2022-10-07 17:20:33
ንጻሬ ታሪክ2
ታሪክ ዳቦ ላይሆን ለምን ትተርካላችሁ?ለሚሉ ያሉኝ ጥያቄዎች፡፡
እኛ ኦርቶዶክሳውያን ታሪክን የምንረዳው መሠረተ ፍኖት ስለሆነ ነው እንጂ በዳቦ ልክ አናይም ፡፡ ያማ ቢሆን እንደ ዔሳው በመብል በቀየርነው ነበር፡፡
ታሪክ ትናንት ነው ግን ያላለፈ ዛሬም ነው፡፡ በእኛ እና በአባቶቻችን መካከል ዘመን እንጂ ልዩነት የለም የጴጥሮስ ሕይወት ሕይወታችን ነውና፡፡ታሪክ የልለው ሰው ከመሆን በላይ ምን ጨለማ ይኖራል?
ትናንት አንድ ዓይናችን ከዛሬ ጋራ ሲጨመር ደግሞ ሁለት ዓይናችን ነው፡፡ለነገ ስናስብ ሥስተኛ ዓይን ይኖረናል ማለት ነው፡፡
ታሪክ ከህሊና ቀውስ እና ከልቡና መንሸራተት ያድናል፡፡
አቡነ ዮሐንስ እንዳሉት ፦ የሞላ ታሪካችንን በጎደለ ሆዳችን አንቀይረውም፡፡ለመሆኑ፦
1 በዓለም ዓቀፍ ደረጃ በባህል እና ቅርስ ታሪክ ዙሪያ እንደ ባህል ሚኒስተር ባለው ተቅዋም ተቀጥረው ዳቦ የሚያገኙ ስንት ናቸው?
በሀገራችንስ?ከፊድራል እስከ ቀበሌ በባህል ወስጥ ዳቦ የሚያገኙ ስንት ናቸው?
2በዓለም ዐቀፍ ታሪክ ለመጎብኘት የሚንቀሳቀሱ የዓለም ህዝቦች ስንት ናቸው? በሀገራችንስ? እነሱን ለማስጎብኘት የተቀጠሩ ስንት ናቸው?
3 በተለያዩ የትምህርት ተቅዋማት የታሪክ መምህር ሁነው ዳቦ የሚያገኙ ስንት ናቸው?
4በተለያየ ቅርጽ አይነት በታሪክ ዙሪያ ላይ ጥናት የሚሠሩ እና መጽሐፍ ያሳተሙ ስንት ናቸው?
5በተለያየ ሚድያ ታሪክ እያወሩ ኑሯቸውን የሚመሩ ስንት ናቸው?
6ታሪክ ባይኖር ይህ ሁሉ በምን ይኖራል ብለው ያስባሉ?የዓለም ቅርጽስ ምን ይመስል ነበር?
የእኛው ሀገር ችግር የሞላ ህሊናንም ሆድንም የሚያጠግበውን ታሪክ በመጥላት ላይ የተመሠረተ የቀነጨረ አስተሳስብ ነው፡፡
በዚያውስ ላይ ከታሪክ በላይ መምህር አለ?የለም? ከታሪክ እና ከሥነ ፍጥረት የበለጠ መምህር በምድር ላይ የለም፡፡
(መምሕር ገብረ መድኅን እንየው)
https://t.me/zdfitsumkebe
https://t.me/zdfitsumkebe
https://t.me/zdfitsumkebe
1.2K views✞£iŧsûm✞, edited 14:20