Get Mystery Box with random crypto!

የሴቷ ፈጣሪ ጌታ እግዚአብሔር ወንድ ልጅ ለመፍጠር ብዙ አልደከመም። ከመሬት አፈር አንሥቶ አንድ | ዘማሪ ዲ/ን ፍፁም ከበደ

የሴቷ ፈጣሪ

ጌታ እግዚአብሔር ወንድ ልጅ ለመፍጠር ብዙ አልደከመም። ከመሬት አፈር አንሥቶ አንድ ወንድ ፈጠረ!! ስሙንም አዳም አለው!! ሴት ሊፈጥር ሲል ጊዜው መሸበት። ከመፍጠር አረፈ። በሳምንቱ ሴት ሊፈጥር አስቦ ነበር። በወቅቱ ግን ደመ ግቡ ሴት ሊፈጥር ሲል ምክንያተ ስሕተት ሆና ታየችው። መፍጠር ቢታክተው ከወንድ ጎን ከፈላት። በቃ!!
ከዚህ በኋላ ብዙ ጠቢባን ተነሥተዋል። ሴት ልጅን ለመፍጠር ደክመዋል። ከዓለማየሁ ዋሴ በቀር ሴትን የፈጠረ የለም።
ወዳጄ ዶር ዓለማየሁ ግን ከዱዳሌብ አፈር ከሰማይ አየር ነሥቶ እንደ ሊጥ አቦካው። ከዚያ በብዕሩ እያጣቀሰ ይቺን ደመ ግቡ ሴት ፈጠረ። ስሟንም ሚተራሊዮን አለው!! ጌታም ይቺን ፍጥረት ሊያይ ከሰማይ ወረደ!! ዶክተሩ በመፍጠር እንደመሰለው ዐይቶ አደነቀ!!
(ማዕበል ፈጠነ የቅኔው ሊቅ )

እንዲህ አርጎ ስለ ገለፀው መጽሐፍ ጸሐፈ ሊቁ ያለውን ላካፍላቹሁ ወደድኩ ይበልጥ መጽሐፍን ብታነቡት ይህቺ ሴት ማን እንደሆነች ትገነዘባላቹሁ ያነበባቹሁም ድንቅስ አርጎ ገለፃት ብላቹሁ ትገረማላቹሁ!!! ።


ዲያቆን ፍፁም ከበደ

https://t.me/zdfitsumkebede
https://t.me/zdfitsumkebede