን ሰማይና ምድርን የፈጠረ አምላክን የወለደች ብትሆንም ከምድር የተገኘች ምድራዊት መሆኖን ያስረዳል።
የጣቶቿ ሁለት መሆን በሕሊናም በሥጋም ድንግል መሆኗን ወይም በአባቶቻችን አነጋገር በሁለት ወገን ድንግል መሆኗን ያስረዳል።

እንዲህ አይነት የአሣሣል ጥበቦች በጥንታውያን የቤተክርስቲያን ሥዕላት ላይ የተለመዱ ናቸው እንጂ አሁን የመጡ ዘመን አመጣሽ አይደሉም። ለማሳየት ከላይ ያለውን ስዕል ጥንታዊውን ሥዕል መመልከት ይቻላል።
ስለዚህ የሉሲፈር ሥዕል ተብሎ ከሚታወቀው የጣዖት ሥዕል ጋር የሚገናኝ አይደለም።


ዲያቆን ወሰን የለው በሐሩ


Share share

https://t.me/ZDfitsumkebede
4.9K views✞£iŧsûm✞, 06:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-08 06:56:39
ምልዕተ ፀጋ
ክብረ ቅዱሳን ንፅሕት ነሽ 2
የአምላክ እናት ኪዳነ ምሕረት ደስ ይበልሽ

አዝ

አባሕርያቆስ በመንፊስ ቅዱስ እየተቃኘ
ጎሳ ልብየ ቃለ ሰናየ አፈለቀ አለ
ያንቺን ምስጋና በማብዛት ሳይሆን እያሳጠረ (2)
ስለዚህ ድንግል ከፋ ከፋ አርገን እንወድሻለን
ስለ ወለድሽው ያለሙን ንጉስ መዳሐኒአለምን
አስገኝተሻል የሚበላውን የሚጠጣውን2

አዝ
ሰማይ ብርሀና ወንዞች ቀለማት ሆነው፡ቢሰሩ
ፀጋ ክብርሽን እንፃፈው ቢሉ መች ይበቃሉ
እንደሐዋርያት ዕፁብ ድንቅነሽ ብለው ያርፋሉ 2
እንቺ ሙሽራ እመ ክርስቶስ ምስራቀ ፀሐይ
ፀጋሽ ይድረሰኝ መሻቴን ሙይው ፅድቁንም እንዳይ
ነይ ከልጅሽ ጋር ኪዳነ ምሕረት የነብሴ ሲሳይ 2

አዝ
ስምሽ ስንቅ ነው ለተሰደዱት ለባዘኑት
ግርማ ሞገስነሽ በባዕድ ሀገር ለባዘኑት
ከአይን ጥቅሻ ስለ ፈጠነ የምልጃሽ ሙላት 2
ማርያም ውድስት በአፈ መላእክት ወአፈ ሰብ
እንደ ማር ወለላ የምስጋናሽ ጣም ጣፋጭ ሚበላ
ኪዳነ ምሕረት ሆንሻት ለነብሴ ጥላ ከለላ 2

ዘማሪ ዲያቆን ፋፁም ከበደ
የተዋህዶ ልጆች ሼር ሰብስክራብ እናድርግ !









4.8K viewsማኔ ቴቄል ፋሪስ, 03:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-07 08:22:24 ዘማሪ ዲያቆን ፍፁም ከበደ pinned a photo
05:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-06 16:40:29
ተጠንቀቁ ውሸት ነው

ተመልከቱ ፎቶውን

<<ከቤት እንዳታወጡ ቤት አስቀምጡ !!>>

ውድ የቻናሌ ቤተሰቦች ሰው የtube እና የtik tok ተከታይ ለማፍራት ከቤተክርስቲያን አስተምሕሮ ውጪ እንዲ አድርጉ እያለን ነው ።

<<ከቤት እንዳታወጡ ቤት አስቀምጡ !!>>

የእመቤታችን ሥዕል ተበርዟል የሉሲፈርን የጣት አቀማመጥ ለእመቤታችን እና ለጌታችን ተመሳሳይ የጣት አቀማመጥ ተሥለዋል በማለት ብዙዎች ዘንድ ግርታን ፈጥሯል


መልስ አላት ቤተክርስቲያናችን
ሙሉውን መልስ ይጠብቁኝ በኔ ቻናል

መልስ ሚመልስልን

ዲያቆን ወሰን የለው በሐሩ

Share share share

joine joine joine

https://t.me/ZDfitsumkebede
https://t.me/ZDfitsumkebede
https://t.me/ZDfitsumkebede
6.4K views✞£iŧsûm✞, 13:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ