Get Mystery Box with random crypto!

ዘማሪ ዲ/ን ፍፁም ከበደ

የቴሌግራም ቻናል አርማ zdfitsumkebe — ዘማሪ ዲ/ን ፍፁም ከበደ
የቴሌግራም ቻናል አርማ zdfitsumkebe — ዘማሪ ዲ/ን ፍፁም ከበደ
የሰርጥ አድራሻ: @zdfitsumkebe
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 22.71K
የሰርጥ መግለጫ

ዘማሪ ዲያቆን ፍፁም ከበደ

Ratings & Reviews

5.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

2

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 29

2022-08-30 07:51:23 + ድንገት የተበጠሰ ገመድ +

የደብረ ዳሞ ገዳም በገመድ ብቻ የሚወጣ እጅግ ጥንታዊ ገዳም ነው:: ይህንን አቡነ አረጋዊ በዘንዶ የወጡትን ታላቅ ገዳም ለመውጣት በግንባታው ወቅት በአፄ ገብረ መስቀል የተሠራ ደረጃ ነበረው:: ሆኖም አቡነ አረጋዊ ደረጃውን ዳህምሞ (አፍርሰው) ብለው በማዘዛቸው እስከ አሁን ድረስ በገመድ የሚወጣበት ገዳም ሆኖአል::

የደብረ ዳሞ መውጫ ገመድ እጅግ ወፍራም ሲሆን እስከ አሁን ድረስ በብዙ ሺህዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ተንጠላጥለው ወጥተው ወርደውበታል:: ይህ እጅግ ወፍራም ገመድ ለዘመናት ሲያገለግል ተበጥሶ ሰው ጥሎ አያውቅም:: በታሪክ የማይዘነጋና መሃል ላይ የተበጠሰበትና ሰው የጣለበት ቀን አለ:: (የዲያቢሎስ መተናኮል ነው የሚል አለ)

በዚያ ቀን በተበጠሰው ገመድ ላይ የወረደው መንገደኛ ጻድቁ አባ ተክለ ሃይማኖት ነበሩ:: መነኮሳቱን ተሰናብተው በዚያ ገመድ ሲወርዱ ተበጥሶ የማያውቀው ገመድ ድንገት ተበጠሰ:: ከላይ የሚያዩት አባቶች ቁልቁል እያዩ በድንጋጤ ጮኹ:: ሆኖም እግዚአብሔር ለጻድቁ የብርሃን ክንፍ ሠጥቶአቸው ከተበጠሰው ገመድ ተለይተው እንደ መልአክ በርረው ሁለት ሺህ ክንድ ያህል ወርደው መሬት ላይ አረፉ:: ባረፉባት ሥፍራም ቤተ ክርስቲያን ተሠራባት::

ወዳጄ በሕይወትህ ድንገት የተበጠሰ ገመድ የለም? ሳትጠብቀው የተበጠሰ ገመድ ማንም ላይ ሳይበጠስ አንተ ላይ የጨከነ ገመድ የለም? ምን ዓይነት ገመድ አትበለኝ:: የእንጀራ ገመድ የኑሮ ገመድ የትምህርት ገመድ የፈለግኸው ገመድ በለው:: እሱን ተጠምጥመህ ይዘህ ወደ አንዳች ቦታ ለመድረስ የተማመንክበት ተስፋህን ሙሉ በሙሉ የጣልክበት ገመድ የለም? ድንገት ተበጥሶ ዙሪያው ገደል አልሆነብህም? ሰዎች ማንም ላይ ያልተበጠሰ ገመድ አንተ ላይ ሲበጠስ አይተው "ምኑ ዕድለ ቢስ ነው?" ብለው የተደነቁብህ እንደ ቅዱስ ጳውሎስ "ከባሕር አደጋ ተርፎ ዕባብ የነደፈው እንዴት ኃጢአተኛ ቢሆን ነው?" ብለው በትዝብት ዓይን እንዲያዩህ ያደረገ በሕይወትህ ሳታስበው ተበጥሶ ዙሪያው ገደል የሆነ ሥፍራ ላይ የጣለህ የሕይወት ገመድ ይኖር ይሆናል::

በዕድልህ አትማረር በሕይወትህ ድንገት የሚበጠስብህ ገመድ የምትወድቅበት ሳይሆን ክንፍ አውጥተህ የምትበርበት ነው:: ፈጣሪ የተማመንክበትን የምታየውን ገመድ እንዲበጠስብህ ከፈቀደ ያላየኸውን ክንፍ ሊሠጥህ እንጂ ሊጥልህ አይደለም:: የሕይወትህን ገመድ የተበጠሰበትን ቀን "እግዚአብሔር ለመልካም አሰበው" ብለህ እንደ ዮሴፍ ታመሰግንበታለህ::
ገመድህን የሚበጥሰው ከገደል ሊጥልህ ሳይሆን በክንፍ አብቅሎ ሊተክልህ ነው:: የሚተክልህ በበረሃ ሳይሆን በእግዚአብሔር ቤት ውስጥ ነው:: ተራ ተክል የምትሆን እንዳይመስልህ:: የሃይማኖት ተክል (ተክለ ሃይማኖት) ትሆናለህ:: ተክለ መንፈስ ቅዱስ ተክለ ወልድ ተክለ አብ ትሆናለህ:: አብ የተከለው ደግሞ አይነቀልም!

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
ታኅሣሥ 24 2013 ዓ ም


JOINE JOINE


https://t.me/zdfitsumkebe
https://t.me/zdfitsumkebe
https://t.me/zdfitsumkebe
1.4K views✞£iŧsûm✞, 04:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 07:51:11 ዘማሪ ዲያቆን ፍፁም ከበደ pinned «ተጀምሯል    ክፍል - 1 የወሊድ መቆጣጠሪያ የውርጃ አብዮት ክፍል - 1 ጋብቻ ምስጢር ነው ። ልጆች ደግሞ በረከት ናቸው። ትንሿ ቤተክርስቲያን ወይም ቤተ ሰብም የዋናዋ ቤተክርስቲያን ምእመናን መፍሪያ ናቸው። በቤተ ሰብ መንፈሳውያን ልጆች ተወልደው አድገው አባላት ወደ ዋናዋ ቤተክርስቲያን ይጨመራሉ ። የወደፈቱ ካህናት ፣ የወደፈቱ የመነኮሳት ፣ በአጠቃላይ…»
04:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 08:03:35 ተጀምሯል    ክፍል - 1

የወሊድ መቆጣጠሪያ የውርጃ አብዮት

ክፍል - 1

ጋብቻ ምስጢር ነው ። ልጆች ደግሞ በረከት ናቸው። ትንሿ ቤተክርስቲያን ወይም ቤተ ሰብም የዋናዋ ቤተክርስቲያን ምእመናን መፍሪያ ናቸው። በቤተ ሰብ መንፈሳውያን ልጆች ተወልደው አድገው አባላት ወደ ዋናዋ ቤተክርስቲያን ይጨመራሉ ። የወደፈቱ ካህናት ፣ የወደፈቱ የመነኮሳት ፣ በአጠቃላይ የመንግስተ ሰማያት ልጆች ይጨምራሉ።




መጽሐፍ ቅዱስ ባልንና ሚስትን አንድ ከሚያደርጋቸው ምክንያት አንዱ ፦ "ዘር አይደለምን ?" ይላል (ሚል.2፥15)። ይህን በብሉይ ኪዳን ምድርን ለመሙላት እንደ ነበረ ፥ በሐዲስ ኪዳን ግን የእግዚአብሔርን ቤተክርስቲያን ፣ መንግስተ ሰማያትን በኦርቶዶክሳዊ ዘር መሙላት ነው ። ይኸው የኖኀ ልጆች ከመርከብ ወጥተው በዝተው ተባዝተው ምድርን ሞላት የቅድስት ቤተ ክርስቲያን ልጆች ደግሞ በዝተው ተባዝተው ገነትን እንደሚሞሏት ማለት ነው ።



አቡ ቀለምሲስ ዮሐንስ በራዕዮ ቤተ ክርስቲያንን፣ መንግስተ ሰማያትን " ሐዲስ ምድር " ብሎ የሚጠራትም ለዚህ ነው (ራዕ . 21፥1)። ሐዲስ ምድርን ለምን ተባለች ለሚለው ሊቃውንት ፦ " ምድር አልፍ እርሷ የምትተካ ስለ ኾነ ፣ በምድር በሰሩት ስራ የምትወረስ ስለ ኾነ ፣ ምድራውያን ጻድቃን የሚወርሷት ስለ ኾነ " ይላሉ ።



ስለዚህ ሰይጣን መንፈሳውያን ልጆች እንደማይወለዱ ክቡር ጋብቻን አጥብቆ ይጠላል ። በውርጇ ፣ በወሊድ መቆጣጠሪያና በመሳሰሉት አማካኝነት የመንግስተ ሰማይ ልጆች እንዳይበዙ የሚገኙበትን ክቡር ጋብቻ ያቀልላል ፤ እንዲፈረስ ብሎም የማይፈነቅለው ድንጋይ የለም። የቤተ ክርስቲያን አባቾች አንደ አንድ ልብ መካሪ እንደ አንድ ቃል ተናጋሪ ኾነው የወሊድ መቆጣሪያን የተቃወሙት ለዚህ ነው።


በወሊድ መቆጣጠሪ ዙሪያ ላይ ጥያቄ ማንሳት የተጀመረው እጅግ በቅርብ ጊዜ ነው።
ውርጇን እየተቃወሙ ስለ ወሊድ መቆጣጠሪያ ጥርጣሬ የሚገባቸው ሰዎች የመጡት በቅርቡ ነው ። ከሕክምናው እድገት ጋር በማያያዝም "ውርጃ እስካልተፈጸመ ድረስ ምን ችግር አለው ? የጀመሩት ከጥቂት ዓመታት በፈት ነው ። ኃምሳ ዓመት ቢኾነው ነው። አሳባቸውንም እንዲህ ልናጠቃልለው እንችላለን ፦




" እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ የሕክምና ሳይንስ ብዙ የወሊድ መቆጣጠሪያ አማራጮች አልበሩባትም። የነበሩትም ቢኾኑ ውርጃን የሚያስከትሉ ነበሩ ። ቀደምት ቅዱሳን አበው የወሊድ መቆጣጠሪያንም ጨምረው የተቃወሙትና ያወገዙት ውርጇ እንዳይኖር በማሰብ ነው። አሁን ሳይንሱ እንደ ደረሰበት የወሊድ መቆጣጠሪያ ውርጇን እንደማያስከትል ቢያውቁ ኖሮ ምን አልባት ባላ ወገዙት ነበር" የሚል ነው።

ይህ ግን ብዙ ስሕተት ያለበት አስተያየት ነው ። ይህንን በሚከተሉት ነጥቦች በዝርዝር ማየት እንችላለን ። .......

( "ትንሿ ቤተከርስቲያን ኦርቶዶክሳዊ ጋብቻ ፣ ቤተሰብና የሕፃናት አስተዳደግ " ገብረ እግዚአብሔር ኪደ )



ቀጣይ ክፍል - 2 ይቀጥላል

በኔ Telegrame ቻናል

ዘማሪ ዲያቆን ፍፁም ከበደ



JOINE JOINE


https://t.me/zdfitsumkebe
https://t.me/zdfitsumkebe
https://t.me/zdfitsumkebe
4.7K views✞£iŧsûm✞, 05:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-27 20:21:31  የእመቤታችን ሕይወት ከጌታ ሞት በኋላ

እመቤታችን በቤተ ዮሐንስ ከቤተሰቦቹ ጋር አሥራ አምስት ዓመት  ኖረች።   ቤታቸው በደብረ ዘይት ተራራ አቅራቢያ ነበር። እርሱም ከሔደበት አገልግሎት ሲመለስ ይጎበኛት ነበር። በወቅቱ ለአማንያኑና ለሐዋያት አማካሪም አጽናኝም ነበረች።  ለሐዋርያት ተአምራታዊ  ስለ ነበሩት የመልአኩ ብስራት፣ ያለ ወንድ ዘር ስለ መጽነስዋ፣ የእርሷን የልጅነት ታሪክ ትነግራቸው ነበር ይላል።

በተጨማሪም ልክ እንደ ሐዋርያቱ እርስዋም ቤተ ክርስቲያንን (ማኅበረ መእመናንን) በማቋቋም ረድታቸዋለች፤ በምልጃዋ ይታገዙ ነበር። ሐዋርያት ከበዓለ ሃምሳ በኋላ ሐዋርያት ለአሥር አመታት ያኽል ኢየሩሳሌም ነበሩ። ለአይሁድ ድኅነትን ሲሰብኩ። 

ሐዋርያት ብዙውን ጊዜ ከእመቤታችን ጋር ያሳልፉ ነበር። ቅዱስ ዮሐንስ ወደ ኤፌሶን ሲሔድ ከእርሱ ጋር ወስዷታል። ብዙዎ እርሷን ለማየት ከሩቅ ይመጡ ነበር። ይኽንን አስመልክቶ ቅዱስ አግናጥዮስም የቅዱስ ዮሐንስ ደቀ መዝሙር ለቅዱስ ዮሐንስ ሲጽፍለት ሲጽፍ እንዲኽ ነበር ያለው፡- 

“ከተቻለ በኢየሩሳሌም የሚኖረውን የአማኞች ጉባኤ ለማየት ለመካፈል እመጣለሁ፡፡ በተለይም የኢየሱስን እናት ለማየት፡ እርሷ የተከበረች ፣ትሁት፤ በሁሉም አስደናቂ፣ ሁሉም እርሷን ለማየት ይሻል፡፡ እርሷ የእግዚአብሔር እናት ሁላችንን ትባርካለች፤ ምልዕተ ጸጋ ወክብር፣ እርሷ በስደትና በመከራ ውስጥ ሁሉ ደስተኛ ናት፣ ደኃ በመሆን አታዝንም፣ በሚያበሳጩአትም ሁሉ አትበሳጭም፣ እንደውም አብልጣ ታደርግላቸዋለች፡፡ ያያት ሁሉ ይደነቃል፣ ይደሰታል” በማለት ጽፎለታል።

በመጀመሪያው የክርስቲያኖች ስደት ከዮሐንስ ጋር ሆና ወደ ኤፊሶን ተሰዳ ነበር በ43 ዓ.ም። “በዚያም ዘመን ንጉሡ ሄሮድስ መከራ ያጸናባቸው ዘንድ ከቤተ ክርስቲያኑ በአንዳንዶቹ ላይ እጁን ጫነባቸው። የዮሐንስንም ወንድም ያዕቆብን በሰይፍ ገደለው” ሐዋ.12.1

በቆጵሮስም(ሳይፕረስ) ከሞት ከተነሳው ከአልአዛር ጋር  ነበረች ሊቀ ጳጳስ ሆኖ ሳለ።

ዲዮናስዮስ፤ አግናጥዮስ፤ አምብሮስ ስለ እመቤታችን መንፈሳዊ ሕይወት ትንታኔ ሲሰጡ፦ 

"ድንግልናዋ በሥጋ ብቻ አይደለም በነፍስዋ፣ በሕሊናዋ፣ በልብዋ። በልብዋ ትኁት፣ አእምሮዋ ጠቢብ ነበር። ሥራና ንባብ ወዳጅ ነበረች። ጥንቁቅ ተናጋሪ ናት፣ የኑሮዋ መመሪያ ማንንም አያስቀይምም ነበር። ታላላቆችን ታከብራለች፣ አትታበይም። አትቀናም፣ ጤናማ አእምሮ አላት፤ ምግባር ትወዳለች፣ ሁሌም ትጾማላች፣ ሲያስፈልጋት ብቻ ትተኛለች፡ ሰውነቷ እንኳ ዐረፍ ብሎ መንፈሷ ንቁ ነው። ቀን ያነበበችውን በሕልምዋ ትደግመዋለች፡ ከቤት የምትወጣው ለቤተ ክርስቲያን ሥራ ብቻ ነው፡፣ አልያም ዘመዶቿን ለማየት" በማለት ገልጦታል።

ቅዱስ አትናቴዎስም ሲቀጥል፡-

በጣም መልካም ያማረ አቋም የነበራትና መልካም ሥራዎችን የምትወድድ ነበረች። በወንዶች መታየትን ፈጽማ አትፈልግም ነበር፣ ግን እግዚአብሔርን እንዲመረምራት ትጠይቃዋለች፤  ከጨዋታ የራቀ (የመናኝ) ሰውን ኑሮ ትኖር የነበረ ሲኾን ማር ከምትሰጥ ንብ ጋር ትመሳሰላለች። በእጆቿ ከሠራቻቸው ሥራዎች የምታገኘውን ገንዘብ ለድኾች ታከፋፍላለች። በብቸኝነት ኹለት ነገራትን እንዲያደርግላት ወደ እግዚአብሔር ትጸልያለች፤ ይኸውም መጥፎ ሐሳብ በልቧ ውስጥ እንዳይሠርጽና ልቧ በጭራሽ ከፍቅር አምላካዊ እየቀዘቀዘ እንዳይኼድ ነበረ። ንግግሯ የተረጋጋ እና ድምፆቿም ዝግ ያሉ ናቸው፤ በየቀኑም መንፈሳዊ ርምጃ (ብቃታዊ መሻሻል ዕድገት) ማድረግ ትፈልጋለች፤ በየቀኑም ያነን ታደርጋለች፤ በጠዋት ስትነሣም ከዚኽ በፊት አስቀድማ ከሠራቻቸው አስበልጣ ሥራዎቿን ለመሥራት ትፈልጋለች፤ ሞትን ፈጽማ አትፈራም ነበር። ይልቁኑ በሐዘን ኹና የመንግሥተ ሰማያት መዠመሪያ (መግቢያ) እንዳላቋረጠች በየቀኑ እያየች በጸሎቷ ታነሣለች) በማለት የደናግል መመኪያነቷን በስፋት ገልጾታል፡፡ (ዶ/ር ሮዳስ)

ኒሲፎረስ (ታሪክ ጸሐፊው) ስለ መልኳ ሲጽፍልን፦

"መካከለኛ ቁመት፣ ጸጉሯ ወረቃማ፣ ዓይኗ እንደ ወይራ ዘይት ብርሃን ያበራል፣ የዓይን ቅንድቧ ጠንካራና ጥቁር ነው፣ አንደበቷ የሚጣፍጥ ንግግር አለው፣ ጣቶችዋና መዳፍዋ ረጃጅም ናቸው"። በተአምረ ማርያም ላይ የእመቤታችን መልክ የአምላክን መልክ ይመስላል የሚል ንባብ አለ። ይኽም በአካል ልጇን ትመስላለች ማለት ሲሆን፤ ሌላውና ትልቁ ግን  መልክ የውጭ ውበትን ሳይሆን የመንፈሳዊ ሕይወትን ውበትን ማለት ነው። ቅዱስ ጳውሎስም የልጁን መልክ እንድንመስል ነግሮናል። 

ኒሲፎረስ ይቀጥላል እንዲኽ በማለት፦ "ስትናጋገር ተራ ንግግር አትናገርም፤ አትበሳጭም በፍጹምም አትናደድም፣ በፍጹም ስለራስዋ አትናገርም፣ የምታስበው ለሌላው ነበር። የልብሶችዋ ቀለም ተፈጥሮአዊ ቀለም ነበር።

ዲዮናስየስም ሲጽፍ ስለ እመቤታችን እረፍት  “አንቀላፋች ” ብሏታል። የሥጋዋን ወደ ሰማይ ማረግ የተናገረውና ጽፎ የተገኘው ለመጀመሪያ ጊዜ የሰርዴሱ ሊቀ ጳጳስ ሜሊተን ነው ብሎ አስፍሮላታል።

በአጠቃላይ ስለ እመቤታችን የማረፍ ታሪክ በትክክል መረጃን ሰብስቦ ያሰፈረው የአራተኛው መቶ ክፍለ ዘመን ጸሐፊው ኒሲፎረስ ነው። በተመሳሳይም የሐገራችን ሊቅ ቅዱስ ያሬድ ስለ እመቤታችን እረፍት ሲናገር ፦“ሞትኪሰ ማርያም ይመስል ከብካበ”  ማርያም ሆይ አሟሟትሽ ሰርግን ይመስላል ይላል። 

የእመቤታችን አማላጅነት አይለየን

መ/ር ንዋይ ካሳሁን

https://t.me/akanim1wasen2
2.7K viewsወሰንየለው ባህሩ, 17:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-27 15:08:31
✞ የታተመች ዓለት ✞

ከታተመው ዓለት ላይ ውኃን አፍልቆ እስራኤልን ስለ ውኃ ጥማት የተጮኽ ጩኅት ያስወገደ ጌታ በሲኦል በርሐ ጽምዓ ነብስ ደርሶባቸው ይጯጯሁ ለነበሩ ነብሳት ጩኽታቸውን ሰምቶ የሕይወትን ውኃ ያፈለቀው ከታተመችው ዓለት ከእመቤታችን ነው ።

እነሱ የሚያውቁት ያንኑ ነበርና << ብፁዕ ዘይሰቲ እማይ እይትግሃ ለግብፅ ፤ ከግብፅ ምንጮች ውኃን የሚጠጣ ብፁዕ ነው >> እያሉ በምድረበዳ ኑሮአቸውን ያማርሩ በነበሩበት በዚያ ሰዓት ከግብፅ ምንጮች የተሻለ ጥሩ ምንጭ ያለው መሆኑን ለሕዝቡ እግዚአብሔር ያስታወቀባት እስከ ዛሬም ድረስ "ዘአንቅዐ ማየ እምኮኩህ እስመ ለዓለም ምሕረቱ" ከዓለት ውኃን ያፈለቀው እርሱ ምሕረቱ ለዘለዓለም ነውና ። መዝ 35... ተብሎ የተመሰገነባት ያች ዓለት ከዓለቶች ሁሉ ተለይታ የታተመች ዓለት ናት።


እስኪ አስቡት ! በዚያ ዘመን በሲኦል የነበሩ ነብሳት ከመዳን ቀን በፈት ከመከራው ብዛት የተነሳ " አብርሃም አባት ሆይ ማረኝ በዚህ ነበልባል አሰቃያለሁና የጣቱን ጫፍ በውኃ ነክሮ ጉሮሮዬን የርስልኝ ዘንድ ዓልዓዛርን እንድትሰድልኝ እለምንሃለው ሉቃ 16-24 እያሉ ይጮሁበት የነበረበት ዘመን ነበር እኮ ፤ ለተጠማው ዓለም ዘላለማዊት ጽምዓ ነብስን ያስወገደለት የሕይወት ውኃችን ክርስቶስ ያፈለቀው ከመንፈሳዊቷ አለት ከእመቤታችን ነው " መጠማታችንን ዓይቶ ነው "የተጠማ ሁሉ ወደኔ ይምጣ ይጠጣም " ዮሐ 6፥ .... ላይ በመካከላችን የሰበከው

ስድስት መቶ ሺህ ሕዝብን ከታተመው ዓለት ውኃን አፍልቆ መመገብ የቻለ ጌታ በድንግልና ከታተመ ማሕፀን የሕይወትን ውኃ አፍልቆ እስራኤል ዘነብስ እኛን ከዘላለማዊ ጥማት ቢታደገን ምን ይሳነዋል።

( ሊቀ ሊቃውንት ስምዓ ኮነ ከ"ሕይወተ ማርያም መጽሐፍ) የተወሰደ ።



ዘማሪ ዲያቆን ፍፁም ከበደ
2.6K views✞£iŧsûm✞, 12:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-26 12:40:25 + ለምን ትቀናለህ? + 

በዜና አበው ላይ አጋንንት አንድን መነኩሴ ለማሰናከል ሲማከሩ የሚያሳይ ታሪክ ተጽፎአል፡፡ መነኩሴው ለብዙ ዘመናት በተጋድሎ አሳልፎ ከብቃት የደረሰ መናኝ ነበር፡፡ የአጋንንቱ ጭፍራ በአለቃቸው ተመርተው ይህንን መነኩሴ ለማሳት ዘመቱ፡፡ ተራ በተራ ወደ እርሱ እየሔዱ የፈተና ወጥመዳቸውን ዘረጉበት፡፡ በዝሙት ሊፈትኑት ሞከሩ፡፡ አልተሳካም፡፡ በምግብም ሞከሩ ድል ነሣቸው፡፡ የሚያውቁትን የፈተና ስልት በተለያየ መንገድ እየተገለጹ አንዴ ሰው አንዴ መልአክ እየመሰሉ ሊጥሉት ቢሞክሩም አልቻሉም፡፡

አለቃቸው ይኼን ጊዜ በሉ እኔ የማደርገውን ተመልከቱ አላቸውና መንገደኛ መስሎ ወደ መነኩሴው ቀረበ፡፡ በጆሮው የሆነ ነግሮት ወዲያው ተሰናብቶት ወጣ፡፡ ይህንን ጊዜ አጋንንቱ እያዩት መነኩሴው መንፈሳዊ ገጽታው ተገፍፎ ፊቱ በቁጣና በንዴት ሲለዋወጥ ተመለከቱት፡፡ በዚህም ተደንቀው ምን ብለህ ነው ያሸነፍከው? ብለው አለቃቸውን ጠየቁት፡፡ እርሱም እንዲህ አላቸው፦ ‘ከአንተ ጋር ያደገውና ከአንተ ጋር የተማረው ጓደኛህ እኮ የእስክንድርያ ፓትርያርክ ሆኖ ተሾመ’ ብዬ ነገርኩትና ወጣሁ፡፡ አሁን ልቡ በቅናት እየነደደ ነው አላቸው፡፡ አጋንንቱ በደስታ ጨፈሩ፡፡

ሰይጣን የቅናትን ኃይል ጠንቅቆ ያውቃል፡፡ መጽሐፈ ቅዳሴ ሞትን ሲገልጸው ‘በሰይጣን ቅናት ወደ ዓለም የገባ’ ይለዋል፡፡ ሰይጣን በሰው ልጅ ጸጋ ቀንቶ አዳምና ሔዋንን በፈጣሪያቸው እንዲቀኑና አምላክ መሆን እንዲመኙ አድርጎ ዓለምን ያመሰቃቀለ ነውና ይህንን መነኩሴ ለመጣል ለሺህ ዓመታት ብዙዎችን ወግቶ የጣለባትን ሰይፉን መዘዘበት፡፡ መነኩሴው የእኩያውን መሾም ሲሰማ ቅናቱን መቋቋም አቃተው::

ቅናት እጅግ ክፉ ኃጢአት ነው፡፡ ሰው ቢዘሙት ቢሰክር በሥጋው ነው:: ቅናት ግን በምታስተውል ነፍሱ ውስጥ የሚበቅል መርዝ ነው፡፡   ቃየልን በየዋህ ወንድሙ ላይ ያስጨከነው ቅናት ነበር፡፡ የአቤል ስኬት ለቃየል ውድቀት መስሎ ስለተሰማው በግፍ ሊገድለው በቃ፡፡

ዮሴፍ የለበሳት ቀለምዋ ብዙ የሆነ ጌጠኛ ቀሚስ በወንድሞቹ ዘንድ የመረረ ጥላቻን አትርፋለት ነበር፡፡ አንዱ አጊጦ አምሮ ሲታይ ቢሞትና ቢገላገሉት ደስ የሚላቸው የዮሴፍ ወንድሞች በየዘመኑ አሉ፡፡  

ዮሴፍም አርፎ አልተቀመጠም፡፡ እየሔደ ሕልሙን ይነግራቸው ነበር፡፡ ስለ ሕልሙም የበለጠ ጠሉት ይላል፡፡ ወዳጄ ሕልምህን ዝም ብለህ ለሰዎች አትዝራ፡፡ ሕልም ስልህ ተኝተህ የምታየውን ብቻ ማለቴ አይደለም፡፡ ራእይህን ፣ ተስፋህን ዕቅድህን ሲያውቁ የሚንገበገቡ የዮሴፍ ወንድሞች በየዘመኑ  አሉ፡፡ ፍቺው ባይገባቸውም ባልተፈታ ሕልም ይጠሉሃል፡፡ ምንም ነገር ሳታደርግ እንኳን "ለምን አለምከው?" ብለው ጥርስ ይነክሱብሃል፡፡ ዮሴፍ ግን ይኼ ስላልገባው ነገራቸው፡፡ ወዳጄ አንተም ሕልምህን እንደ ዮሴፍ በየዋህነት የምትዘራ ከሆንህ እንግዲህ የዮሴፍ አምላክ ይጠብቅህ፡፡

ቅናት እጅግ ከባድ ነው፡፡ እረኛው ዳዊት ጎልያድን የገደለ ዕለት የተዘፈነለት መዘዘኛ ዘፈንም ነበረ፡፡ ‘ሳኦል ሺህ ገደለ ዳዊት እልፍ ገደለ’ ብለው ዘፈኑለት፡፡ ይህች ዘፈን በሳኦል ጆሮ ስትደርስ ዳዊት ላይ ብዙ ጦር አስወረወረች፡፡ ሳኦሎች ሌላ ሰው ከእነርሱ በላይ ሲመሰገን የሰሙ ዕለት በቅናት ታውረው ገበታ ላይ ሳይቀር ሰይፍ ይመዛሉ፡፡

የጠፋው ልጅ ወንድምን አስበው፡፡ (ሉቃ 15:20) ወንድሙ ከጠፋበት ተመልሶ ደስታ ሲደረግ እርሱ ግን ከፍቶት ውጪ ቁጭ አለ፡፡ ወዳጄ ቅናት ከቤተ ክርስቲያንና ከእግዚአብሔር መንግሥት ያስወጣል፡፡ የሌላው ስኬት ካበሳጨህ እንደጠፋው ልጅ ወንድም ውጪ ቁጭ ብለህ አፈር እየጫርክ ‘እምቢየው አልገባም’ እያልክ እያልጎመጎምክ ትቀራለህ፡፡

ክርስቶስ ላይ አይሁድ ያቀረቡት ትችት ሁሉ ለሕግ ከመቆርቆር ሳይሆን ከቅናት ነበር፡፡ ጲላጦስ እንኳን ‘በቅናት አሳልፈው እንደሠጡት ያውቅ ነበር’ ይላል፡፡ አንዳንዴ ሰዎች ቅናታቸውን በሌላ ነገር እንደ አይሁድ ሸፍነው ትችት ያቀርባሉ፡፡ ለእግዚአብሔር ሕግ እንደተቆረቆሩ ፣ ለሥርዓቱ እንዳዘኑ መስለው ውስጣቸው ያለውን ቅናትና ጥላቻ ያንጸባርቃሉ፡፡

የሰንበት መሻር ፣ ለቄሣር ግብር መከፈል ፣ የመቅደሱ በሦስት ቀን ፈርሶ መሠራት እንዳንገበገባቸው እርር እያሉ ቢናገሩም እውነታው ግን ቅናት ነው፡፡ ‘የቤትህ ቅናት በላኝ’ እንዳለው ጌታ በየዘመኑ የሰዎች ቅናት ብዙ ንጹሐንን ትበላለች፡፡

ወዳጄ በሌላው ትቀና እንደሆን አሁኑኑ ከዚህ ውስጥን በልቶ ከሚጨርስ ካንሰር ራስህን አድን፡፡

ራስህን ከሌሎች ጋር አታወዳድር፡፡ በምድር ላይ እግዚአብሔር የፈጠረው አንተን የሚመስል ሌላ ሰው የለም፡፡ ካንተ ቀድሞም በትክክል አንተን የሆነ ሰው አልተፈጠረም ለወደፊትም አይፈጠርም፡፡ እግዚአብሔር ቀድሞ ያልሠራው ደግሞም የማይሠራው ምርጥ ዕቃው ነህና ራስህን ከሌላ ጋር አታወዳድር፡፡

ለአንተ ብቻ የሠጠው ጸጋ አለና ሌሎችን መመልከት ትተህ ውስጥህ ያለውን ውድ ማንነት ቆፍረህ አውጣ፡፡ ያንተ ሕይወት ቁልፍ የተቀበረው አንተው ውስጥ ነው፡፡ ሌሎችን ረስተህ ወደ ራስህ ጠልቀህ ግባ፡፡ መብለጥ ከፈለግህም አሁን ያለውን ራስህን ብለጠውና ሌላ ትልቅ አንተን ሁን፡፡ 

በቅናት እንዳትቃጠል ሌሎችን ሰዎችንም ውደዳቸው፡፡ ከወደድሃቸው ‘ፍቅር አይቀናም’ና የእነርሱ ስኬት የደስታህ ምንጭ ይሆናል፡፡ የቅናት ስሜት ሲሰማህም ‘ቀናተኛ ልቤን ፈውስልኝ’ ብለህ ለምነው፡፡

‘በአገባብ እንመላለስ፤ በዘፈንና በስካር አይሁን፥ በዝሙትና በመዳራት አይሁን፥ በክርክርና በቅናት አይሁን’ ሮሜ 13፡13

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ

https://t.me/akanim1wasen2
3.0K viewsወሰንየለው ባህሩ, 09:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-26 09:31:07 ✞ ክፍትን እፈጥራለሁ ኢሳ 45፡7 ✞


የክፍ ምንጭ እግዚአብሔር ካልሆነ ክፍትን እፈጥራለሁ ለምን አለ በመጅመሪያ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ እንዲህ የሚሉትን ቃሎች እንመልከት ፦


" ብርሃንን ሰራሁ ፣ ጨለማንም ፈጠርሁ ፤ ደኅንነትን እሰራለሁ ፣ ክፍትንም እፈጥራለሁ እንዚህን ሁሉ ያደረግሁ እግዚአብሔር እኔ ነኝ ።" (ኢሳ 45፡7)

" ወይስ ክፍ ነገር በከተማ የመጣ እንደሆነ ያደረገው እግዚአብሔር አይደለምን ? አሞ 3:6

በመጽሐፍ ቅዱስ ትምሕርት ፣ "ክፍት" ወይም " ክፍ ነገር የሚለው ሁለት ነገርችን የሚያመለክት ቃል ነው ።

አንደኛው

፦ ክፍ የሚባለው ነገር ፣ በባሕርያቸው (በራሳቸው) ክፍ የሆኑ ነገሮችን የሚወክል ቃል ነው ። ለምሳሌ ጣዖትን ማምለክ፣ ሟርት፣ማመንዘር፣መዳራት፣መናፍቅነት፣ከሃዲነት፣ስካር፣ሰውን መጥላት፣ምቀኝነት፣ርኩሰት፣ዝሙት፣እና ይህን የመሳሰሉ ነገሮችን ምን ጊዜም በራሳቸው ክፍዎች ናቸው። እንደዚህ ያሉትን ማድረግ በእግዚአብሔር ዘንድ የተጠላ ነው። ቅዱስ ጳውሎስ " እንደዚህ ያሉትን የሚያደርጉ የእግዚአብሔር መንግስት አይወርሱም " እንዳለ ። (ገላ 5፡21)


ሁለተኛው ደግሞ

በራሳቸው ክፍ ያልሆኑ ፣ ሆኖም ግን እኛ ለጊዜው ስለማያስደስቱን ክፍ የምንላቸውን ነገሮች የሚገልጽ ቃል ነው ። ለምሳሌ አባት ልጁን ቢቀጣው ያ ቅጣት ልጁ ለግዜው ያበሳጨዋል እንጂ አያስደስተውም ፣ ስለዚህ ቅጣቱ ለልጁ "ክፍ" ነው ። አባትዮው ግን ያን የሚያደርገው ለልጁ ከማሰቡ ለልጁ ካለው ፍቅር የተነሳ እንጂ ልጁን ለመጉዳት ብሎ ስላልሆነ ከአባትዮ አንጻር ያቅጣት "መልካም" እንጂ ክፍ አይደለም ። እግዚአብሔርም እንደ አባትነቱ እያንዳንዱን ተበናጠልም ሆነ በጋራ የሚገስፅባቸው መንገዶች አሉ ።

አባቱ የሚቀጣው ልጅ የሚያየው የጊዜው መቀጣቱን እንጂ ከዚያ ባሻገር ያለውን ጠቀሜታውን ባለመሆኑ እንደሚያዝንና ቅጣቱን "ክፍ" እንደሚለው ፤ እኛም እግዚአብሔር እንደዚያ የሚያደርግበትን ምክንያት ካለማወቃችን የተነሳ እነዚህ ተግሳፆች "ክፍ" ልንላቸው እንችላለን ። ስለዚህ ከላይ ባየናቸው
በሁለቱ ጥቅሶች ላይ "ክፍትን እፈጥራለሁ" የሚለው "ክፍ " የሚገልጸው በራሱ የሆነውን የመጀመሪያውን አይነት ክፍ (ኃጥያትን) ሳይሆን ሁለተኛውን እኛ በተለምዶ "ክፍ" ብለን የምንጠራውን ተግሳጹን ቅጣቱን ነው ። ይህን ቅዱስ ጳውሎስ እንዲህ ሲል አብራርቶ ጽፎልናል ።

ከዚህ በላይ የቀጡት የስጋችን አባቶች ነበሩን ፣ እንፈራቸውም ነበር ፤ እንዴትስ ይልቅ ለመናፍስት አባት አብልጠን ልንገዛና በሕይወት ልንኖር በተገባን ? መልካም ሆኖ እንደታያቸው ለጥቂት ቀን ይቀጡን ነበርና፣ እርሱ ግን ከቅድስናው እንድንካፈል ለጥቅማችን ይቀጣናል። ቅጣት ሁሉ ለጊዜው የሚያዘን እንጂ ደስ የሚያሰኝ አይመስልም ፣ ዳሩ ግን በኋላ ለለመዱት የሰላምን ፍሬ እርሱም ፅድቅን ያፈራላቸዋል ። ዕብ . 12-9-11


እግዚአብሔር ክፍትን (ተግሳፅን ) የሚያመጣብን ወደ አርሱ አንድን መለስ ነው።


እግዚአብሔር በባሕርዩ ከክፍት የራቀና ክፍትን የሚጸየፍ ንጹሕ ባሕርይ አምላክ ነው ። " በእውነት እግዚአብሔር ክፍትን አይሰራም (ኢዮ 42-10-12)


(መድሎተ ጽድቅ ቅጽ ፪ ዲያቆን ያረጋል አበጋዝ)
የቻናሌ ቤተሰቦች ይህን የእውነት ሚዛን መጽሐፍ ታነቡት ትማሩበት በመንፈሳዊ እውቀት ትጎለምሱበት መልእክቴ ነው )


ዘማሪ ዲያቆን ፍፁም ከበደ

JOINE JOINE


https://t.me/zdfitsumkebe
https://t.me/zdfitsumkebe
https://t.me/zdfitsumkebe
2.7K views✞£iŧsûm✞, 06:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-25 17:47:22
በልጇ ቀኝ ያለችው

Vedio አውርደው ያድምጡ





በልጇ ቀኝ ያለችው አምላክን ያቀፈችው
አማላጅ ናት ማርያም ለሰው የተሰጠችው (2)



አምላክ አክብሯታል እናቱ አድርጓታል
ማርልኝ ስትለው ልጇም ይለመናል
የሰርጉ ቤት ውሃ ጣፍጭ ወይን የሆነው
ባዛኝቷ ምልጃ በድንግል ማርያም ነው


አዝ

ዮሐንስ ከቤቱ በደስታ አስገባት
ለኛም እናት ሆንሽን እርሱ ተቀብሎሽ
ምልጃሽ ይረዳናል አለ ከኛ ጋራ
ልጅሽም ይሰማል ያንቺን ስም ስንጠራ

አዝ

ሰው እና እግዚአብሔር የተገናኙበት
መልካሟ መሰላል ድንግል ማርያም ናት
የእርቅ ሰደቃችን ውቢቷ ከተማ
ምልክታችን ነሽ የዘላለም አርማ



ሕፃን ፌኔት አብርሃም

https://t.me/zdfitsumkebe
https://t.me/zdfitsumkebe
https://t.me/zdfitsumkebe
2.8K views✞£iŧsûm✞, 14:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-25 11:03:43 ዘማሪ ዲያቆን ፍፁም ከበደ pinned «✟ የክርስቲያኖች ሕይወት እና ባሕረ ኤርትራ ✟ ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘኑሲስለክርስቲያኖች ሁሉ አስተማሪ ስለሚሆን ሕይወቱ ሙሴ እና እስራኤል ባሕረ ኤርትራን መሻገራቸውን የክርስቲያኖች ሕይወት ምን መሆን እንዳለበት ጋር እያነፃፀር እንዲህ ያስተምራል ። ሰው በማንኛው ጊዜ ቢሆን ከግብፅ ሰራዊት ሲያመልጥ መንገዱን ይመራው ዘንድ መሪ ያገኛል ። መሪውም መንገዱን በሚገባ የሚያውቅ ነውና ። በውኆችም መካከል…»
08:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-24 20:48:41 ✟ የክርስቲያኖች ሕይወት እና ባሕረ ኤርትራ ✟

ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘኑሲስለክርስቲያኖች ሁሉ አስተማሪ ስለሚሆን ሕይወቱ ሙሴ እና እስራኤል ባሕረ ኤርትራን መሻገራቸውን የክርስቲያኖች ሕይወት ምን መሆን እንዳለበት ጋር እያነፃፀር እንዲህ ያስተምራል ።

ሰው በማንኛው ጊዜ ቢሆን ከግብፅ ሰራዊት ሲያመልጥ መንገዱን ይመራው ዘንድ መሪ ያገኛል ። መሪውም መንገዱን በሚገባ የሚያውቅ ነውና ። በውኆችም መካከል እንኳ ቢመራው መሪውን እየተከተለ ውኆችን ተሻግሮ መንገዱን ይቀጥላል ። ሰው በውኃ ሲሻገር ከኋላው በፍጥነት ይከተሉት የነበሩት የግብፅ ሰራዊት እርሱ ወደ ገባበት ውኃ ተከትለውት ይገባሉ ። ነገር ግን ብቻውን ከውኃው ይወጣል። እነርሱ ግን ውኃ ውስጥ ሰጥመው ይቀራሉ ። የግብፅ ሰራዊት የተባሉት የሰውን ነብስ ለክፍት ባርያ የሚያደርጉ ፍትወታትና ኅጣውእ ናቸው። እነርሱም የሰው ነፍስ ከባርነት ለመላቀቅ ወደ መሪዋ ስትገሰግስ እርሷን በባርነት ለማጽናት በፍጥነት የሚከተሏት ናቸው። ነገር ግን እርሷ የሚያድናትን ለምና ወደ ውኃ ስትገባ ተከትለዋት ቢገቡም ነገር ግን እርሷ ወጣች ፤ እነርሱ ግን በውኋ ተደምስሰው ቀሩ ። በሃይማኖት በትር እና በሚያበራ ዐምድ ደመና ምክንያት ውኃው ለእርሷ ሕይወትን የሚሰጣት ሆኗልና ።

ከውኃ የሚወጡ ሁሉ ከጠላት ሰራዊት አንዱን እንኳ ይዘው መውጣት አይገባቸውም ፤ በአንዱ ምክንያት ዳግም ወደ ባርነት ይያዛሉና ። በአማናዊው ሙሴ በክርስቶስ ያመኑትም ከተጠመቁ በኋላ ከመጠመቃቸውም በፈት ጦር ይሰብቁባቸው የነበሩትን እኩያትና ኃጣውእ በጥምቀት ከሞቱበት ዳግም ሊያስነሷቸው አይገባም ። ባሕሩን የተሻገሩ እስራኤል በትርን ለያዘው ለሙሴ እየታዘዙ ጉዞአቸውን እስከ ምድረ ርስት እንደቀጠሉ እንዲሁ ክርስቲያኖችም ጥምቀትን ተጠምቀው ጥምቀታቸው የተፈጸመበት ክህነት የያዙ ሐዋርያትና አበውን በመታዘዝ እስከ መንግስተ ሰማያት ድረስ ይደርሳሉ። እስራኤል በመንገዳቸው 12 ምንጮች እና 70 የዘንባባ ዛፎችን እንዳገኙ ፤ ክርስቲያኖችም በክርስትና ሕይወታቸው የ12ቱን ሐዋርያትና የሰባውን አርድእት ትምሕርት አግኝተው በጽድቅ ይጸናሉ። እስራኤል በሕሩን ከተሻገሩ በኋላ በጉዟቸው ከሙሴ እና ከደመናው እንዳልተለዩ እንዲሁ በምግባር ሊጸና የሚወድ ክርስቲያንም ከሙሴ (ማለትም ከሕገ እግዚአብሔርና) እና ከደመናው (ከሕጉ መንፈሳዊ ትርጉም) እራሱን መለየት የለበትም።


ባሕሩን በመሻገራቸው ምክንያት ነፍስ ንጽሕት ሆናለች ። ጠላት ከሚባሉ ኅጣውእ ራሷን ለየች ። በመንገዷም መራራ የሆነባትን ውኃ ጣፈጠላት ፤ከሰማይም መና ወረደላት ይህም መና የተባለም ኋላ ለሚያኑበት ምግብ (ኅብስት) ሆኖ ይበላ ዘንድ ከሰማይ የወረደው (ሰው የሆነ ) ክርስቶስ ነው። ነፍስ ይህን ሰማያዊ መና ብቻ ከተመገበች በልዕልና ያለ እግዚአብሔርን ማወቅ ትጀምራለች ። ወደዚህ እውቀት የሚያደርሳት መንገድ ደግሞ ንጽሕና ነው ። ይኸው እስራኤል ሰውነታቸውና ልብሳቸው አጥበው እንዲያነጹ የታዘዙት አፍአዊ ንጽሕና ብቻ ሳይሆን ውስጣዊ ንጽሕናም ነው ።


    ( "ማስያስ" የኦርቶዶክሳዊው ነገረ መለኮት መቅድማዊ ነጥቦች" ዲያቆን ሚክያስ አስረስ  ) መጽሐፍ የተወሰደ  የቻናሌ ቤተሰቦች  ይህ መጽሐፍ ይህን ጽሑፍ የመሰሉ ጥልቅ ምስጥራያትን የያዘ ነው ታነቡ ትማሩበት ዘንድ መልእክቴ ነው። 



ዘማሪ ዲያቆን ፍፁም ከበደ

JOINE JOINE


https://t.me/zdfitsumkebe
https://t.me/zdfitsumkebe
https://t.me/zdfitsumkebe
3.3K views✞£iŧsûm✞, 17:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ