Get Mystery Box with random crypto!

ክርስቶስ ድንቅ ነው አንዱ ካየው የሰው እንዲህ ማነስ ትዝብት የተነሳ ለወዳጁ የልቡን እንዲህ | ዘማሪ ዲ/ን ፍፁም ከበደ

ክርስቶስ ድንቅ ነው

አንዱ ካየው የሰው እንዲህ ማነስ ትዝብት የተነሳ ለወዳጁ የልቡን እንዲህ ይለዋል አንድ ሰው ይገርመኛል እህ ከማለቱ ሊሰማው እንደቃጣ ገብቶታል ደገመው አንድ ሰው ይገርመኛል። የእርሱ ሞልቶለት ባልመጉደሉ አምላኩን ከማመስገን ይልቅ በኔ ከሙላት አንሶ መታየቱ ያስፈነጥዘዋል የኔ ማነስ እንጂ የእርሱ ሞልቶ መፍሰስ ደስታውን አለማምጣቱ አንድ ሰው ይገርመኛል። እርሀቤ ጥጋቡ የሆነለት በሽታዬ ጤንነቱ የሆነለት አንድ ሰው ይገርመኛል ። እንባዬ መታበሱ አልዋጥ ያለው የኔን እንባ ዘወትር ቀድቶ ሚጠጣው ያ ሰው ይገርመኛል ። ሳስበው ለራሱ አለመኖሩ የእኔን ውጣ ሳይሆን ውረድ መመልከቱ መዝጎቦ ጠባሳዬን ቆጥሮ መቅለሙ አንድ ሰው ይገርመኛል ።
ግን ሰው የሆነው ክርስቶስ ያስደንቀኛል ዶሮ ጫጩቶቿን በክንፏ እንደምሰበስብ አንተንም ከጠላት ቀስት እሰበስብሀለው እያለ ዘወትር እንደ ልቤ ካለው በዳዊት ቃል በኩል ሹክ ሲለኝ ። እየተራበ ለአንድ ጊዜ አይደለም ዘላለማዊ ምግብ እንደ ሰጠኝ ሚያሳውቀኝ ክርስቶስ ይደንቀኛል ። በእሱ መከራ ድካም የኔን ጥንካሬን መመለሱ ። በእርሱ ጥማት የኔን የዘላለም ጥምን ማርካት መቻሉ በእውነት ሰው የሆነ እውነት ክርስቶስ ይደንቀኛል። በእርሱ ቁስል ቁስሌ መዳኑ ምሰጠው እንዳች ሳይኖረኝ ሁሉን የሰጠኝ ሰው የሆነ ክርስቶስ እውነት ያሰደንቀኛል ።
ከአምላኬ ቸርነት አንፃር የጠላቴ ክፍት ሚዛን የማይደፍ ሆኖ መታየቱ በእውነት እኔ ይደንቀኛል በእውነት ክርስቶስ ሰው የሆነ ያስደንቀኛል ። ብሎ ዝም ከማለቱ ወዳጁ የደነቀህ ሰው የሆነ እውነት ክርሰቶስ ድንቅ ነው ብሎ ጨረሰው እርእሱን ።


ዘማሪ ዲያቆን ፍፁም ከበደ
ሐምሌ 7 /2014