Get Mystery Box with random crypto!

' በሁለት ወገን ድንግል ' እመቤታችን ከተወደደ ልጇ ጋር የተሳለውን ሥዕል አድኅ | ዘማሪ ዲ/ን ፍፁም ከበደ

" በሁለት ወገን ድንግል "


እመቤታችን ከተወደደ ልጇ ጋር የተሳለውን ሥዕል አድኅኖን እና በተለምዶ የሉሲፈር ሥዕልን የማመሳሰል ነገር አለ። የእመቤታችን ሥዕል ተበርዟል የሉሲፈርን የጣት አቀማመጥ ለእመቤታችን እና ለጌታችን ተመሳሳይ የጣት አቀማመጥ ተሥለዋል በማለት ብዙዎች ዘንድ ግርታን ፈጥሯል። እውነታው ግን ሁለቱም ፈጽመው የማይገናኙ ሆነው እናገኛቸዋለን።

በሥዕሉ ላይ ጌታችን እና እመቤታችን የጣታቸው አቀማመጥ ይሄን ይመስላል።

✞ ጌታ ጣት ወደ ላይ መሆን ትርጉም ✞

የጌታችን ሁለት ጣቱን ወደላይ አድርጎ ዓለምን ሲባርክ እንመለከታለን። በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን መሠረት ትርጓሜው እንዲህ ነው። ጣቱን ወደላይ ማድረጉ ልዕልናውን ወይም ልዑል አምላክ፥ ሰማያዊ አምላክ መሆኑን ያስረዳል። ሁለቱ ጣቶቹ ሁለት ልደት መሆኑን ያስረዳሉ።

✞ የእመቤታችን ጣት ወደታች መሆን ትርጉም ✞

የእመቤታችን ጣት ደግሞ ወደታች መሆኑ ምንም እንኳን ሰማይና ምድርን የፈጠረ አምላክን የወለደች ብትሆንም ከምድር የተገኘች ምድራዊት መሆኖን ያስረዳል።
የጣቶቿ ሁለት መሆን በሕሊናም በሥጋም ድንግል መሆኗን ወይም በአባቶቻችን አነጋገር በሁለት ወገን ድንግል መሆኗን ያስረዳል።

እንዲህ አይነት የአሣሣል ጥበቦች በጥንታውያን የቤተክርስቲያን ሥዕላት ላይ የተለመዱ ናቸው እንጂ አሁን የመጡ ዘመን አመጣሽ አይደሉም። ለማሳየት ከላይ ያለውን ስዕል ጥንታዊውን ሥዕል መመልከት ይቻላል።
ስለዚህ የሉሲፈር ሥዕል ተብሎ ከሚታወቀው የጣዖት ሥዕል ጋር የሚገናኝ አይደለም።


ዲያቆን ወሰን የለው በሐሩ


Share share

https://t.me/ZDfitsumkebede