Get Mystery Box with random crypto!

✞ የመስቀሉ መቀበር ✞ አይሁድ ግን ቅዱስ መስቀሉ በፈታቸው ልዩ ልዩ ተአምራትንና ብዙ ምልክቶችን | ዘማሪ ዲ/ን ፍፁም ከበደ

✞ የመስቀሉ መቀበር ✞

አይሁድ ግን ቅዱስ መስቀሉ በፈታቸው ልዩ ልዩ ተአምራትንና ብዙ ምልክቶችን ሲያደርግ እያዩ ማመን ተሳናቸው ቀደም ሲል ጌታ በመካከላቸው በሕይወት /በአካል/ እየተመላለሰ በሽተኞችን እየፈወሰ ሙታንን እያስነሳና
ኅብስት አበርክቶ እየመገበ ብዙ ተአምራት እያደረገ ቢያስተምራቸው ቀንተው ተመቅኝተው ገርፈውና ሰቅለው እንደገደሉት ሁሉ ይህንም ቅዱስ መስቀል ወደ ቆሻሻ ቦታ ከመጣላቸውም በላይ መሬት ቆፍረው ቀብረውት ነበር።

አይሁድ ንጹሐን መሰቀል በቆሻሻ ሲቀብሩ ከነጭራሹ ስመዝክሩ እንዲጠፍ ተረስቶ እንዲቀር ለማድረግ ከሁሉ በታች የጌታ መስቀልን አድርገው ሁለቱ ሽፍቶች ፈያታዊ ዘየማንና ፈያታዊ ዘጸጋም አብረው የተሰቀሉባቸው መስቀሎችንም አከታትለውና ደርበው ከቀበሩት በኃላ የከተማውን ቤት ጥራጊ ሁሉ በላዩ እንዲደፍ ዓዋጅ በማስነገር ተራራ እስኪያህል ድረስ በቆሻሻ አስደፍነው ነበር ።
በዚህ ዓይነት ከሁለት መቶ ዓመት በላይ ዘመን በማስቆጠርና ተከታታይ ትውልድን በማሳለፍ እየተረሳና ደብዛው እየጠፍ ከመሄድ በስተቀር የሚያስታውሰውና የሚያውቀው አልነበረም ። አይሁድ ይህንን ማድረጋቸው ኢትዮጵያዊው ቅዱስ ያሬድ <<መስቀል መልዕልተ ኩሉ ነገር>> መስቀል ከሁሉ በላይ ነው ሲል እንደተናገረው የማያቋርጥ የእግዚአብሔር ኃይል መገለጫ መሆኑን ባለመገንዘባቸው ነበር ።

ይሁን እንጂ ጌታ በቅዱስ ወንጌሉ << እስመ አልቦ ክዱን ዘኢይትከሰት ወአልቦ ኅቡዕ ዘኢይትዐወቅ>> የማይገለጥ የተከደ የማይታወቅ የተሰወረ ምንም የለምና ሲል አስቀድሞ እንደተናገረውና ሁሉ (ማቴ 1.፥26 ሉቃ 12፥2) ከሰው ኃይል ይልቅ የእግዚአብሔር ኃይል ከሰው ጥበብ ይልቅ የእግዚአብሔር ጥበብ ይበልጣልና እነሱ በሚገለጽባቸው ተአምራት ምልክቶች የተሰወረ እንዲወጣ ፈቃዱ በመሆኑ ለዚህ ምክንያት የሚሆኑትን ንጉስ ቆስጠንጢኖስን ቅድስት እሌኒን የቅዱስ መስቀልን እና መገኘት ምክንያት አድርጎ አስነሳ ።


( ፍኖተ ስብከት ሊቀ ስዩም አዲሱ ላቀው)


ዘማሪ ዲያቆን ፍፁም ከበደ


https://t.me/zdfitsumkebe
https://t.me/zdfitsumkebe
https://t.me/zdfitsumkebe